መዝሙር 1
1
አንደኛ መጽሐፍ
ከመዝሙር 1–41
መዝሙር 1
1ብፁዕ ነው፣
በክፉዎች ምክር የማይሄድ፣
በኀጢአተኞች መንገድ የማይቆም፣
በፌዘኞችም ወንበር የማይቀመጥ፤
2ነገር ግን ደስ የሚሠኘው በእግዚአብሔር ሕግ ነው፤
ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያሰላስለዋል።
3እርሱም በወራጅ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች፣
ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፣
ቅጠሏም እንደማይጠወልግ ዛፍ ነው፤
የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
4ክፉዎች ግን እንዲህ አይደሉም፤
ነገር ግን ነፋስ ጠራርጎ እንደሚወስደው
ገለባ ናቸው።
5ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ ፊት፣
ኀጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር መቆም አይችሉም።
6 እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ይጠብቃልና፤
የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.