መዝሙር 102
102
መዝሙር 102
በዐዘነና ልመናውን በእግዚአብሔር ፊት ባፈሰሰ ጊዜ፣ የተጨነቀ ሰው ጸሎት።
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤
ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ።
2በመከራዬ ቀን ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤
ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤
በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ መልስልኝ።
3ዘመኔ እንደ ጢስ ተንኖ ዐልቋልና፤
ዐጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ግለዋል።
4ልቤ ዋግ እንደ መታው ሣር ደርቋል፤
እህል መብላትም ዘንግቻለሁ።
5ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ፣
ዐጥንቴ ከቈዳዬ ጋራ ተጣበቀ።
6ይብራ መሰልሁ፤
በፍርስራሽ መካከል እንዳለ ጕጕት ሆንሁ።
7ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤
በቤቴ ጕልላት ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆንሁ።
8ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ይዘልፉኛል፤
የሚያክፋፉኝም ስሜን እንደ ርግማን ቈጥረውታል።
9ዐመድ እንደ እህል ቅሜአለሁና፤
መጠጤንም ከእንባ ጋራ ቀላቅያለሁ።
10ከቍጣህና ከመዓትህ የተነሣ፣
ወደ ላይ አንሥተኸኝ የነበርሁትን መልሰህ ጣልኸኝ።
11ዘመኖቼ እንደ ምሽት ጥላ ናቸው፤
እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።
12 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ተቀምጠሃል፤
ስምህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።
13ትነሣለህ፤ ጽዮንንም በርኅራኄ ዐይን ታያለህ፤
ለርሷ በጎነትህን የምታሳይበት ዘመን ነውና፤
የተወሰነውም ጊዜ ደርሷል።
14አገልጋዮችህ በድንጋዮቿ ደስ ይሰኛሉ፤
ለዐፈሯም ይሳሳሉ።
15ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ስም፣
የምድርም ነገሥታት ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ።
16 እግዚአብሔር ጽዮንን መልሶ ይሠራታልና፤
በክብሩም ይገለጣል።
17እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤
ልመናቸውንም አይንቅም።
18ወደ ፊት የሚፈጠር ሕዝብ እግዚአብሔርን ያወድስ ዘንድ፣
ይህ ለመጪው ትውልድ እንዲህ ተብሎ ይጻፍ፤
19“እግዚአብሔር በከፍታ ላይ ካለው መቅደሱ ወደ ታች ተመልክቷልና፤
ከሰማይም ሆኖ ምድርን አይቷል፤
20ይኸውም የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፣
ሞት የተፈረደባቸውንም ያድን ዘንድ ነው።”
21ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም በጽዮን፣
ምስጋናውም በኢየሩሳሌም ይታወጃል፤
22ይህም፣ ሕዝቦችና መንግሥታት፣
እግዚአብሔርን ለማምለክ በአንድነት ሲሰበሰቡ ይሆናል።
23ብርታቴን መንገድ ላይ ቀጨው፤#102፥23 ወይም በኀይሉ ብርታቴን ቀጨው
ዕድሜዬንም በዐጭሩ አስቀረው።
24እኔም እንዲህ አልሁ፤
“አምላኬ ሆይ፤ በዘመኔ እኩሌታ አትውሰደኝ፤
ዘመናትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራሉ።
25አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፤
ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።
26እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤
ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፤
እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፤
እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ።
27አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤
ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።
28የአገልጋዮችህ ልጆች ተደላድለው ይኖራሉ፤
ዘራቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል።”
Currently Selected:
መዝሙር 102: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
መዝሙር 102
102
መዝሙር 102
በዐዘነና ልመናውን በእግዚአብሔር ፊት ባፈሰሰ ጊዜ፣ የተጨነቀ ሰው ጸሎት።
1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጸሎቴን ስማ፤
ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ።
2በመከራዬ ቀን ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤
ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤
በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ መልስልኝ።
3ዘመኔ እንደ ጢስ ተንኖ ዐልቋልና፤
ዐጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ግለዋል።
4ልቤ ዋግ እንደ መታው ሣር ደርቋል፤
እህል መብላትም ዘንግቻለሁ።
5ከጩኸቴ ድምፅ የተነሣ፣
ዐጥንቴ ከቈዳዬ ጋራ ተጣበቀ።
6ይብራ መሰልሁ፤
በፍርስራሽ መካከል እንዳለ ጕጕት ሆንሁ።
7ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤
በቤቴ ጕልላት ላይ እንዳለ ብቸኛ ወፍ ሆንሁ።
8ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ይዘልፉኛል፤
የሚያክፋፉኝም ስሜን እንደ ርግማን ቈጥረውታል።
9ዐመድ እንደ እህል ቅሜአለሁና፤
መጠጤንም ከእንባ ጋራ ቀላቅያለሁ።
10ከቍጣህና ከመዓትህ የተነሣ፣
ወደ ላይ አንሥተኸኝ የነበርሁትን መልሰህ ጣልኸኝ።
11ዘመኖቼ እንደ ምሽት ጥላ ናቸው፤
እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።
12 እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ለዘላለም በዙፋንህ ተቀምጠሃል፤
ስምህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።
13ትነሣለህ፤ ጽዮንንም በርኅራኄ ዐይን ታያለህ፤
ለርሷ በጎነትህን የምታሳይበት ዘመን ነውና፤
የተወሰነውም ጊዜ ደርሷል።
14አገልጋዮችህ በድንጋዮቿ ደስ ይሰኛሉ፤
ለዐፈሯም ይሳሳሉ።
15ሕዝቦች የእግዚአብሔርን ስም፣
የምድርም ነገሥታት ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ።
16 እግዚአብሔር ጽዮንን መልሶ ይሠራታልና፤
በክብሩም ይገለጣል።
17እርሱ ወደ ችግረኞች ጸሎት ይመለከታል፤
ልመናቸውንም አይንቅም።
18ወደ ፊት የሚፈጠር ሕዝብ እግዚአብሔርን ያወድስ ዘንድ፣
ይህ ለመጪው ትውልድ እንዲህ ተብሎ ይጻፍ፤
19“እግዚአብሔር በከፍታ ላይ ካለው መቅደሱ ወደ ታች ተመልክቷልና፤
ከሰማይም ሆኖ ምድርን አይቷል፤
20ይኸውም የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፣
ሞት የተፈረደባቸውንም ያድን ዘንድ ነው።”
21ስለዚህ የእግዚአብሔር ስም በጽዮን፣
ምስጋናውም በኢየሩሳሌም ይታወጃል፤
22ይህም፣ ሕዝቦችና መንግሥታት፣
እግዚአብሔርን ለማምለክ በአንድነት ሲሰበሰቡ ይሆናል።
23ብርታቴን መንገድ ላይ ቀጨው፤#102፥23 ወይም በኀይሉ ብርታቴን ቀጨው
ዕድሜዬንም በዐጭሩ አስቀረው።
24እኔም እንዲህ አልሁ፤
“አምላኬ ሆይ፤ በዘመኔ እኩሌታ አትውሰደኝ፤
ዘመናትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራሉ።
25አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፤
ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።
26እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤
ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፤
እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፤
እነርሱም ወዲያ ይጣላሉ።
27አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤
ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።
28የአገልጋዮችህ ልጆች ተደላድለው ይኖራሉ፤
ዘራቸውም በፊትህ ጸንቶ ይኖራል።”
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.