መዝሙር 108

108
መዝሙር 108
108፥1-5 ተጓ ምብ – መዝ 57፥7-11
108፥6-13 ተጓ ምብ – መዝ 60፥5-12
የዳዊት መዝሙር፤ ማሕሌት።
1አምላክ ሆይ፤ ልቤ ጽኑ ነው፤
እቀኛለሁ፤ በፍጹም ነፍሴም እዘምራለሁ።
2በገናና መሰንቆም ተነሡ፤
እኔም ማልጄ እነሣለሁ።
3 ጌታ ሆይ፤ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤
በሰዎችም መካከል እዘምርልሃለሁ።
4ምሕረትህ ከሰማያት በላይ ታላቅ ናትና፤
ታማኝነትህም እስከ ሰማያት ትደርሳለች።
5አምላክ ሆይ፤ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ በል፤
ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትንሰራፋ።
6ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፣
በቀኝ እጅህ ርዳን፤ መልስልንም።
7እግዚአብሔር ከመቅደሱ ተናገረ፤
“ደስ እያለኝ ሴኬምን እከፋፍላለሁ፤
የሱኮትንም ሸለቆ እለካለሁ።
8ገለዓድ የእኔ ነው፤ ምናሴም የእኔ ነው፤
ኤፍሬም የራስ ቍሬ ነው፤
ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው።
9ሞዓብ የመታጠቢያ ገንዳዬ ነው፤
በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እወረውራለሁ፤
በፍልስጥኤም ላይ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።”
10ወደ ተመሸገችው ከተማ ማን ይወስደኛል?
ወደ ኤዶምያስ ማን ይመራኛል?
11እግዚአብሔር ሆይ፤ የጣልኸን አንተ አይደለህምን?
አምላክ ሆይ፤ ከሰራዊታችንም ጋራ አትወጣም።
12በጠላት ላይ ድልን አቀዳጀን፤
የሰው ርዳታ ከንቱ ነውና።
13በእግዚአብሔር ክንደ ብርቱ እንሆናለን፤
ጠላቶቻችንን የሚረጋግጥልን እርሱ ነውና።

Currently Selected:

መዝሙር 108: NASV

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ