መዝሙር 124

124
መዝሙር 124
የዳዊት መዝሙረ መዓርግ።
1እስራኤል እንዲህ ይበል፤
እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ባይሆን ኖሮ፣
2ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፣
እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ባይሆን ኖሮ፣
3ቍጣቸው በላያችን በነደደ ጊዜ፣
በቁመናችን በዋጡን ነበር፤
4ጐርፍ ባጥለቀለቀን፣
ፈረሰኛው ውሃ ባሰጠመን፣
5ደራሽ ውሃም ጠራርጎ በወሰደን ነበር።
6በጥርሳቸው ከመዘንጠል የጠበቀን፣
እግዚአብሔር ይባረክ።
7ነፍሳችን እንደ ወፍ፣
ከዐዳኝ ወጥመድ አመለጠች፤
ወጥመዱ ተሰበረ፤
እኛም አመለጥን።
8የሰማይና የምድር ፈጣሪ፣
የእግዚአብሔር ስም ረዳታችን ነው።

Currently Selected:

መዝሙር 124: NASV

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ