መዝሙር 127

127
መዝሙር 127
የሰሎሞን መዝሙረ መዓርግ።
1 እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣
ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤
እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣
ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።
2የዕለት ጕርስ ለማግኘት በመጣር፣
ማልዳችሁ መነሣታችሁ፣
አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው፤
እርሱ ለሚወድዳቸው እንቅልፍን ያድላልና።#127፥2 ወይም ተኝተው ሳሉ ምግብ ያዘጋጅላቸዋል።
3እነሆ፤ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፤
የማሕፀንም ፍሬ ከቸርነቱ የሚገኝ ነው።
4በወጣትነት የተገኙ ወንዶች ልጆች፣
በጦረኛ እጅ እንዳሉ ፍላጾች ናቸው።
5ብፁዕ ነው፤
ኰረጆዎቹ በእነዚህ የተሞሉ ሰው፤
ከጠላቶቻቸው ጋራ በአደባባይ በሚሟገቱበት ጊዜ፣
አይዋረዱም።

Currently Selected:

መዝሙር 127: NASV

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ