የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙር 142

142
መዝሙር 142
ዋሻ ውስጥ በነበረ ጊዜ፤ የዳዊት ማስኪል፤#142፥0 የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ የሚያሳይ ወይም በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም። ጸሎት።
1ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤
ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር ልመና አቀርባለሁ።
2ብሶቴን በፊቱ አፈስሳለሁ፤
ችግሬንም በፊቱ እናገራለሁ።
3መንፈሴ በውስጤ ሲዝል፣
መንገዴን የምታውቅ አንተ ነህ፤
በመተላለፊያ መንገዴ ላይ፣
ወጥመድ በስውር ዘርግተውብኛል።
4ወደ ቀኜ ተመልከት፤ እይም፤
ስለ እኔ የሚገድደው የለም፤
ማምለጫም የለኝም፤
ስለ ነፍሴም ደንታ ያለው የለም።
5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤
ደግሞም፣ “አንተ መጠጊያዬ ነህ፤
በሕያዋንም ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ” እላለሁ።
6እጅግ ተስፋ ቈርጫለሁና፣
ጩኸቴን ስማ፤
ከዐቅም በላይ ሆነውብኛልና፣
ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።
7ስምህን አመሰግን ዘንድ፣ ነፍሴን ከእስር አውጣት፤
ከምታደርግልኝም በጎ ነገር የተነሣ፣
ጻድቃን በዙሪያዬ ይሰበሰባሉ።

Currently Selected:

መዝሙር 142: NASV

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ