መዝሙር 150
150
መዝሙር 150
1ሃሌ ሉያ።#150፥1 አንዳንዶች ከ6 ጭምር እግዚአብሔር ይመስገን ይላሉ።
እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤
በታላቅ ጠፈሩ አመስግኑት።
2ስለ ብርቱ ሥራው አመስግኑት፤
እጅግ ታላቅ ነውና አመስግኑት።
3በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤
በበገናና በመሰንቆ ወድሱት።
4በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑት፤
በባለአውታር መሣሪያና በእንቢልታ አመስግኑት።
5ተርገብጋቢ ድምፅ ባለው ጸናጽል አመስግኑት፤
ድምፀ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት።
6እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን።
ሃሌ ሉያ።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.