መዝሙር 20
20
መዝሙር 20
ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር።
1 እግዚአብሔር በጭንቅ ቀን ይስማህ፤
የያዕቆብም አምላክ ስም ይጠብቅህ።
2ከመቅደሱ ረድኤት ይላክልህ፤
ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ።
3ቍርባንህን ሁሉ ያስብልህ፤
የሚቃጠል መሥዋዕትህን ይቀበልልህ። ሴላ
4የልብህን መሻት ይስጥህ፤
ዕቅድህን ሁሉ ያከናውንልህ።
5በአንተ ድል ደስ ይበለን፤
በአምላካችን ስም አርማችንን ከፍ እናደርጋለን።
እግዚአብሔር የለመንኸውን ሁሉ ይፈጽምልህ።
6 እግዚአብሔር፣ የቀባውን እንደሚያድን
አሁን ዐወቅሁ።
የማዳን ኀይል ባለው ቀኝ እጁ፣
ከተቀደሰው ሰማይ ይመልስለታል።
7እነዚህ በሠረገላ፣ እነዚያ በፈረስ ይመካሉ፤
እኛ ግን ትምክሕታችን የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም ነው።
8እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፤
እኛ ግን ተነሣን፤ ጸንተንም ቆምን።
9 እግዚአብሔር ሆይ፤ ንጉሥን አድን፤
እኛም በጠራንህ ቀን ስማን።#20፥9 ወይም አድን! ንጉሥ ሆይ፤ ስማን
Currently Selected:
መዝሙር 20: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
መዝሙር 20
20
መዝሙር 20
ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር።
1 እግዚአብሔር በጭንቅ ቀን ይስማህ፤
የያዕቆብም አምላክ ስም ይጠብቅህ።
2ከመቅደሱ ረድኤት ይላክልህ፤
ከጽዮንም ደግፎ ይያዝህ።
3ቍርባንህን ሁሉ ያስብልህ፤
የሚቃጠል መሥዋዕትህን ይቀበልልህ። ሴላ
4የልብህን መሻት ይስጥህ፤
ዕቅድህን ሁሉ ያከናውንልህ።
5በአንተ ድል ደስ ይበለን፤
በአምላካችን ስም አርማችንን ከፍ እናደርጋለን።
እግዚአብሔር የለመንኸውን ሁሉ ይፈጽምልህ።
6 እግዚአብሔር፣ የቀባውን እንደሚያድን
አሁን ዐወቅሁ።
የማዳን ኀይል ባለው ቀኝ እጁ፣
ከተቀደሰው ሰማይ ይመልስለታል።
7እነዚህ በሠረገላ፣ እነዚያ በፈረስ ይመካሉ፤
እኛ ግን ትምክሕታችን የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም ነው።
8እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፤
እኛ ግን ተነሣን፤ ጸንተንም ቆምን።
9 እግዚአብሔር ሆይ፤ ንጉሥን አድን፤
እኛም በጠራንህ ቀን ስማን።#20፥9 ወይም አድን! ንጉሥ ሆይ፤ ስማን
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.