መዝሙር 29

29
መዝሙር 29
የዳዊት መዝሙር።
1እናንተ ኀያላን፣ ለእግዚአብሔር ስጡ፤
ክብርንና ብርታትን ለእግዚአብሔር ስጡ።
2ለስሙ የሚገባ ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤
በቅድስናው ግርማ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
3እግዚአብሔር ድምፅ በውሆች ላይ ነው፤
የክብር አምላክ አንጐደጐደ፤
እግዚአብሔር በታላላቅ ውሆች ላይ አንጐደጐደ።
4እግዚአብሔር ድምፅ ኀያል ነው፤
እግዚአብሔር ድምፅ ግርማዊ ነው።
5እግዚአብሔር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፤
እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይሰባብራል።
6ሊባኖስን እንደ ጥጃ፣
ሢርዮንንም#29፥6 አርሞንዔም የተባለው ተራራ ነው። እንደ አውራሪስ ግልገል ያዘልላል።
7እግዚአብሔር ድምፅ
የእሳት ነበልባል ይረጫል።
8እግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤
እግዚአብሔር ድምፅ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
9እግዚአብሔር ድምፅ ወርካዎችን ይወዘውዛል፤#29፥9 ወይም እግዚአብሔር አጋዘን እንድትወልድ ያደርጋል
ጫካዎችንም ይመነጥራል፤
ሁሉም በርሱ ቤተ መቅደስ ሆኖ “ይክበር!” ይላል።
10 እግዚአብሔር በጐርፍ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ ተቀምጧል፤#29፥10 ወይም ይቀመጣል
እግዚአብሔር በንጉሥነቱ ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።
11 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታትን ይሰጣል፤
እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።

Currently Selected:

መዝሙር 29: NASV

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ