መዝሙር 46

46
መዝሙር 46#46 ርእስ ምናልባት የሙዚቃውን ሁኔታ ሊያሳይ ይችላል።
ለመዘምራን አለቃ፤ የቆሬ ልጆች መዝሙር፤ በአላሞት#46 ርእስ በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም። መዝሙር።
1አምላካችን መጠጊያችንና ኀይላችን፣
በሚደርስብን መከራ ሁሉ የቅርብ ረዳታችን ነው።
2ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ እንኳ፣
ተራሮችም ወደ ባሕር ጥልቅ ቢሰምጡ አንፈራም።
3ውሆች ቢያስገመግሙ፣ ዐረፋ ቢደፍቁም፣ ተራሮችም ከውሆቹ ሙላት የተነሣ
ቢንቀጠቀጡም አንደናገጥም። ሴላ
4የእግዚአብሔርን ከተማ፣
የልዑልን የተቀደሰ ማደሪያ ደስ የሚያሰኙ የወንዝ ፈሳሾች አሉ።
5እግዚአብሔር በመካከሏ ነው፤ አትናወጥም፤
አምላክ በማለዳ ይረዳታል።
6ሕዝቦች በዐመፅ ተነሡ፤ መንግሥታትም ወደቁ፤
ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ፤ ምድርም ቀለጠች።
7የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው፤
የያዕቆብም አምላክ መጠጊያችን ነው። ሴላ
8ኑና የእግዚአብሔርን ሥራ፣
ምድርንም እንዴት ባድማ እንዳደረጋት እዩ።
9ከዳር እስከ ዳር ጦርነትን ከምድር ያስወግዳል፤
ቀስትን ይሰብራል፤ ጦርን ያነክታል፤
ጋሻንም#46፥9 ወይም ሠረገላንም በእሳት ያቃጥላል።
10“ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤
በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፤
በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”
11የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው፤
የያዕቆብም አምላክ መጠጊያችን ነው። ሴላ

Currently Selected:

መዝሙር 46: NASV

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ