መዝሙር 49
49
መዝሙር 49
ለመዘምራን አለቃ፤ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
1እናንተ ሕዝቦች ሁላችሁ፤ ይህን ስሙ፤
በዓለም የምትኖሩ ሁሉ፤ ይህን አድምጡ።
2ዝቅተኞችና ከፍተኞች#49፥2 ዕብራይስጡ የአዳም ልጆችና የሰው ልጆች ይላል።፣
ባለጠጎችና ድኾች ይህን በአንድነት ስሙ።
3አፌ የጥበብን ቃል ይናገራል፤
የልቤም ሐሳብ ማስተዋልን ይሰጣል።
4ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፤
እንቆቅልሼንም በበገና እፈታለሁ።
5የአጭበርባሪዎች ክፋት በከበበኝ ጊዜ፣
በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?
6በሀብታቸው የሚመኩትን፣
በብልጽግናቸውም የሚታመኑትን ለምን እፈራለሁ?
7የሌላውን ሕይወት መቤዠት የሚችል ሰው፣
ወይም ለእግዚአብሔር ወጆ የሚከፍልለት ማንም የለም።
8የነፍስ ቤዛ ውድ ነውና፤
በቂ ዋጋም ከቶ ሊገኝለት አይችልም፤
9በዚህም ዘላለም ይኖራል፣
መበስበስንም አያይም።
10ጠቢባን ሟቾች መሆናቸው የሚታይ ነው፤
ሞኝና ደነዝም ይጠፋሉ፤
ጥሪታቸውንም ለሌላው ጥለው ይሄዳሉ።
11መሬቶችን በስማቸው ቢሰይሙም፣
መቃብራቸው የዘላለም ቤታቸው፣
ከትውልድ እስከ ትውልድም መኖሪያቸው ይሆናል።
12ሰው በሀብቱ እንደ ተከበረ አይዘልቅም፤
ታይተው የሚጠፉ እንስሳትን ይመስላል።#49፥12 በሰብዓ ሊቃናት ትርጕምና በሱርስቱ ቅጅ 12 ከ20 ጋራ አንድ ዐይነት ነው፤ ዕብራይስጡ ግን ከዚህ ይለያል።
13ይህ የተላላዎች ዕድል ፈንታ፣
የእነርሱንም አባባል ተቀብለው ለሚከተሏቸው፣
መጨረሻ ግብ ነው። ሴላ
14እንደ በጎች ለሲኦል#49፥14 በዚህ እና በ15 ላይ ዕብራይስጡ ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ አንዳንድ የእንግሊዝኛ ቅጆች ግን መቃብር ይላሉ። የተዳረጉ ናቸው፤
ሞትም እረኛቸው ይሆናል፤
ቅኖች በማለዳ ይገዟቸዋል፤
አካላቸው ከክብር ቤታቸው ርቆ፣
በሲኦል ይፈራርሳል።
15እግዚአብሔር ግን ነፍሴን#49፥15 ወይም ሕይወቴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል፤
በርግጥም ይወስደኛል። ሴላ
16ሰው ባለጠጋ ሲሆን፣
የቤቱም ክብር ሲበዛለት አትፍራ፤
17በሚሞትበትም ጊዜ ይዞት የሚሄደው አንዳች የለምና፤
ክብሩም ዐብሮት አይወርድም።
18በሕይወት ሳለ ራሱን እንደ ተባረከ ቢቈጥርም፣
ሰዎች በበለጸግህ ጊዜ ቢያወድሱህም፣
19ብርሃን ከቶ ወደማያዩት፣
ወደ አባቶች ማኅበር ይቀላቀላል።
20ሰው በሀብቱ እንደ ተከበረ አይዘልቅም፤
ታይተው የሚጠፉ እንስሳትን ይመስላል።
Currently Selected:
መዝሙር 49: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
መዝሙር 49
49
መዝሙር 49
ለመዘምራን አለቃ፤ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
1እናንተ ሕዝቦች ሁላችሁ፤ ይህን ስሙ፤
በዓለም የምትኖሩ ሁሉ፤ ይህን አድምጡ።
2ዝቅተኞችና ከፍተኞች#49፥2 ዕብራይስጡ የአዳም ልጆችና የሰው ልጆች ይላል።፣
ባለጠጎችና ድኾች ይህን በአንድነት ስሙ።
3አፌ የጥበብን ቃል ይናገራል፤
የልቤም ሐሳብ ማስተዋልን ይሰጣል።
4ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፤
እንቆቅልሼንም በበገና እፈታለሁ።
5የአጭበርባሪዎች ክፋት በከበበኝ ጊዜ፣
በክፉ ቀን ለምን እፈራለሁ?
6በሀብታቸው የሚመኩትን፣
በብልጽግናቸውም የሚታመኑትን ለምን እፈራለሁ?
7የሌላውን ሕይወት መቤዠት የሚችል ሰው፣
ወይም ለእግዚአብሔር ወጆ የሚከፍልለት ማንም የለም።
8የነፍስ ቤዛ ውድ ነውና፤
በቂ ዋጋም ከቶ ሊገኝለት አይችልም፤
9በዚህም ዘላለም ይኖራል፣
መበስበስንም አያይም።
10ጠቢባን ሟቾች መሆናቸው የሚታይ ነው፤
ሞኝና ደነዝም ይጠፋሉ፤
ጥሪታቸውንም ለሌላው ጥለው ይሄዳሉ።
11መሬቶችን በስማቸው ቢሰይሙም፣
መቃብራቸው የዘላለም ቤታቸው፣
ከትውልድ እስከ ትውልድም መኖሪያቸው ይሆናል።
12ሰው በሀብቱ እንደ ተከበረ አይዘልቅም፤
ታይተው የሚጠፉ እንስሳትን ይመስላል።#49፥12 በሰብዓ ሊቃናት ትርጕምና በሱርስቱ ቅጅ 12 ከ20 ጋራ አንድ ዐይነት ነው፤ ዕብራይስጡ ግን ከዚህ ይለያል።
13ይህ የተላላዎች ዕድል ፈንታ፣
የእነርሱንም አባባል ተቀብለው ለሚከተሏቸው፣
መጨረሻ ግብ ነው። ሴላ
14እንደ በጎች ለሲኦል#49፥14 በዚህ እና በ15 ላይ ዕብራይስጡ ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ አንዳንድ የእንግሊዝኛ ቅጆች ግን መቃብር ይላሉ። የተዳረጉ ናቸው፤
ሞትም እረኛቸው ይሆናል፤
ቅኖች በማለዳ ይገዟቸዋል፤
አካላቸው ከክብር ቤታቸው ርቆ፣
በሲኦል ይፈራርሳል።
15እግዚአብሔር ግን ነፍሴን#49፥15 ወይም ሕይወቴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል፤
በርግጥም ይወስደኛል። ሴላ
16ሰው ባለጠጋ ሲሆን፣
የቤቱም ክብር ሲበዛለት አትፍራ፤
17በሚሞትበትም ጊዜ ይዞት የሚሄደው አንዳች የለምና፤
ክብሩም ዐብሮት አይወርድም።
18በሕይወት ሳለ ራሱን እንደ ተባረከ ቢቈጥርም፣
ሰዎች በበለጸግህ ጊዜ ቢያወድሱህም፣
19ብርሃን ከቶ ወደማያዩት፣
ወደ አባቶች ማኅበር ይቀላቀላል።
20ሰው በሀብቱ እንደ ተከበረ አይዘልቅም፤
ታይተው የሚጠፉ እንስሳትን ይመስላል።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.