መዝሙር 52
52
መዝሙር 52
ለመዘምራን አለቃ፤ ኤዶማዊው ዶይቅ ወደ ሳኦል መጥቶ፣ “ዳዊት ወደ አቢሜሌክ ቤት መጥቷል” ብሎ በነገረው ጊዜ፤ የዳዊት ማስኪል።#52 ርእስ የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ የሚያሳይ ወይም በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም።
1ኀያል ሆይ፤ በክፋት ለምን ትኵራራለህ?
አንተ በእግዚአብሔር ዐይን የተናቅህ፣
እንዴትስ ዘወትር ትታበያለህ?
2አንተ ማታለልን ሥራዬ ብለህ የያዝህ፤
አንደበትህ እንደ ሰላ ምላጭ፣
ጥፋትን ያውጠነጥናል።
3ከበጎ ነገር ይልቅ ክፋትን፣
ጽድቅን ከመናገር ይልቅ ዐመፃን ወደድህ። ሴላ
4አንተ አታላይ አንደበት ሆይ፤
ጐጂ ቃላትን ሁሉ ወደድህ!
5እግዚአብሔር ግን ለዘላለም ያንኰታኵትሃል፤
ይነጥቅሃል፤ ከድንኳንህም መንጥቆ ያወጣሃል፤
ከሕያዋንም ምድር ይነቅልሃል። ሴላ
6ጻድቃን ይህን አይተው ይፈራሉ፤
እንዲህ እያሉም ይሥቁበታል፤
7“እግዚአብሔርን መጠጊያ ያላደረገ፣
ነገር ግን በሀብቱ ብዛት የተመካ፣
በክፋቱም የበረታ፣
ያ ሰው እነሆ!”
8እኔ ግን በእግዚአብሔር ቤት፣
እንደ ለመለመ የወይራ ዛፍ ነኝ፤
ከዘላለም እስከ ዘላለም፣
በእግዚአብሔር ምሕረት እታመናለሁ።
9ስላደረግኸው ነገር ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፤
ስምህ መልካም ነውና፣
ስምህን ተስፋ አደርጋለሁ፤
በቅዱሳንም መካከል አመሰግንሃለሁ።
Currently Selected:
መዝሙር 52: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
መዝሙር 52
52
መዝሙር 52
ለመዘምራን አለቃ፤ ኤዶማዊው ዶይቅ ወደ ሳኦል መጥቶ፣ “ዳዊት ወደ አቢሜሌክ ቤት መጥቷል” ብሎ በነገረው ጊዜ፤ የዳዊት ማስኪል።#52 ርእስ የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ የሚያሳይ ወይም በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም።
1ኀያል ሆይ፤ በክፋት ለምን ትኵራራለህ?
አንተ በእግዚአብሔር ዐይን የተናቅህ፣
እንዴትስ ዘወትር ትታበያለህ?
2አንተ ማታለልን ሥራዬ ብለህ የያዝህ፤
አንደበትህ እንደ ሰላ ምላጭ፣
ጥፋትን ያውጠነጥናል።
3ከበጎ ነገር ይልቅ ክፋትን፣
ጽድቅን ከመናገር ይልቅ ዐመፃን ወደድህ። ሴላ
4አንተ አታላይ አንደበት ሆይ፤
ጐጂ ቃላትን ሁሉ ወደድህ!
5እግዚአብሔር ግን ለዘላለም ያንኰታኵትሃል፤
ይነጥቅሃል፤ ከድንኳንህም መንጥቆ ያወጣሃል፤
ከሕያዋንም ምድር ይነቅልሃል። ሴላ
6ጻድቃን ይህን አይተው ይፈራሉ፤
እንዲህ እያሉም ይሥቁበታል፤
7“እግዚአብሔርን መጠጊያ ያላደረገ፣
ነገር ግን በሀብቱ ብዛት የተመካ፣
በክፋቱም የበረታ፣
ያ ሰው እነሆ!”
8እኔ ግን በእግዚአብሔር ቤት፣
እንደ ለመለመ የወይራ ዛፍ ነኝ፤
ከዘላለም እስከ ዘላለም፣
በእግዚአብሔር ምሕረት እታመናለሁ።
9ስላደረግኸው ነገር ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፤
ስምህ መልካም ነውና፣
ስምህን ተስፋ አደርጋለሁ፤
በቅዱሳንም መካከል አመሰግንሃለሁ።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.