መዝሙር 8
8
መዝሙር 8
ለመዘምራን አለቃ፤ በጊጊት#8፥0 በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም። የሚዜም፤ የዳዊት መዝሙር።
1 እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤
ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው!
ክብርህ ከሰማያት በላይ፣
ከፍ ከፍ ብሏል።
2ከልጆችና ጡት ከሚጠቡ ሕፃናት አፍ፣
ምስጋናን#8፥2 ወይም ብርታትን አዘጋጀህ፤
ከጠላትህ የተነሣ፣
ባላንጣንና ቂመኛን ጸጥ ታሰኝ ዘንድ።
3የጣቶችህን ሥራ፣
ሰማያትህን ስመለከት፣
በስፍራቸው ያኖርሃቸውን፣
ጨረቃንና ከዋክብትን ሳይ፣
4በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?
ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?
5ከመላእክት#8፥5 ኤሎሂም በዚህ ክፍል አምላክ ተብሎ ሊተረጐም ይችላል። በጥቂት አሳነስኸው፤
ክብርንና ግርማን አጐናጸፍኸው።
6በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤
ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፤
7በጎችንና ላሞችን ሁሉ፣
የዱር አራዊትንም፣
8የሰማይ ወፎችንና
የባሕር ዓሦችን፣
በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትንም ሁሉ አስገዛህለት።
9 እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤
ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው!
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.