መዝሙር 89
89
መዝሙር 89
የይዝራኤላዊው የኤታን ማስኪል።#89፥0 የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ የሚያሳይ ወይም በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም።
1ስለ እግዚአብሔር ምሕረት ለዘላለም እዘምራለሁ፤
በአፌም ታማኝነትህን ከትውልድ እስከ ትውልድ እገልጻለሁ።
2ምሕረትህን ለዘላለም እንደምትመሠርት፣
ታማኝነትህንም በሰማይ እንደምታጸና እናገራለሁ።
3አንተም እንዲህ ብለሃል፤ “ከመረጥሁት ጋራ ኪዳን ገብቻለሁ፤
ለባሪያዬ ለዳዊት ምያለሁ፤
4‘ዘርህን ለዘላለም እተክላለሁ፤
ዙፋንህንም ከትውልድ እስከ ትውልድ አጸናለሁ።’ ” ሴላ
5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያት ድንቅ ሥራህን፣
ታማኝነትህንም በቅዱሳን ጉባኤ መካከል ያወድሳሉ፤
6በላይ በሰማያት ከእግዚአብሔር ጋራ ማን ሊስተካከል ይችላል?
ከሰማያውያን ፍጥረታትስ መካከል ማን እግዚአብሔርን ይመስለዋል?
7እግዚአብሔር በቅዱሳን ጉባኤ መካከል በጣም የሚፈራ፣
በዙሪያውም ካሉት ሁሉ በላይ እጅግ የሚከበር ነው።
8የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ኀያል ነህ፤ ታማኝነትህም ከብቦሃል።
9የባሕርን ቍጣ ትቈጣጠራለህ፤
ሞገዱም ሲነሣ ጸጥ ታደርገዋለህ።
10አንተ ረዓብን የተሰየፈ ያህል አደቀቅኸው፤
በብርቱ ክንድህም ጠላቶችህን በተንሃቸው።
11ሰማያት የአንተ ናቸው፤ ምድርም የአንተ ናት፤
ዓለምንና በውስጧ ያለውን ሁሉ አንተ መሠረትህ።
12ሰሜንንና ደቡብን የፈጠርህ አንተ ነህ፤
ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ሐሤት ያደርጋሉ።
13አንተ ክንደ ብርቱ ነህ፤
እጅህ ኀያል ናት፤ ቀኝ እጅህም ከፍ ከፍ ያለች ናት።
14ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረቶች ናቸው፤
ምሕረትና ታማኝነት በፊትህ ይሄዳሉ።
15ብፁዕ ነው፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ እልልታን የሚያውቅ፣
በፊትህም ብርሃን የሚሄድ ሕዝብ፤
16ቀኑን ሙሉ በስምህ ደስ ይላቸዋል፤
በጽድቅህም ሐሤት ያደርጋሉ፤
17አንተ የብርታታቸው ክብር ነህና፤
በሞገስህም ቀንዳችንን#89፥17 የጥንካሬ ምልክት ነው። ከፍ ከፍ አደረግህ።
18ጋሻችን#89፥18 ወይም ልዑል ማለት ነው። የእግዚአብሔር ነውና፤
ንጉሣችንም የራሱ የእስራኤል ቅዱስ ነው።
19በዚያ ጊዜ በራእይ ተናገርህ፤
ታማኝ ሕዝብህንም እንዲህ አልህ፤
“ኀያሉን ሰው ሥልጣን አጐናጸፍሁት፤
ከሕዝብ መካከል የተመረጠውንም ከፍ ከፍ አደረግሁት።
20ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁ፤
በተቀደሰው ዘይቴም ቀባሁት።
21እጄ ይደግፈዋል፤
ክንዴም ያበረታዋል።
22በጠላት አይበለጥም፤
ክፉ ሰውም አይበግረውም።
23ባላንጣዎቹን በፊቱ አደቅቃቸዋለሁ፤
ጠላቶቹንም እቀጠቅጣለሁ።
24ታማኝነቴና ምሕረቴ ከርሱ ጋራ ይሆናል፤
በስሜም ቀንዱ ከፍ ከፍ ይላል።
25እጁን በባሕር ላይ፣
ቀኝ እጁንም በወንዞች ላይ አኖራለሁ።
26እርሱም፣ ‘አንተ አባቴ ነህ፤
አምላኬና መዳኛ ዐለቴም ነህ’ ብሎ ይጠራኛል።
27እኔም ደግሞ በኵሬ አደርገዋለሁ፤
ከምድር ነገሥታትም በላይ ከፍ ይላል።
28ምሕረቴንም ለዘላለም ለርሱ እጠብቃለሁ፤
ከርሱ ጋራ የገባሁት ኪዳንም ጸንቶ ይኖራል።
29የዘር ሐረጉን ለዘላለም፣
ዙፋኑንም በሰማያት ዕድሜ ልክ አጸናለሁ።
30“ልጆቹ ሕጌን ቢተዉ፣
ደንቤን ባይጠብቁ፣
31ሥርዐቴን ቢጥሱ፣
ትእዛዜንም ባያከብሩ፣
32ኀጢአታቸውን በበትር፣
በደላቸውን በጅራፍ እቀጣለሁ።
33ምሕረቴን ግን ከርሱ አላርቅም፤
ታማኝነቴንም አላጓድልበትም።
34ኪዳኔን አላፈርስም፤
ከአፌ የወጣውንም አላጥፍም።
35አንድ ጊዜ በቅድስናዬ ምያለሁና፣
ዳዊትን አልዋሸውም።
36የዘር ሐረጉ ለዘላለም፣
ዙፋኑም በፊቴ እንደ ፀሓይ ጸንቶ ይኖራል፤
37በሰማይ ታማኝ ምስክር ሆና እንደምትኖረው፣
እንደ ጨረቃ እርሱ ለዘላለም ይመሠረታል።” ሴላ
38አሁን ግን ናቅኸው፤ ጣልኸውም፤
የቀባኸውንም እጅግ ተቈጣኸው።
39ከባሪያህ ጋራ የገባኸውን ኪዳን አፈረስህ፤
የክብር ዘውዱን ትቢያ ላይ ጥለህ አቃለልኸው።
40ቅጥሩን ሁሉ አፈራረስህ፤
ምሽጉንም ደመሰስህ።
41ዐላፊ አግዳሚው ሁሉ ዘረፈው፤
ለጎረቤቶቹ መዘባበቻ ሆነ።
42የጠላቶቹን ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አደረግህ፤
ባላንጣዎቹም ሁሉ ደስ አላቸው።
43የሰይፉን ስለት አጠፍህ፤
በጦርነትም ጊዜ አልረዳኸውም።
44ግርማዊነቱን አጠፋህበት፤
ዙፋኑንም ከዐፈር ደባለቅኸው።
45የወጣትነት ዘመኑን አሳጠርኸው፤
ዕፍረትንም አከናነብኸው። ሴላ
46 እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ራስህንስ ለዘላለም ትሰውራለህን?
ቍጣህስ እንደ እሳት የሚነድደው እስከ መቼ ነው?
47ዘመኔ ምን ያህል ዐጭር እንደ ሆነች ዐስብ፤
የሰውን ልጆች እንዲያው ለከንቱ ፈጠርሃቸው!
48ሞትን ሳያይ ሕያው ሆኖ የሚቀር ሰው አለን?
ራሱን ከሲኦል እጅ ማዳን የሚችል ማን ነው? ሴላ
49ጌታ ሆይ፤ ለዳዊት በታማኝነትህ የማልህለት፣
የቀድሞው ምሕረትህ የት አለ?
50ጌታ ሆይ፤ ባሪያህ#89፥50 ባሮችህ የሚሉ አሉ። እንዴት እንደ ተፌዘበት፣
የብዙ ሰዎችንም ነቀፋ እንደ ታቀፍሁ ዐስብ።
51 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ የተሣለቁበትን፣
የቀባኸውን ሰው ርምጃ የነቀፉበትን ሁኔታ ዐስብ።
52 እግዚአብሔር ለዘላለም ይባረክ፤
አሜን፤ አሜን።
Currently Selected:
መዝሙር 89: NASV
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
መዝሙር 89
89
መዝሙር 89
የይዝራኤላዊው የኤታን ማስኪል።#89፥0 የሥነ ጽሑፉን ቅርጽ የሚያሳይ ወይም በሙዚቃ ውስጥ የሚጠቀሙበት ቃል ሳይሆን አይቀርም።
1ስለ እግዚአብሔር ምሕረት ለዘላለም እዘምራለሁ፤
በአፌም ታማኝነትህን ከትውልድ እስከ ትውልድ እገልጻለሁ።
2ምሕረትህን ለዘላለም እንደምትመሠርት፣
ታማኝነትህንም በሰማይ እንደምታጸና እናገራለሁ።
3አንተም እንዲህ ብለሃል፤ “ከመረጥሁት ጋራ ኪዳን ገብቻለሁ፤
ለባሪያዬ ለዳዊት ምያለሁ፤
4‘ዘርህን ለዘላለም እተክላለሁ፤
ዙፋንህንም ከትውልድ እስከ ትውልድ አጸናለሁ።’ ” ሴላ
5 እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያት ድንቅ ሥራህን፣
ታማኝነትህንም በቅዱሳን ጉባኤ መካከል ያወድሳሉ፤
6በላይ በሰማያት ከእግዚአብሔር ጋራ ማን ሊስተካከል ይችላል?
ከሰማያውያን ፍጥረታትስ መካከል ማን እግዚአብሔርን ይመስለዋል?
7እግዚአብሔር በቅዱሳን ጉባኤ መካከል በጣም የሚፈራ፣
በዙሪያውም ካሉት ሁሉ በላይ እጅግ የሚከበር ነው።
8የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ኀያል ነህ፤ ታማኝነትህም ከብቦሃል።
9የባሕርን ቍጣ ትቈጣጠራለህ፤
ሞገዱም ሲነሣ ጸጥ ታደርገዋለህ።
10አንተ ረዓብን የተሰየፈ ያህል አደቀቅኸው፤
በብርቱ ክንድህም ጠላቶችህን በተንሃቸው።
11ሰማያት የአንተ ናቸው፤ ምድርም የአንተ ናት፤
ዓለምንና በውስጧ ያለውን ሁሉ አንተ መሠረትህ።
12ሰሜንንና ደቡብን የፈጠርህ አንተ ነህ፤
ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ሐሤት ያደርጋሉ።
13አንተ ክንደ ብርቱ ነህ፤
እጅህ ኀያል ናት፤ ቀኝ እጅህም ከፍ ከፍ ያለች ናት።
14ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረቶች ናቸው፤
ምሕረትና ታማኝነት በፊትህ ይሄዳሉ።
15ብፁዕ ነው፤
እግዚአብሔር ሆይ፤ እልልታን የሚያውቅ፣
በፊትህም ብርሃን የሚሄድ ሕዝብ፤
16ቀኑን ሙሉ በስምህ ደስ ይላቸዋል፤
በጽድቅህም ሐሤት ያደርጋሉ፤
17አንተ የብርታታቸው ክብር ነህና፤
በሞገስህም ቀንዳችንን#89፥17 የጥንካሬ ምልክት ነው። ከፍ ከፍ አደረግህ።
18ጋሻችን#89፥18 ወይም ልዑል ማለት ነው። የእግዚአብሔር ነውና፤
ንጉሣችንም የራሱ የእስራኤል ቅዱስ ነው።
19በዚያ ጊዜ በራእይ ተናገርህ፤
ታማኝ ሕዝብህንም እንዲህ አልህ፤
“ኀያሉን ሰው ሥልጣን አጐናጸፍሁት፤
ከሕዝብ መካከል የተመረጠውንም ከፍ ከፍ አደረግሁት።
20ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁ፤
በተቀደሰው ዘይቴም ቀባሁት።
21እጄ ይደግፈዋል፤
ክንዴም ያበረታዋል።
22በጠላት አይበለጥም፤
ክፉ ሰውም አይበግረውም።
23ባላንጣዎቹን በፊቱ አደቅቃቸዋለሁ፤
ጠላቶቹንም እቀጠቅጣለሁ።
24ታማኝነቴና ምሕረቴ ከርሱ ጋራ ይሆናል፤
በስሜም ቀንዱ ከፍ ከፍ ይላል።
25እጁን በባሕር ላይ፣
ቀኝ እጁንም በወንዞች ላይ አኖራለሁ።
26እርሱም፣ ‘አንተ አባቴ ነህ፤
አምላኬና መዳኛ ዐለቴም ነህ’ ብሎ ይጠራኛል።
27እኔም ደግሞ በኵሬ አደርገዋለሁ፤
ከምድር ነገሥታትም በላይ ከፍ ይላል።
28ምሕረቴንም ለዘላለም ለርሱ እጠብቃለሁ፤
ከርሱ ጋራ የገባሁት ኪዳንም ጸንቶ ይኖራል።
29የዘር ሐረጉን ለዘላለም፣
ዙፋኑንም በሰማያት ዕድሜ ልክ አጸናለሁ።
30“ልጆቹ ሕጌን ቢተዉ፣
ደንቤን ባይጠብቁ፣
31ሥርዐቴን ቢጥሱ፣
ትእዛዜንም ባያከብሩ፣
32ኀጢአታቸውን በበትር፣
በደላቸውን በጅራፍ እቀጣለሁ።
33ምሕረቴን ግን ከርሱ አላርቅም፤
ታማኝነቴንም አላጓድልበትም።
34ኪዳኔን አላፈርስም፤
ከአፌ የወጣውንም አላጥፍም።
35አንድ ጊዜ በቅድስናዬ ምያለሁና፣
ዳዊትን አልዋሸውም።
36የዘር ሐረጉ ለዘላለም፣
ዙፋኑም በፊቴ እንደ ፀሓይ ጸንቶ ይኖራል፤
37በሰማይ ታማኝ ምስክር ሆና እንደምትኖረው፣
እንደ ጨረቃ እርሱ ለዘላለም ይመሠረታል።” ሴላ
38አሁን ግን ናቅኸው፤ ጣልኸውም፤
የቀባኸውንም እጅግ ተቈጣኸው።
39ከባሪያህ ጋራ የገባኸውን ኪዳን አፈረስህ፤
የክብር ዘውዱን ትቢያ ላይ ጥለህ አቃለልኸው።
40ቅጥሩን ሁሉ አፈራረስህ፤
ምሽጉንም ደመሰስህ።
41ዐላፊ አግዳሚው ሁሉ ዘረፈው፤
ለጎረቤቶቹ መዘባበቻ ሆነ።
42የጠላቶቹን ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አደረግህ፤
ባላንጣዎቹም ሁሉ ደስ አላቸው።
43የሰይፉን ስለት አጠፍህ፤
በጦርነትም ጊዜ አልረዳኸውም።
44ግርማዊነቱን አጠፋህበት፤
ዙፋኑንም ከዐፈር ደባለቅኸው።
45የወጣትነት ዘመኑን አሳጠርኸው፤
ዕፍረትንም አከናነብኸው። ሴላ
46 እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ እስከ መቼ ይሆናል? ራስህንስ ለዘላለም ትሰውራለህን?
ቍጣህስ እንደ እሳት የሚነድደው እስከ መቼ ነው?
47ዘመኔ ምን ያህል ዐጭር እንደ ሆነች ዐስብ፤
የሰውን ልጆች እንዲያው ለከንቱ ፈጠርሃቸው!
48ሞትን ሳያይ ሕያው ሆኖ የሚቀር ሰው አለን?
ራሱን ከሲኦል እጅ ማዳን የሚችል ማን ነው? ሴላ
49ጌታ ሆይ፤ ለዳዊት በታማኝነትህ የማልህለት፣
የቀድሞው ምሕረትህ የት አለ?
50ጌታ ሆይ፤ ባሪያህ#89፥50 ባሮችህ የሚሉ አሉ። እንዴት እንደ ተፌዘበት፣
የብዙ ሰዎችንም ነቀፋ እንደ ታቀፍሁ ዐስብ።
51 እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ የተሣለቁበትን፣
የቀባኸውን ሰው ርምጃ የነቀፉበትን ሁኔታ ዐስብ።
52 እግዚአብሔር ለዘላለም ይባረክ፤
አሜን፤ አሜን።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.