1 የጴጥሮስ መልእክት መግቢያ
መግቢያ
መጀመሪያው የሐዋርያው የጴጥሮስ መልእክት የተጻፈው በመልእክቱ ውስጥ “የእግዚአብሔር ምርጥ ሕዝብ” በመባል ለሚጠሩትና በታናሽቱ እስያ ሰሜናዊ ክፍል ለተበተኑት ክርስቲያኖች ነው፤ የመልእክቱ ዋና ዓላማ በእምነታቸው ምክንያት ስደትና መከራ ደርሶባቸው የነበሩትን አንባቢዎች ለማበረታታትና ለማጽናናት ነው፤ ጸሐፊው ይህን የሚያደርገው የሞቱን፥ የትንሣኤውን፥ ተመልሶ የመምጣቱን ተስፋ የሚያበሥረውን የኢየሱስ ክርስቶስን የምሥራች ቃል ለአንባቢዎቹ በማስታወስ ነው፤ የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወት በምሳሌነት በመመልከት መከራን በትዕግሥት መቀበል እንዳለባቸው ያሳስባቸዋል፤ ከዚህም ጋር በማያያዝ መከራ የእምነታቸውን ጥራት እንደሚፈትንና “ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ቀን” ተገቢ ዋጋቸውን እንደሚቀበሉ ያስገነዝባቸዋል።
ጸሐፊው በመከራ እንዲታገሡ ከማደፋፈሩም ሌላ አንባቢዎቹ የክርስቶስ ተከታዮች መኖር እንደሚገባቸው ዐይነት እንዲኖሩ ያሳስባቸዋል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1፥1-2
የእግዚአብሔር አዳኝነት ማስታወሻ 1፥3-12
የተቀደሰ ሕይወትን ለመኖር የተሰጠ ምክር 1፥13—2፥10
በችግር ጊዜ የክርስቲያን ኀላፊነት 2፥11—4፥19
የክርስቲያን ትሕትናና አገልግሎት 5፥1-11
ማጠቃለያ 5፥12-14
Currently Selected:
1 የጴጥሮስ መልእክት መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997