አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 14
14
ዮናታን በፍልስጥኤማውያን ላይ በቈራጥነት የጣለው አደጋ
1አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን የጦር መሣሪያ የሚሸከምለትን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን “ወደ ፍልስጥኤማውያን የጦር ሰፈር እንሻገር” አለው። ነገር ግን ዮናታን ይህን ጉዳይ ለአባቱ እንኳ አልነገረውም፤ 2በዚህ ጊዜ ሳኦል ከጊብዓ በጣም ሳይርቅ በሚግሮን በአንድ የሮማን ዛፍ ሥር ሰፍሮ ነበር፤ ከእርሱም ጋር ስድስት መቶ ያኽል ጭፍሮች ነበሩ፤ 3በሴሎ የእግዚአብሔር ካህን የነበረው የዔሊ ልጅ ካህኑ ፊንሐስ የወለደው የኢካቦድ ወንድም የአሒጡብ ልጅ አኪያ ኤፉድ ለብሶ ከእርሱ ጋር አብሮ ነበር። እነርሱም ዮናታን ወዴት እንደ ሄደ አላወቁም ነበር።
4ዮናታን ወደ ፍልስጥኤማውያን ሰፈር ለመድረስ በሚክማስ መተላለፊያ መውጣት ነበረበት፤ በመተላለፊያውም ከግራና ከቀኝ ሁለት ሾጣጣ አለቶች ሲኖሩ የአንደኛው አለት ስም ቦጼጽ፥ የሁለተኛውም ስም ሴኔ ተብሎ ይጠራል፤ 5ከአለቶቹም አንዱ ከመተላለፊያው በስተ ሰሜን በኩል በሚክማስ ፊት ለፊት የሚገኘው ሲሆን፥ ሁለተኛውም በስተደቡብ በኩል በጌባዕ ፊት ለፊት ይገኝ ነበር።
6ዮናታን ጋሻ ጃግሬ የሆነውን ወጣት “ና ወደ እነዚያ ወደ አልተገረዙት ወገኖች የጦር ሰፈር እንሻገር እግዚአብሔር ይረዳን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት እግዚአብሔር ማዳን አይሳነውም” አለው።
7ወጣቱም ጋሻጃግሬ “የምትፈቅደውን ነገር ሁሉ አድርግ፤ እኔ ከአንተ አልለይም፤ በሙሉ ልቤም ከአንተ ጋር ነኝ” አለው።
8ዮናታንም እንዲህ አለው፤ “እሺ እንግዲያውስ ወደ ማዶ እንሻገርና ለፍልስጥኤማውያን ፊት ለፊት እንታያቸው፤ 9እነርሱም ‘ወደ እናንተ እስክንመጣ ድረስ በዚያ ጠብቁን’ ቢሉን፥ ባለንበት እንቈያለን፤ 10ነገር ግን ‘ወደ እኛ ኑ’ ቢሉን፥ ወደ እነርሱ እንሄዳለን፤ ይህም እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን የሚያቀዳጀን ለመሆኑ ምልክት ይሆንልናል።”
11እነርሱም ወጣ ብለው ለፍልስጥኤማውያን ታዩአቸው፤ ፍልስጥኤማውያንም “እነሆ! አንዳንድ ዕብራውያን ከተሸሸጉበት ጒድጓድ በመውጣት ላይ ናቸው!” ተባባሉ፤ 12ከዚህ በኋላ ፍልስጥኤማውያን ዮናታንንና ጋሻጃግሬውን ጠርተው “የምንነግራችሁ ጉዳይ ስላለን ወደዚህ እኛ ወዳለንበት ኑ!” አሉአቸው። ዮናታንም ጋሻጃግሬውን “እንግዲህ ተከተለኝ፤ እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን ለእስራኤል ይሰጣል” አለው፤ 13ዮናታንም በእጁና በጒልበቱ እየዳኸ ወደ አፋፉ ወጣ፤ ጋሻጃግሬውም ተከተለው፤ ዮናታንም በፍልስጥኤማውያን ላይ ድንገተኛ አደጋ በመጣል መታቸው፤ ጋሻጃግሬውም ገደላቸው። 14በመጀመሪያውም ግድያ በአንድ የእርሻ ክልል ላይ ኻያ ያኽል ሰዎችን ገደሉ፤ 15በገጠር የነበሩ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ተሸበሩ፤ አደጋ ጣዮችና በሰፈር የነበሩ ወታደሮችም ሁሉ በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ እግዚአብሔር በላከባቸውም አስጨናቂ ሽብር መሬት ተንቀጠቀጠች።
የፍልስጥኤማውያን መሸነፍ
16የሳኦል ወታደሮች የብንያም ግዛት በሆነችው በጊብዓ መሽገው ሁኔታውን ሁሉ በመጠባበቅ ላይ ሳሉ በመታወክ የሚሸሹትን ፍልስጥኤማውያን አዩ። 17ስለዚህም ሳኦል “እስቲ ወታደሮችን ቊጠሩና ከእኛ መካከል የጐደሉ እንዳሉ አረጋግጡ” ብሎ አዘዘ፤ በትእዛዙም መሠረት ሠራዊቱን በቈጠሩ ጊዜ ዮናታንና ጋሻጃግሬው አለመኖራቸው ታወቀ። 18ሳኦልም ካህኑን አኪያን “ኤፉዱን ይዘህ ና” አለው። በዚያን ቀን ካህኑ አኪያ ኤፉድ ለብሶ በእስራኤል ሕዝብ ፊት ነበር፤ 19ሳኦል ከካህኑ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ፥ በፍልስጥኤማውያን ሰፈር የተነሣው ሁከትና ሽብር እየባሰበት ሄደ፤ ሳኦልም ካህኑን “እግዚአብሔርን ለመጠየቅ አሁን ጊዜ የለንም” አለው። 20ከዚህ በኋላ ሳኦልና ወታደሮቹ ካሉበት በመንቀሳቀስ ወደ ውጊያው ሄዱ፦ እዚያም ፍልስጥኤማውያን ግራ በመጋባት እርስ በርሳቸው በሰይፍ ይጋደሉ ነበር። 21ከፍልስጥኤማውያን ጋር በመተባበር ወደ ጦሩ ሰፈር ሄደው የነበሩ አንዳንድ ዕብራውያንም ፍልስጥኤማውያንን ከድተው ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ተባበሩ። 22በኤፍሬም ኮረብታዎች ተደብቀው የነበሩ ሌሎች እስራኤላውያንም ፍልስጥኤማውያን በሽሽት ላይ መሆናቸውን ሰሙ፤ ስለዚህም ከወገን ጦር ጋር ተባብረው ፍልስጥኤማውያንን ማሳደድ ጀመሩ፤ 23እስከ ቤትአዌን ከተማ ማዶ ባለው መንገድ ሁሉ ተከታትለው ወጉአቸው፤ እግዚአብሔርም በዚያን ቀን እስራኤልን በመታደግ አዳነ።
ከጦርነቱ በኋላ የተፈጸሙ ድርጊቶች
24በዚያን ቀን እስራኤላውያን በራብ ደከሙ፤ ምክንያቱም ሳኦል “ጠላቶቼን እስክበቀል ድረስ ዛሬ እህል ውሃ የሚቀምስ ማናቸውም ሰው የተረገመ ይሁን!” ብሎ ሕዝቡን በማስማል ማንም ሰው እህል ውሃ እንዳይቀምስ ትእዛዝ ሰጥቶ ነበር። ከዚህም የተነሣ ሁሉም ምንም ነገር ሳይቀምሱ ቀኑን ሙሉ ዋሉ። 25ጫካ ወደበዛበትም ቦታ በመጡም ጊዜ በየስፍራው ማር. አግኝተው ነበር፤ 26ዛፉ ሁሉ ማር. የሞላበት ቢሆንም የሳኦልን ርግማን በመፍራት ከማሩ የቀመሰ ማንም አልነበረም፤ 27ዮናታን ግን አባቱ ሕዝቡን ማስማሉን ስላልሰማ፥ የያዘውን በትር በመዘርጋት ወለላውን እየሳበ ጥቂት ማር. በላ፤ ወዲያውኑ ብርታት አግኝቶ ዐይኑ በራ፤ 28ነገር ግን ከወታደሮቹ አንዱ “እኛ ሁላችን በራብ ደክመን ዝለናል፤ አባትህ ግን ‘በዛሬው ዕለት ምንም ዐይነት ምግብ የሚመገብ ሰው የተረገመ ይሁን’ ሲል በብርቱ አስጠንቅቆናል” አለው። 29ዮናታንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አባቴ በሕዝባችን ላይ የፈጠረው ችግር ምን ያኽል ከባድ ነው! ትንሽ ማር. አግኝቼ በመብላት ብርታት አግኝቼ ዐይኔ እንደ በራ ተመልከት! 30ታዲያ ዛሬ ሕዝባችን ጠላትን ድል መትቶ ከምርኮ የሚያገኘውን ምግብ ቢመገብ ኖሮ እንዴት በተሻለው ነበር? የሚገድሉአቸው ፍልስጥኤማውያን ቊጥር ምን ያኽል ይበዛ እንደ ነበር እስቲ ገምት።”
31በዚያን ቀን እስራኤላውያን ከሚክማስ እስከ አያሎን ባለው መንገድ ሁሉ እያሳደዱ በመውጋት ፍልስጥኤማውያንን ድል መቱ፤ በዚህም ጊዜ እስራኤላውያንም በራብ እጅግ ዝለው ነበር። 32ስለዚህም ከጠላት ባገኙት ምርኮ ላይ እየተረባረቡ በጎችን፥ የቀንድ ከብቶችንና ጥጆችን ባገኙበት ቦታ እያረዱ ሥጋውን ከነደሙ መብላት ጀመሩ፤ 33ለሳኦልም “ተመልከት ሕዝቡ ደም ያለበትን ሥጋ በመብላታቸው በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት ሠርተዋል” የሚል ወሬ ደረሰው። #ዘፍ. 9፥4፤ ዘሌ. 7፥26-27፤ 17፥10-14፤ 19፥26፤ ዘዳ. 12፥16፤ 23፤ 15፥23።
ሳኦልም “ይህ የክሕደት ተግባር ነው! አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባላችሁ ወደዚህ አምጡልኝ” ሲል ጮኸባቸው። 34ከዚህም በኋላ ሌላ ትእዛዝ እንዲህ ሲል አስተላለፈ፤ “ወደ ሕዝቡ ሄዳችሁ ‘የቀንድ ከብቶቻችሁንና በጎቻችሁን ሁሉ አምጡ፤ እነርሱንም ዐርዳችሁ በዚህ ስፍራ መመገብ አለባችሁ፤ ደም ያለበትንም እርጥብ ሥጋ በመብላት በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአት አትሥሩ’ ብላችሁ ንገሩአቸው።” ስለዚህም ሕዝቡ ሁሉ በዚያን ሌሊት የቀንድ ከብቶቻቸውንና በጎቻቸውን ሁሉ አምጥተው በዚያ ዐረዱ፤ 35ሳኦልም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ ይህም እርሱ የሠራው መሠዊያ የመጀመሪያው ነበር።
36ሳኦልም ወታደሮቹን “እንግዲህ እንውረድና በፍልስጥኤማውያን ላይ በሌሊት አደጋ እንጣልባቸው፤ እስኪነጋም ድረስ ሀብታቸውን ዘርፈን ሁሉንም እንፍጃቸው” አለ። እነርሱም “መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ” አሉት። ካህኑ ግን “በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንጠይቅ” አለ።
37ሳኦልም “በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ እንጣልባቸውን? ድልንስ ለእኛ ትሰጣለህን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በዚያን ቀን ምንም መልስ አልሰጠም። 38ከዚህ በኋላ ሳኦል ለሕዝቡ መሪዎች እንዲህ አለ፤ “ወደዚህ ቀርባችሁ ዛሬ ምን ዐይነት ኃጢአት እንደ ተሠራ መርምራችሁ ዕወቁ፤ 39በደል ሠርቶ የተገኘው ሰው ልጄ ዮናታን እንኳ ቢሆን በሞት እንደሚቀጣ ለእስራኤል ድልን በሰጠው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ።” ነገር ግን አንዳች መልስ የሰጠው ሰው አልተገኘም። 40ከዚያም በኋላ ሳኦል “እናንተ ሁላችሁም በዚያ በኩል ቁሙ፤ እኔና ልጄ ዮናታን ደግሞ በዚህ በኩል እንቆማለን” አላቸው።
እነርሱም “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” አሉት።
41ሳኦልም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “እግዚአብሔር ሆይ! ዛሬ ስለምን መልስ አልሰጠኸኝም? የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! በእነዚህ በተቀደሱ ድንጋዮች አማካይነት መልስ ስጠኝ፤ ይህን በደል የሠራነው ዮናታን ወይም እኔ ከሆንን በኡሪም አማካይነት፥ ይህን በደል የፈጸሙ ሕዝብህ እስራኤል ከሆኑ በቱሚም አማካይነት መልስ ስጠኝ።” መልሱም ዮናታንንና ሳኦልን ስላመለከተ ሕዝቡ ነጻ ሆኑ፤ #ዘኍ. 27፥21፤ 1ሳሙ. 28፥6። 42ከዚህም በኋላ ሳኦል “በእኔና በልጄ በዮናታን መካከል ዕጣ ጣሉ” አለ፤ ዕጣውም በዮናታን ላይ መጣ፤ 43ከዚህም በኋላ ሳኦል ዮናታንን “ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ። ዮናታንም “በበትሬ ጫፍ አስነክቼ ጥቂት ማር. ቀምሻለሁ እነሆ በዚህ እገኛለሁ፤ ለመሞትም ዝግጁ ነኝ” አለ።
44ሳኦልም “እግዚአብሔር ይፍረድብኝ፤ አንተ ከሞት ቅጣት አታመልጥም!” አለው።
45ሕዝቡ ግን ሳኦልን “ይህን ታላቅ ድል ለእስራኤል ያስገኘ ዮናታን ይሞታልን? ከቶ አይደረግም! መሞቱ ይቅርና ከራስ ጠጒሩ አንዲቱ እንደማትወድቅ በሕያው እግዚአብሔር ስም እንምላለን፤ ዛሬ እርሱ ያደረገው ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ረዳትነት የተፈጸመ ነው” አሉ፤ በዚህም ዐይነት ሕዝቡ ዮናታንን ከሞት ቅጣት አዳኑት።
46ከዚያም በኋላ ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ተገታ፤ እነርሱም ተመልሰው ወደ አገራቸው ሄዱ።
የሳኦል ዘመነ መንግሥትና የቤተሰቡ ሁኔታ
47ሳኦል በእስራኤል ከነገሠ በኋላ፥ በሁሉም ስፍራ የሚገኙ ጠላቶቹን ወጋ፤ እነርሱም የሞአብ፥ የዐሞንና የኤዶም ሕዝቦች፥ የጾባ ነገሥታትና ፍልስጥኤማውያን ናቸው፤ በተዋጋበት ስፍራ ሁሉ ድል አድራጊ ሆነ፤ 48በጀግንነትም ተዋግቶ የዐማሌቅን ሕዝብ እንኳ ሳይቀር ድል መታ፤ እርሱም እስራኤላውያንን ከጠላቶቻቸው እጅ አዳነ።
49የሳኦልም ወንዶች ልጆች ዮናታን፥ ይሽዊና ማልኪሹዓ ተብለው ይጠሩ ነበር፤ ታላቋ ሴት ልጁም ሜራብ ስትሆን፥ ታናሽዋ ሜልኮል ትባል ነበር፤ 50ሚስቱም አሒኖዓም ተብላ የምትጠራ የአሒማዓጽ ልጅ ነበረች፤ የሠራዊቱም አዛዥ አበኔር ተብሎ የሚጠራው የአጐቱ የኔር ልጅ ነበር። 51ስለዚህም የሳኦል አባት ቂስና የአበኔር አባት ኔር የአቢኤል ልጆች ነበሩ።
52ሳኦል በነበረበት ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በብርቱ ጠላትነት ሲዋጋ ኖረ፤ ስለዚህም ብርቱ ወይም ጀግና የሆነ ሰው ሲያገኝ እየመለመለ በጦር ሠራዊቱ ውስጥ ያስመዘግበው ነበር።
Currently Selected:
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 14: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997