አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 22
22
ዳዊት በዓላምና በምጽጳ
1ዳዊት ከጋት ከተማ ሸሽቶ በዐዱላም ከተማ አጠገብ ወደሚገኝው ወደ አንድ ዋሻ ሄደ፤ ወንድሞቹና ሌሎቹም ቤተሰቦቹ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደዚያ ሄደው ከእርሱ ጋር ተቀላቀሉ፤ #መዝ. 57፤ መዝ. 142። 2የተጨነቁ፥ ዕዳ ያለባቸው፥ እንዲሁም ሆድ የባሳቸው አንዳንድ ሰዎች ወደ እርሱ ስለ ሄዱ ብዛታቸው በድምሩ እስከ አራት መቶ ደረሰ፤ ዳዊትም የእነርሱ መሪ ሆነ።
3ዳዊትም ከዚያ ተነሥቶ በሞአብ ወደምትገኘው ወደ ምጽጳ ሄደ፤ የሞአብንም ንጉሥ “እግዚአብሔር ለእኔ የሚያደርግልኝን ነገር እስካውቅ ድረስ እባክህ አባቴና እናቴ መጥተው በአንተ ዘንድ እንዲቈዩ ፍቀድላቸው” ሲል ጠየቀው። 4በዚህም ዐይነት ወላጆቹን በሞአብ ንጉሥ ዘንድ ተዋቸው፤ እነርሱም ዳዊት እየተደበቀ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ በዚያው ቈዩ።
5ከዚህ በኋላ ነቢዩ ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ “በዚህ አትቈይ፤ አሁኑኑ ፈጥነህ ወደ ይሁዳ ሂድ” ሲል ነገረው፤ ስለዚህም ዳዊት ከዚያ ተነሥቶ ወደ ሔሬት ጫካ ገባ።
የካህናት መገደል
6ከዕለታት አንድ ቀን ሳኦል ጦሩን በእጁ እንደ ያዘ በጊብዓ በሚገኝ ኮረብታ ላይ ታማሪስክ ተብሎ በሚጠራ ዛፍ ሥር ተቀምጦ ነበር፤ ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም በዙሪያው ቆመው ነበር፤ በዚህን ጊዜ ዳዊትና ተከታዮቹ በአንድ ስፍራ መኖራቸው ለሳኦል ተነገረው፤ 7ሳኦልም ባለሟሎችን እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የብንያም ሰዎች አድምጡኝ! በውኑ የእሴይ ልጅ ዳዊት ለሁላችሁም ለእያንዳንዳችሁ የእርሻ መሬትና የወይን ተክል ቦታ የሚሰጣችሁና በሠራዊቱም ውስጥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች አድርጎ የሚሾማችሁ ይመስላችኋልን? 8በእኔስ ላይ ሤራ የምታካሄዱት ስለዚህ ነውን? የገዛ ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር መተባበሩን የነገረኝ ከእናንተ አንድ እንኳ የለም፤ ስለ እኔ የሚያስብ ከቶ ማንም የለም፤ ወይም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ አገልጋዬ በእኔ ላይ እንዲሸምቅ ልጄ ያነሣሣው መሆኑን ከእናንተ ማንም የነገረኝ የለም።”
9በዚህን ጊዜ ከባለሥልጣኖቹ ጋር ኤዶማዊው ዶይቅ እዚያ ቆሞ ስለ ነበር “እኔ የእሴይን ልጅ በኖብ ወደሚገኘው የአሒጡብ ልጅ ወደ ሆነው ወደ አቤሜሌክ በመጣ ጊዜ አይቼዋለሁ፤ 10ዳዊትም ምን ማድረግ እንደሚገባው አቤሜሌክ እግዚአብሔርን ጠይቆለታል፤ ከዚያም በኋላ ለዳዊት ጥቂት ምግብና የፍልስጥኤማዊውን የጎልያድን ሰይፍ ሰጥቶታል” ሲል ተናገረ። #1ሳሙ. 21፥7-9፤ መዝ. 52።
11ስለዚህም ንጉሥ ሳኦል ወደ ካህኑ የአሒጡብ ልጅ ወደ ሆነው ወደ አቤሜሌክና በኖብ ወደሚገኙት ዘመዶቹ ወደሆኑት ካህናት ሁሉ መልእክት ላከ፤ እነርሱም መጡ፤ 12ሳኦልም፥ “የአሒጡብ ልጅ ሆይ! እንግዲህ ስማ” አለው።
አቤሜሌክም “እነሆኝ ጌታ ሆይ!” ብሎ መለሰ።
13ሳኦልም “አንተና የእሴይ ልጅ በእኔ ላይ ያሤራችሁት ስለምንድን ነው? ለእርሱ ምግብና ሰይፍ ሰጥተኸዋል እግዚአብሔርንም ጠይቀህለታል፤ እነሆ፥ እርሱ አሁን በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሥቶ እኔን ለመግደል አጋጣሚ ጊዜ በመፈለግ ላይ ነው” ሲል ጠየቀው።
14አቤሜሌክም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ዳዊት ለአንተ የታመነ የጦር መኰንን ነው፤ የአንተው የራስህ ዐማች ከመሆኑም ሌላ የክብር ዘብህ አዛዥ ነው፤ በቤተ መንግሥትህም አደባባይ እንደ እርሱ የሚከበር ማን አለ? 15በውኑ እግዚአብሔርን ስለ እርሱ መጠየቅ ይህ ዛሬ የመጀመሪያ ጊዜዬ ነውን? አይደለም! ንጉሥ ሆይ! እኔን አገልጋይህንም ሆነ ቤተሰቤን በዚህ ጉዳይ ላይ አትውቀስ፤ ስለዚህ ጉዳይ ይብዛም ይነስም እኔ የማውቀው ነገር የለም።”
16ንጉሡም “አቤሜሌክ ሆይ! አንተና መላው ዘመዶችህ ሞት ይገባችኋል!” አለው። 17ከዚህም በኋላ ሳኦል በአጠገቡ ወደቆሙት ዘብ ጠባቂዎች መለስ ብሎ “እነዚህን የእግዚአብሔርን ካህናት ግደሉ! እነርሱ ከዳዊት ጋር በእኔ ላይ ዐምፀውብኛል፤ እንዲሁም ሁሉን ነገር እያወቁ ዳዊት መኰብለሉን እንኳ አልነገሩኝም” አላቸው፤ ዘብ ጠባቂዎቹ ግን “የእግዚአብሔርን ካህናት አንገድልም” አሉ። 18ስለዚህም ሳኦል ዶይቅን “አንተው ግደላቸው!” አለው፤ ኤዶማዊው ዶይቅም ተነሥቶ ሁሉንም ገደለ፤ በዚያኑ ቀን የፈጃቸው ኤፉድ የሚለብሱ ካህናት ብዛት ሰማኒያ አምስት ነበር፤ 19ከዚህም በኋላ ሳኦል የካህናት ከተማ በሆነችው በኖብ የሚኖሩት ሁሉ ወንዶችና ሴቶች፥ ልጆችና ሕፃናት፥ የቀንድ ከብቶችና አህዮች፥ እንዲሁም የበግ መንጋዎች ሁሉ እንዲገደሉ አደረገ።
20ነገር ግን አብያታር የሚባል ከአቤሜሌክ ወንዶች ልጆች አንዱ ብቻ አምልጦ በመሄድ ከዳዊት ጋር ተቀላቀለ፤ 21ሳኦል የእግዚአብሔርን ካህናት እንዴት እንደ ፈጀም ለዳዊት ነገረው፤ 22ዳዊትም አብያታርን “እኔ በዚያ ቀን ኤዶማዊውን ዶይቅን እዚያ ባየሁት ጊዜ ሁሉን ነገር ለሳኦል እንደሚነግረው ዐውቄ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ስለ ዘመዶችህ ሁሉ እልቂት እኔ ተጠያቂነት አለብኝ፤ 23አንተ ግን ከእኔ ጋር ኑር፤ አይዞህ አትፍራ፤ በእርግጥ ሳኦል አንተንም እኔንም ለመግደል ይፈልጋል፤ ነገር ግን አንተ ከእኔ ጋር በሰላም ትኖራለህ” አለው።
Currently Selected:
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 22: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997