አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 24
24
ዳዊት የሳኦልን ሕይወት ማትረፉ
1ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ወግቶ ከተመለሰ በኋላ ዳዊት በዔንገዲ አጠገብ በሚገኘው ምድረ በዳ የሚገኝ መሆኑን ሰማ፤ 2ስለዚህም ሳኦል በእስራኤል ምርጥ የሆኑትን ሦስት ሺህ ወታደሮች በማስከተል “የሜዳ ፍየሎች አለት” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በስተ ምሥራቅ በኩል ዳዊትን አሳዶ ለመያዝ ሄደ፤ 3በመንገድ ዳር ባሉት የበጎች ማደሪያዎች አቅራቢያ ወደሚገኘው ወደ አንድ ዋሻ ወገቡን ሊሞክር ወደ ውስጥ ገባ፤ በዚያም እርሱ ከተቀመጠበት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ዳዊትና ተከታዮቹ ተደብቀው የሚኖሩበት ክፍል ነበር፤ #መዝ. 57፤ መዝ. 142። 4ተከታዮቹም ዳዊትን “እነሆ፥ ጥሩ አጋጣሚ ሆኖልሃል! እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ እንደሚጥልልህ ነግሮሃል፤ እነሆ፥ አሁን በጠላትህ ላይ የፈለግኸውን ማድረግ ትችላለህ!” አሉት፤ ዳዊትም በልቡ እየተሳበ በመቅረብ ሳኦል ሳያውቅ ከልብሱ ጫፍ ላይ ቈርጦ ወሰደ፤ 5ነገር ግን ዳዊትን የኅሊና ወቀሳ አስጨነቀው፤ 6ስለዚህም ተከታዮቹን “እግዚአብሔር ቀብቶ ባነገሠው በጌታዬ ላይ እጄን ከማንሣት እግዚአብሔር ይጠብቀኝ! እርሱ እግዚአብሔር የመረጠው ንጉሥ ስለ ሆነ እኔ በእርሱ ላይ ምንም ዐይነት ጒዳት ላደርስበት አይገባኝም!” አላቸው። #1ሳሙ. 26፥11። 7በዚህም አባባሉ በሳኦል ላይ አደጋ እንዳይጥሉበት ዳዊት ተከታዮቹን ከለከላቸው።
ሳኦልም ከዚያ በመነሣት ከዋሻው ወጥቶ ሄደ፤ 8ዳዊትም ከዚያ ወጥቶ ሳኦልን በመከተል “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” አለው፤ ሳኦልም መለስ ብሎ ዙሪያውን ሲመለከት ዳዊት በመሬት ላይ ለጥ ብሎ እጅ ነሣውና እንዲህ አለው፤ 9“እኔ አንተን ጒዳት እንደማደርስብህ አስመስለው የሚነግሩህን ሰዎች ቃል ስለምን ትሰማለህ? 10ዛሬ በዚህ ሰዓት በዋሻው ውስጥ ሳለህ እግዚአብሔር በእጄ ጥሎህ እንደ ነበር አንተ ራስህ ማየት ትችላለህ፤ አንዳንድ ሰዎችም እንድገድልህ መክረውኝ ነበር፤ ነገር ግን አንተ ‘እግዚአብሔር የቀባህ ንጉሥ ነህና እኔ በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም’ ብዬ ራራሁልህ፤ 11አባቴ ሆይ! እነሆ፥ ከካባህ ላይ ቈርጬ የያዝኩትን ጨርቅ ተመልከት! ታዲያ እኮ ልገድልህ እችል ነበር፤ ነገር ግን ይህን በማድረግ ፈንታ የልብስህን ጫፍ ቈረጥሁ፤ በአንተ ላይ ለማመፅም ሆነ ወይም በአንተ ላይ ጒዳት ላደርስብህ አለመፈለጌን በዚህ መረዳት ትችላለህ፤ አንተ ግን ምንም ነገር ሳላደርግና ሳልበድልህ እኔን ለመግደል ትከታተለኛለህ። 12እንግዲህ ስሕተተኛው ማንኛችን እንደ ሆንን በመለየት እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጥ! እኔ በአንተ ላይ ምንም ዐይነት ጒዳት ላደርስብህ ስለማልፈልግ በእኔ ላይ ስለምታደርገው ክፉ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ራሱ ይበቀል። 13‘ክፉ ነገርን የሚያደርጉ ክፉ ሰዎች ብቻ ናቸው’ የተባለውን ጥንታዊ አነጋገር ታውቃለህ፤ ስለዚህም እኔ በአንተ ላይ ጒዳት ላደርስብህ አልፈልግም። 14እነሆ፥ የእስራኤል ንጉሥ ማንን ለመግደል እንደሚጥር ተመልከት! ማንንም እንደሚያሳድድ አስተውል! የሞተ ውሻን ወይስ ቁንጫን? ማንን እንደሚያሳድድ ተመልከት! #1ሳሙ. 26፥20። 15እግዚአብሔር ይፍረድ፤ ከሁለታችንም ስሕተተኛው ማን እንደ ሆነ እርሱ ይወስን፤ እግዚአብሔር ይህን ጉዳይ ተመልክቶ ይከላከልልኝ፤ ከአንተም እጅ ያድነኝ።”
16ዳዊትም ይህን ተናግሮ እንደ ጨረሰ ሳኦል “ልጄ ዳዊት ሆይ! በእውነት ይህ የአንተ ድምፅ ነውን?” ብሎ ማልቀስ ጀመረ፤ 17ከዚያም በኋላ ዳዊትን እንዲህ አለው፤ “አንተ እውነተኛ ሰው ነህ! እኔ ግን ስሕተተኛ ነኝ፤ ይህን የመሰለ በደል ስፈጽምብህ አንተ ለእኔ ቸርነት አድርገህልኛል! 18እግዚአብሔር በእጅህ ቢጥለኝም እንኳ አንተ አልገደልከኝምና ለእኔ በጎ አድራጊ መሆንህንም ዛሬ አስመስክረሃል። 19ጠላት በእጁ ገብቶለት ጒዳት ሳያደርስበት የሚለቀው ሰው ከቶ የት ይገኛል? ዛሬ ለእኔ ስላደረግኸው መልካም ነገር እግዚአብሔር ይባርክህ! 20እነሆ፥ አንተ የእስራኤል ንጉሥ እንደምትሆንና የእስራኤልም መንግሥት በአንተ አገዛዝ ሥር ጸንቶ እንደሚኖር ዛሬ አረጋግጫለሁ። 21እንግዲህ ስሜና የቤተሰቤ ስም ተደምስሶ እንዳይረሳ ለማድረግና የዘሮቼንም ሕይወት ከጥፋት ለማትረፍ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ።” 22ዳዊትም ይህን እንደሚያደርግ ማለለት።
ከዚህ በኋላም ሳኦል ወደ ቤቱ ተመልሶ ሄደ፤ ዳዊትና ተከታዮቹም ወደሚሸሸጉበት ስፍራ ተመለሱ።
Currently Selected:
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 24: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997