አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 30
30
በዐማሌቃውያን ላይ የተደረገ ጦርነት
1ዳዊትና ተከታዮቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ጺቅላግ ሲደርሱ ዐማሌቃውያን ኔጌብንና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ በጺቅላግም ላይ አደጋ ጥለው አቃጠሉአት። 2ሴቶችንና በውስጡም የነበሩትን ሁሉ ማርከው ወስደዋል፤ ከዚያም ለቀው ሲሄዱ ያገኙትን ሁሉ ማርከው ወሰዱ እንጂ ማንንም አልገደሉም ነበር፤ 3ዳዊትና ተከታዮቹም እዚያ በደረሱ ጊዜ ከተማይቱ ተቃጥላ፥ ሚስቶቻቸው፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ተማርከው መወሰዳቸውን ተረዱ፤ 4ዳዊትና ተከታዮቹም ፈጽሞ እስኪደክሙ ድረስ ባለማቋረጥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ። 5ሁለቱ የዳዊት ሚስቶች የኢዝራኤላይቱን አሒኖዓምና የቀርሜሎሳይቱ የናባል ሚስት የነበረችው አቢጌል ተማርከው ነበር። #1ሳሙ. 25፥42-43።
6ሰዎቹ ሁሉ በሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው መማረክ ምክንያት ተማርረው ስለ ነበረ በድንጋይ ሊወግሩት በመነጋገራቸው ዳዊት በታላቅ አደጋ ላይ ነበር። እርሱ ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ልቡን አጽናና፤ 7ዳዊትም የአቤሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን “ኤፉዱን አምጣልኝ” አለው፤ አብያታርም ኤፉዱን አመጣለት፤ #1ሳሙ. 22፥20-23። 8ዳዊትም “እነዚያን ወራሪዎች ተከታትዬ በማሳደድ ልያዛቸውን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ።
እግዚአብሔርም “ተከተላቸው! እነርሱንም ይዘህ ምርኮኞችን በመታደግ ታድናለህ” ሲል መለሰለት።
9ስለዚህም ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ተከታዮቹ ወጥተው ሄዱ፤ ብሦር ተብሎ በሚጠራው ወንዝ አጠገብ በደረሱ ጊዜ፥ ጥቂቶቹ በዚያ ዕረፍት በማድረግ ቈዩ። 10ዳዊት ግን ከአራት መቶ ተከታዮቹ ጋር ማሳደዱን ቀጠለ፤ ሌሎቹ ሁለት መቶ ተከታዮቹ ግን ወንዙን ለመሻገር ስለ ደከሙ ወደ ኋላ ቀሩ። 11አንድ ግብጻዊ ወጣት ከበረሓ ሲመጣ አግኝተው ወደ ዳዊት አቀረቡት፤ እነርሱም የሚመገበው እህል ሰጥተውት በላ፤ ውሃም አጠጡት። 12ደረቅ የበለስ ፍሬና ሁለት ጥፍጥፍ ዘቢብ አቀረቡለት፤ ወጣቱም ከተመገበ በኋላ እንደገና በረታ፤ ከዚያ በፊት ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እህል ውሃ አልቀመሰም ነበር። 13ዳዊትም ወጣቱን “የማን አገልጋይ ነህ? አመጣጥህስ ከየት ነው?” ሲል ጠየቀው።
ወጣቱም “እኔ ግብጻዊ የሆንኩ የአንድ ዐማሌቃዊ አገልጋይ ነኝ፤ ታምሜ ስለ ነበር ከሦስት ቀን በፊት ጌታዬ ጥሎኝ ሄደ፤ 14ይህም ከመሆኑ በፊት በይሁዳ ደቡብ የምትገኘውን የከሪታውያንን ግዛትና የካሌብን ግዛት በመውረር ጺቅላግን አቃጥለናታል” ሲል መለሰለት።
15ዳዊትም “እነዚያ ወራሪዎች ወዳሉበት ስፍራ ልትመራን ትችላለህን?” ሲል ጠየቀው።
ወጣቱም “እንደማትገድለኝና ለጌታዬም አሳልፈህ እንደማትሰጠኝ ከማልክልኝ ላሳይህ እችላለሁ” ሲል መለሰለት። 16ከዚያም በኋላ ዳዊትን ወራሪዎቹ ወዳሉበት እየመራ አደረሰው።
ወራሪዎቹም በየቦታው ተበታትነው በመብላትና በመጠጣት ተድላ ደስታ በማድረግ ላይ ነበሩ፤ ከፍልስጥኤምና ከይሁዳ ያገኙት ምርኮ እጅግ ብዙ ነበር፤ 17በምሽት ጊዜ ዳዊት በእነርሱ ላይ አደጋ ጥሎ እስከ ማግስቱ ማታ ድረስ ተዋጋቸው፤ በግመል ላይ ተቀምጠው እየጋለቡ ከሸሹት አራት መቶ ወጣቶች በስተቀር ከነዚያ ወራሪዎች ያመለጠ አንድም አልነበረም፤ 18ዳዊትም ዐማሌቃውያን የወሰዱበትን ማንኛውንም ሰውና ንብረት፥ እንዲሁም ሁለቱን ሚስቶቹን ጭምር አዳነ፤ 19አንድም የጐደለ ሳይኖር ዳዊት የተከታዮቹን ወንዶችና ሴቶች ልጆች፥ እንዲሁም ዐማሌቃውያን ማርከው የወሰዱትን ምርኮ ሁሉ አስመለሰ፤ 20የከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎችንም ሁሉ አገኘ፤ ተከታዮቹም እንስሶቹን በፊታቸው እየነዱ “ይህ ሁሉ የዳዊት ምርኮ ነው!” አሉ።
21ዳዊትም ደክሞአቸው በብሦር ምንጭ አጠገብ ዕረፍት በማድረግ ቈይተው ወደነበሩት ወደ ሁለት መቶ ተከታዮቹ ተመልሶ ሄደ። እነርሱም ዳዊትንና ተከታዮቹን ሊቀበሉአቸው መጡ፤ ዳዊትም ወደ እነርሱ ቀረብ ብሎ ደኅንነታቸውን በመጠየቅ ሰላምታ አቀረበላቸው። 22ነገር ግን ከዳዊት ጋር አብረው ከሄዱት መካከል የብልግና ጠባይ ያለባቸው አንዳንድ የማይረቡ ሰዎች “ከእኛ ጋር ወደ ጦርነቱ ስላልሄዱ ምርኮ ልናካፍላቸው አይገባም፤ ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ብቻ ተረክበው ወዲያ ይሂዱ” አሉ።
23ዳዊትም “ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሰጠን ድል እናንተ ይህን ማድረግ አትችሉም! እኛን በሕይወት ጠብቆ በወራሪዎች ላይ ድልን የሰጠን እርሱ ነው፤ 24እናንተ በምትሉት ነገር ማንም አይስማማበትም! ወደ ኋላ ቀርቶ ጓዝ ሲጠብቅ የቈየውም ሆነ ወደ ጦርነት የዘመተው ሁሉም የተገኘውን ምርኮ እኩል መካፈል አለበት” ሲል መለሰላቸው። 25ዳዊትም ከዚያን ቀን ጀምሮ ይህን እንደ ሕግና ሥርዓት አድርጎ ስለ ተጠቀመበት በእስራኤል ምድር እስከ ዛሬ ድረስ ሲሠራበት ይኖራል።
26ዳዊትም ወደ ጺቅላግ በተመለሰ ጊዜ ከምርኮው ከፊሉን ወዳጆቹ ለሆኑት ለይሁዳ ሽማግሌዎች ላከላቸው፤ ከላከላቸውም ምርኮ ጋር “ይህ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ተወስዶ የተላከላችሁ ስጦታ ነው” የሚል መልእክት ነበር፤ 27ከዚያም ምርኮ በቤትኤል ለሚገኙ፥ በይሁዳ ደቡብ በራማ ለሚገኙ፥ እንዲሁም በያቲር ከተሞች ለሚገኙ ወገኖች ሁሉ ላከላቸው፤ 28ከዚህም በቀር በዓሮዔር፥ በሲፍሞት፥ በኤሽተሞዓና፥ 29በራካል ለሚገኙ፥ እንዲሁም ለይራሕመኤል ጐሣ ለቄናውያን፥ 30በሖርማ፥ በቦርዓሻን፥ በዐታክና፥ 31በኬብሮን ከተሞች ለሚኖሩ ሁሉ ላከላቸው፤ ከዚህም በቀር እርሱና ተከታዮቹ በተዘዋወሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለሚኖሩ ሰዎች ስጦታ ላከ።
Currently Selected:
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 30: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997