አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 8
8
ንጉሥ ስለ ማንገሥ የእስራኤል ሕዝብ ያቀረቡት ጥያቄ
1ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ሁለቱን ልጆቹን በእስራኤል ላይ ፈራጆች አድርጎ ሾሞአቸው ነበር፤ 2የበኲር ልጁ ኢዩኤል፥ ታናሽ ልጁ አቢያ ተብለው የሚጠሩ ሲሆኑ በቤርሳቤህ ዳኞች ሆነው ተሾመው ነበር፤ 3ነገር ግን የአባታቸውን መልካም አርአያነት አልተከተሉም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ የገንዘብ ጥቅም ፈላጊዎች ሆነው ጉቦ እየተቀበሉ ፍርድን ያጣምሙ ነበር።
4ከዚህ በኋላ የእስራኤል ማኅበር መሪዎች በአንድነት በመሰብሰብ ሳሙኤል ወደሚገኝበት ወደ ራማ መጥተው እንዲህ አሉ፦ 5“እነሆ! አንተ በእርጅና ላይ ነህ፤ ልጆችህም የአንተን መልካም አርአያነት አልተከተሉም፤ ስለዚህ በሌሎች አገሮች እንደሚደረገው እኛን የሚመራን ንጉሥ አንግሥልን።” #ዘዳ. 17፥14። 6ንጉሥ ያነግሥላቸው ዘንድ በመጠየቃቸውም ሳሙኤል አዝኖ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ 7እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፦ “ሕዝቡ የሚሉህን ነገር ሁሉ ተቀበል፤ እነርሱ የናቁት አንተን አይደለም፤ በእነርሱ ላይ ነግሼ እንዳልኖር፥ እነርሱ የናቁት እኔን ነው። 8እኔ እነርሱን ከግብጽ ካወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ ፊታቸውን መልሰው ከእኔ በመራቅ ባዕዳን አማልክትን ሲያመልኩ ኖረዋል፤ እንግዲህ በእኔ ላይ ሲያደርጉት የነበረውን ሁሉ እነሆ በአንተም ላይ መፈጸም ጀምረዋል፤ 9ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ የሚሉህን ተቀበል፤ ነገር ግን ንጉሦቻቸው ወደ ፊት በእነርሱ ላይ የሚፈጽሙባቸውን ነገር ሁሉ በመግለጥ በብርቱ አስጠንቅቃቸው።”
10ሳሙኤልም ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው ለጠየቁት ሕዝብ እግዚአብሔር የነገረውን ሁሉ አስረዳቸው፤ 11እንዲህም ሲል ገለጠላቸው፤ “ንጉሣችሁ የሚያደርግባችሁ ነገር ይህ ነው፦ ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ አንዳንዶቹም በሠረገሎቹም ፊት የሚሮጡ ያደርጋቸዋል፤ 12ከእነርሱም አንዳንዶቹን የሺህ አለቆችና የኀምሳ አለቆች አድርጎ ይሾማል፤ ወንዶቹ ልጆቻችሁ የንጉሡ ሁዳድ አራሾችና መከር ሰብሳቢዎች ይሆናሉ፤ ሌሎችም የጦር መሣሪያና የሠረገላ ዕቃ ሠራተኞች ይሆናሉ። 13ሴቶች ልጆቻችሁም ለእርሱ ሽቶ አዘጋጀች፥ ወጥ ሠሪዎችና እንጀራ ጋጋሪዎች ይሆናሉ። 14ምርጥ የሆነውን የእርሻ መሬታችሁን፥ የወይን ተክል ቦታችሁንና የወይራ ተክላችሁን ሁሉ ወስዶ ለባለሟሎቹ ይሰጥባችኋል። 15ከእህላችሁና ከወይናችሁም ከዐሥር አንዱን እጅ ወስዶ ለቤተ መንግሥቱ ባለሟሎችና አጃቢዎች ይሰጥባችኋል። 16የወንድና የሴት አገልጋዮቻችሁን፥ ምርጥ ከብቶቻችሁንና አህዮቻችሁን ወስዶ ለራሱ መጠቀሚያ ያደርጋቸዋል። 17ከበግና ከፍየል መንጋዎቻችሁ ከዐሥር አንዱን ይወስዳል፤ እናንተም የእርሱ ባሪያዎች ትሆናላችሁ፤ 18ያ ዘመን በደረሰ ጊዜ የመረጣችሁት ንጉሥ ስለሚፈጽምባችሁ በደል በመረረ ሁኔታ ማጒረምረም ትጀምራላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን አቤቱታችሁን አያዳምጥም።”
19ይሁን እንጂ ሕዝቡ ሳሙኤል ለነገራቸው ቃል ሁሉ ዋጋ አልሰጡትም፤ ይልቁንም “እንደዚህ አይደለም! እኛ ንጉሥ እንዲኖረን እንፈልጋለን፤ 20በዚህም ዐይነት ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት እኛን የሚያስተዳድርና ከጠላቶቻችንም ጋር በምንዋጋበት ጊዜ ወደ ጦር ሜዳ የሚመራን ንጉሥ ይኖረናል።” 21ሳሙኤልም እነርሱ ያሉትን ሁሉ አዳመጠ፤ ከዚያም ሄዶ ለእግዚአብሔር ነገረ፤ 22እግዚአብሔርም “እነርሱ በጠየቁህ መሠረት፥ ንጉሥ አንግሥላቸው” አለው፤ ከዚያም በኋላ ወደየቤታቸው እንዲሄዱ ሳሙኤል ሕዝቡን አሰናበተ።
Currently Selected:
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 8: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997