ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 11
11
ዳዊትና ቤርሳቤህ
1የዓመት መጀመሪያ በሆነው በጸደይ ወራት፥ በተለምዶ ነገሥታት ወደ ጦርነት በሚዘምቱበት ጊዜ፥ ዳዊት ኢዮአብን ከጦር መኰንኖቹና ከመላው የእስራኤል ሠራዊት ጋር አዘመተው፤ እነርሱም ዐሞናውያንን ድል ነሥተው ራባ ተብላ የምትጠራውን ከተማ ከበቡ፤ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቈየ። #1ዜ.መ. 20፥1።
2አንድ ቀን ከቀትር በኋላ ዘግየት ብሎ ዳዊት ከቀን እንቅልፉ ነቅቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወጣ፤ እዚያም ወዲያና ወዲህ ሲመላለስ ገላዋን የምትታጠብ አንዲት ሴት አየ፤ ሴትዮዋም በጣም ውብ ነበረች፤ 3ስለዚህ ማንነትዋን ለማወቅ ዳዊት አንድ መልእክተኛ ልኮ ቤርሳቤህ ተብላ የምትጠራው የኤሊዓም ልጅ፥ የሒታዊው የኦርዮ ሚስት መሆንዋን ተረዳ። #11፥3 ቤርሳቤህ፦ በዕብራይስጡ “ባትሼባዕ” ነው። 4እርስዋንም ሄደው ያመጡለት ዘንድ ዳዊት መልእክተኞችን ላከ፤ እነርሱም ሄደው አመጡለትና ከእርስዋ ጋር ግንኙነት አደረገ፤ በዚህም ጊዜ ሴትዮዋ ወርኃዊ የመንጻት ሥርዓትዋን የፈጸመች ጥብቅ ነበረች፤ ከዚህ በኋላ ሴትዮዋ ወደ ቤትዋ ተመልሳ ሄደች። 5ከጊዜ በኋላም መፅነስዋን ስለ ተገነዘበች መልእክት ልካ ለዳዊት ነገረችው።
6ከዚህ በኋላ ዳዊት “ሒታዊውን ኦርዮን ወደ እኔ ላከው” ሲል ወደ ኢዮአብ መልእክት ሰደደ፤ ስለዚህም ኢዮአብ ኦርዮን ወደ ዳዊት ላከው፤ 7ኦርዮ በደረሰ ጊዜ ዳዊት “ኢዮአብና ሠራዊቱ ሁሉ እንዴት ናቸው? የጦርነቱስ ሁኔታ እንዴት ነው?” ሲል ጠየቀው፤ 8ከዚህም በኋላ ዳዊት ኦርዮን “እንግዲህ ወደ ቤትህ ሂድና እግርህን ታጠብ” አለው፤ ኦርዮም ከዳዊት ፊት ወጥቶ ሄደ፤ ዳዊትም ወዲያውኑ የምግብ ስጦታ ላከለት፤ 9ኦርዮ ግን ወደ ቤቱ ሳይሄድ ከንጉሡ ክብር ዘበኞች ጋር በቤተ መንግሥቱ የቅጽር በር አጠገብ ተኝቶ ዐደረ፤ 10ኦርዮ ወደ ቤቱ አለመሄዱን ዳዊት በሰማ ጊዜ “ብዙ ጊዜ ከቤተሰብህ ተለይተህ እነሆ አሁን ገና መመለስህ ነው፤ ታዲያ ወደ ቤትህ ያልሄድከው ስለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።
11ኦርዮም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ “የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች በድንኳን ሰፍረው በጦር ሜዳ ይገኛሉ፤ የቃል ኪዳኑም ታቦት ከእነርሱ ጋር ነው፤ የጦር አለቃዬ ኢዮአብና የእርሱም የጦር መኰንኖች በሜዳ ሰፍረዋል፤ ታዲያ እኔ ወደ ቤቴ ሄጄ መብላት፥ መጠጣት፥ ከሚስቴም ጋር መተኛት እንዴት ይቻለኛል? ይህን የመሰለ ነገር ከቶ እንደማላደርግ በአንተ ሕይወት እምላለሁ!”
12ዳዊትም “በል እንግዲህ የዛሬን እዚህ ዋል፤ ነገ ግን መልሼ እልክሃለሁ” አለው፤ ስለዚህ ኦርዮ በዚያን ቀንና በሚቀጥለው ቀን በኢየሩሳሌም ቈየ፤ 13ዳዊትም ኦርዮን ራት ጋበዘውና እስኪሰክር ድረስ የወይን ጠጅ እንዲጠጣ አደረገው፤ በዚያም ሌሊት ኦርዮ በቤተ መንግሥቱ ዘበኞች ቤት ብርድ ልብሱን በማንጠፍ ተኝቶ ዐደረ እንጂ ወደ ቤቱ አልሄደም።
14በማግስቱም ጧት ዳዊት ለኢዮአብ ደብዳቤ ጻፈና በኦርዮ እጅ ላከው፤ 15የጻፈውም ቃል “ኦርዮን ጦርነቱ በተፋፋመበት ግንባር አሰልፈው፤ ከዚያም አንተ ወደ ኋላ አፈግፍገህ እርሱ እንዲገደል አድርገው” የሚል ነበር። 16በዚህ ዐይነት ኢዮአብ ከተማይቱን ከቦ በመያዝ ላይ ሳለ ጠላት ማየሉን በሚያውቅበት ስፍራ ኦርዮን አሰለፈው። 17የጠላት ወታደሮች ከከተማይቱ ወጥተው የኢዮአብን ሠራዊት ወጉ፤ ከዳዊት የጦር መኰንኖች ጥቂቶቹ ሞቱ፤ ኦርዮም አብሮ ሞተ።
18ከዚህ በኋላ ኢዮአብ ስለ ጦርነቱ የሚያስረዳ መልእክት ወደ ዳዊት ላከ፤ 19ለመልእክተኛውም እንዲህ የሚል መመሪያ ሰጠው፤ “ስለ ጦርነቱ ሁሉን ነገር ለንጉሡ ካስረዳህ በኋላ፥ 20ንጉሡ ተቈጥቶ እንዲህ ይልህ ይሆናል፥ ‘እነርሱን ለመውጋት ወደ ከተማይቱ ለምን ተጠጋችሁ? በግንብ ላይ ሆነው ፍላጻዎችን እንደሚወረውሩባችሁ አላወቃችሁምን? 21የጌዴዎን ልጅ አቤሜሌክ እንዴት እንደ ሞተ አታስታውሱምን? እርሱን ቴቤጽ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ አንዲት ሴት ከግንብ ላይ የወፍጮ ድንጋይ ናዳ በመጣል ገደለችው፤ ታዲያ እናንተ ወደ ግንብ የተጠጋችሁት ለምንድን ነው?’ ንጉሡ ይህን ጥያቄ ቢያቀርብልህ፥ ‘የጦር መኰንንህ ኦርዮም ተገድሎአል’ ብለህ ንገረው።” #መሳ. 9፥53።
22ስለዚህም መልእክተኛው ወደ ዳዊት ሄዶ ኢዮአብ ያዘዘውን ሁሉ እንዲህ ሲል ነገረው፤ 23“ጠላቶቻችን ስለ በረቱብን እኛን ለመውጋት ከከተማይቱ ወጥተው ወደ ሜዳ መጡ፤ እኛ ግን አሳደን ወደ ከተማይቱ ቅጽር በር መለስናቸው። 24ከዚያም በኋላ በግንብ ላይ ሆነው ፍላጻዎችን ወረወሩብን፤ ንጉሥ ሆይ! ከጦር መኰንኖችህ ጥቂቶቹ በዚያን ጊዜ ሞቱ፤ አገልጋይህ ኦርዮም ተገደለ።”
25ዳዊትም መልእክተኛውን “እንዲህ ብለህ ለኢዮአብ ንገረው፦ በጦርነት ላይ ማን እንደሚሞት በቅድሚያ ስለማይታወቅ ‘አይዞህ በርታ’ በለው፤ ብስጭት እንዳያድርበትም ንገረው፤ ይልቁንም ኀይሉን አጠናክሮ አደጋ በመጣል ከተማይቱን እንዲይዝ አስጠንቅቀው” አለው።
26የኦርዮ ሚስት ባልዋ እንደ ተገደለ በሰማች ጊዜ በማልቀስ አዘነችለት፤ 27የሐዘንዋም ጊዜ ሲፈጸም ዳዊት ሰው ልኮ ወደ ቤተ መንግሥት አስመጣት፤ ለእርሱም ሚስት ሆና ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት ያደረገው ነገር እግዚአብሔርን አሳዘነ።
Currently Selected:
ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 11: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997