ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 4
4
የኢያቡስቴ መገደል
1የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ አበኔር በኬብሮን መገደሉን በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ በድንጋጤ ተሸበረ፤ 2ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት መኰንኖች ነበሩት፤ እነርሱም ከብንያም ነገድ የበኤሮት ተወላጆች የሆኑት የሪሞን ልጆች በዓናና ሬካብ ነበሩ፤ በኤሮት የብንያም ክፍል እንደ ሆነች ይታሰብ ነበር፤ 3የበኤሮት የመጀመሪያዎቹ ነዋሪዎችም ወደ ጊታይም ተሰደው ከዚያን ዘመን ጀምሮ የሚኖሩት በዚያው ነበር።
4ሌላው የሳኦል ዘር የዮናታን ልጅ መፊቦሼት ሲሆን፥ እርሱ ሳኦልና ዮናታን በተገደሉ ጊዜ ገና የአምስት ዓመት ልጅ ነበር፤ የእነርሱን ሞት የሚገልጠው ወሬ ከኢይዝራኤል ከተማ በተነገረ ጊዜ ሞግዚቱ እርሱን ይዛ ሸሸች፤ ነገር ግን በጥድፍያ በምትሸሽበት ጊዜ ከእጅዋ ወደቀ፤ ከዚህም የተነሣ ሽባ ሆነ። #2ሳሙ. 9፥3።
5የሪም ልጆች ሬካብና በዓና ወደ ኢያቡስቴ ቤት በመሄድ እኩለ ቀን ላይ ደረሱ፤ እርሱም በዚያን ሰዓት የቀትር ጊዜ ዕረፍት በማድረግ ላይ ነበር፤ #4፥5 ጠባቂዋ ሴት ማንቀላፋትዋ፦ ሌሎች ትርጒሞች ሬካብና በዓና ስንዴ የሚወስዱ መስለው ወደ ውስጥ በመግባት ሆዱን ወግተው ገደሉት ይላሉ። 6ጠባቂዋ ሴት ስንዴ እያበጠረች በበር ላይ ተቀምጣ ታንቀላፋ ነበር፤ ስለዚህም ሬካብና በዓና በቀስታ አልፈው ገቡ፤ 7ከገቡም በኋላ ወደ ኢያቡስቴ መኝታ ክፍል ዘለቁ፤ እርሱም በአልጋ ላይ ተኝቶ ሳለ ወግተው ገደሉት፤ ራሱንም ቈርጠው ወሰዱ፤ ሌሊቱንም ሁሉ በዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ በኩል አልፈው ሄዱ፤ 8የኢያቡስቴንም ራስ በኬብሮን ለነበረው ለንጉሥ ዳዊት ካቀረቡ በኋላ እንዲህ አሉ፤ “ሊገድልህ ይመኝ የነበረው የጠላትህ የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ ይኸውልህ፤ ንጉሥ ሆይ፥ ዛሬ በሳኦልና በቤተሰቡ ላይ እግዚአብሔር ለጌታዬ ለንጉሡ ተበቅሎለታል።”
9ዳዊትም ለሬካብና ለወንድሙ ለበዓና እንዲህ ሲል መለሰላቸው “ከአደጋ ሁሉ ባዳነኝ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ! 10በጺቅላግ ወደ እኔ መጥቶ ስለ ሳኦል ሞት የነገረኝ መልእክተኛም እንደዚሁ መልካም ዜና ያመጣልኝ መስሎት ነበር፤ እኔ ግን እርሱን ይዤ አስገደልኩት፤ መልካም ዜና ነው ብሎ ላመጣውም ወሬ የከፈልኩት ዋጋ ይኸው ነበር። #2ሳሙ. 1፥1-16። 11ታዲያ፥ በገዛ ቤቱ ተኝቶ የነበረውን ንጹሕ ሰው ለገደሉት ሰዎችማ የሚከፈላቸው የበቀል ዋጋ ምን ያኽል የከፋ ይሆን? ስለዚህም እርሱን በመግደላችሁ ምክንያት እኔ በእናንተ ላይ የበቀል እርምጃ በመውሰድ ከምድር ላይ ጠራርጌ አጠፋችኋለሁ!” 12ወዲያውም ዳዊት እንዲገድሉአቸው ለወታደሮቹ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ወታደሮቹም ሬካብንና በዓናን ገደሉአቸው፤ እጃቸውንና እግራቸውንም ቈርጠው በኬብሮን በሚገኘው ኲሬ አጠገብ እንጨት ላይ ሰቀሉአቸው፤ የኢያቡስቴንም ራስ ወስደው በዚያው በኬብሮን በሚገኘው በአበኔር መቃብር ውስጥ ቀበሩት።
Currently Selected:
ሁለተኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 4: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997