2 ወደ ጢሞቴዎስ 4
4
1በእግዚአብሔርና እንዲሁም መንግሥቱን በሚያቋቁምበት ጊዜ፥ በሕያዋንና በሙታን ላይ በሚፈርደው በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ዐደራ እልሃለሁ፤ 2ቃሉን ስበክ፤ ቢመችም ባይመችም በማንኛውም ጊዜ ተግተህ ሥራ፤ እያስረዳህ እየገሠጽክና እየመከርክ፥ በትዕግሥትና በማስተማር ትጋ። 3ሰዎች ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት ለመስማት የማይፈልጉበት ጊዜ ይመጣል፤ ነገር ግን ለወሬ በመጐምጀት እነርሱ ራሳቸው የሚወዱትን ነገር የሚነግሩአቸውን አስተማሪዎች ይሰበስባሉ። 4ስለዚህ እውነትን መስማት ትተው ተረትን መስማት ይወዳሉ። 5አንተ ግን በሁሉ ነገር ጥንቁቅ ሁን፤ መከራን በመቀበል ጽና፤ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አከናውን፤ አገልግሎትህንም ሁሉ ፈጽም።
6እኔ ግን መሥዋዕት ለመሆን ተቃርቤአለሁ፤ ከዚህ ዓለም ተለይቼ የምሄድበት ጊዜም ደርሶአል፤ 7ጦርነትን በመልካም ተዋግቻለሁ፤ የእሽቅድድም ሩጫዬን እስከ መጨረሻው ሮጫለሁ፤ እምነትን ጠብቄአለሁ። 8ከእንግዲህ ወዲህ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ይህንንም አክሊል ያ ትክክለኛ ፍርድን ፈራጁ ጌታ በዚያን ቀን ይሰጠኛል፤ የሚሰጠውም ለእኔ ብቻ ሳይሆን የእርሱን መገለጥ ለሚወድዱ ሁሉ ነው።
ስለ ግል ጉዳዮች
9በፍጥነት ወደ እኔ እንድትመጣ ይሁን፤ 10ዴማስ ይህን ዓለም ወዶ ተለይቶኛል፤ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስ ወደ ገላትያ፥ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል። #ቆላ. 4፥14፤ ፊልሞና 24፤ 2ቆሮ. 8፥23፤ ገላ. 2፥3፤ ቲቶ 1፥4። 11ከእኔ ጋር ያለው ሉቃስ ብቻ ነው፤ ማርቆስ ለአገልግሎት ስለሚጠቅመኝ ፈልገህ ይዘኸው ና። #ቆላ. 4፥14፤ ፊልሞና 24፤ ሐ.ሥ. 12፥12፤25፤ 13፥13፤ 15፥37-39፤ ቆላ. 4፥10። 12ቲኪቆስን ወደ ኤፌሶን ልኬዋለሁ። #ሐ.ሥ. 20፥4፤ ኤፌ. 6፥21-22፤ ቆላ. 4፥7-8። 13ስትመጣ በጢሮአዳ በካርፑስ ዘንድ የተውኩትን ካባ ይዘህልኝ ና፤ መጻሕፍቱንም ይልቁንም የብራና መጻሕፍቱን አምጣልኝ። #ሐ.ሥ. 20፥6።
14የናስ አንጥረኛው እስክንድር ከፍተኛ ጒዳት አደረሰብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይከፍለዋል። #1ጢሞ. 1፥20፤ መዝ. 62፥12፤ ሮም 2፥6። 15እርሱ እኛ የምንናገረውን በብርቱ ስለሚቃወም አንተም ራስህ ከእርሱ ተጠንቀቅ።
16በተከሰስኩበት ነገር የመጀመሪያ መከላከያዬን ባቀረብኩ ጊዜ ሁሉም ተለዩኝ እንጂ ከእኔ ጋር ሆኖ የረዳኝ ማንም አልነበረም፤ ይህንንም ነገር እግዚአብሔር እንደ በደል አድርጎ አይቊጠርባቸው። 17ነገር ግን መልእክቱ በእኔ አማካይነት በሙሉ እንዲነገርና አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ ከእኔ ጋር ሆኖ አበረታኝ፤ ከአንበሳም አፍ ድኛለሁ። 18ጌታ ከማንኛውም ክፉ ነገር ያድነኛል፤ በሰማይ ላለው መንግሥቱም ያበቃኛል፤ ለእርሱ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን! አሜን።
የመጨረሻ ሰላምታ
19ለጵርስቅላና ለአቂላ፥ ለኦኔሲፎርም ቤተሰቦች ሰላምታ አቅርብልኝ። #ሐ.ሥ. 18፥2፤ 2ጢሞ. 1፥16-17። 20ኤራስጦስ በቆሮንቶስ ቀርቶአል፤ ጥሮፊሞስ ስለ ታመመ በሚሊጢ ትቼዋለሁ። #ሐ.ሥ. 19፥22፤ ሮም 16፥23፤ ሐ.ሥ. 20፥4፤ 21፥29። 21ክረምት ሳይገባ ወደ እኔ እንድትመጣ ይሁን።
ኤውቡሉስ፥ ጱዴስ፥ ሊኖስ፥ ቅላውዲያና አማኞችም ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል።
22ጌታ ከአንተ ጋር ይሁን።
የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
Currently Selected:
2 ወደ ጢሞቴዎስ 4: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997