የሐዋርያት ሥራ 16
16
ጢሞቴዎስ ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር
1ጳውሎስ ወደ ደርቤና ወደ ልስጥራ ሄደ፤ በልስጥራ ጢሞቴዎስ የሚባል አማኝ ይኖር ነበር፤ እናቱ አይሁዳዊት ክርስቲያን ነበረች፤ አባቱ ግን አረማዊ ነበር። 2ጢሞቴዎስ በልስጥራና በኢቆንዮን ባሉት ወንድሞች ዘንድ መልካም ዝና ነበረው። 3ጳውሎስ ጢሞቴዎስን ይዞ መሄድ ስለ ፈለገ በዚያ ስፍራ በነበሩት አይሁድ ምክንያት እንዲገረዝ አደረገው፤ ይህንንም ያደረገው እነርሱ የጢሞቴዎስ አባት አረማዊ መሆኑን ያውቁ ስለ ነበረ ስለ እነርሱ ብሎ ነው። 4ጳውሎስና ሲላስ በየከተማው ሲያልፉ በኢየሩሳሌም ባሉት ሐዋርያትና ሽማግሌዎች የተወሰነውን ደንብ ለአማኞች ያስታውቁ ነበር፤ በሥራ ላይ እንዲያውሉትም ያሳስቡአቸው ነበር። 5ስለዚህ አብያተ ክርስቲያን በእምነት ጠነከሩ፤ ቊጥራቸውም በየቀኑ እየጨመረ ይሄድ ነበር።
ጳውሎስ ወደ መቄዶንያ እንዲሄድ መጠራቱ
6ጳውሎስና ሲላስ በእስያ ቃሉን እንዳይናገሩ መንፈስ ቅዱስ ስለ ከለከላቸው በፍርግያና በገላትያ አገር አድርገው አለፉ፤ 7ወደ ሚስያ ድንበር በደረሱ ጊዜ ወደ ቢታኒያ ለመሄድ አስበው ነበር፤ ነገር ግን የኢየሱስ መንፈስ ወደዚያ እንዲሄዱ አልፈቀደላቸውም። 8ስለዚህ በሚስያ በኩል አልፈው ወደ ጢሮአዳ ወረዱ። 9እዚያ በሌሊት አንድ የመቄዶንያ ሰው ቆሞ “ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን!” እያለ ሲለምነው ጳውሎስ በራእይ አየ። 10ጳውሎስ ይህን ራእይ ካየ በኋላ ወዲያውኑ ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ፈለግን፤ ይህም የሆነው ለመቄዶንያ ሰዎችም ወንጌልን እንድናስተምር ጌታ እንደ ጠራን ስለ ተረዳን ነው።
ልድያ በክርስቶስ ማመንዋ
11ከጢሮአዳ በመርከብ ተሳፍረን በቀጥታ ወደ ሳሞትራቄ ሄድን፤ በማግስቱም ወደ ናጱሌ ሄድን። 12ከዚያም ተነሥተን ወደ ፊልጵስዩስ ደረስን፤ ፊልጵስዩስ በመቄዶንያ የምትገኝ ታላቅ ከተማና የሮማውያን ቅኝ አገር ነበረች፤ በዚህችም ከተማ ጥቂት ቀኖች አሳለፍን። 13በሰንበትም ቀን ለጸሎት ይሰበሰቡበት ወደነበረው ከከተማው ውጪ ወደሚገኘው ወደ ወንዝ ዳር ሄድን፤ እዚያም ተቀምጠን ለተሰበሰቡት ሴቶች የእግዚአብሔርን ቃል አስተማርን። 14ይሰሙን ከነበሩትም ሴቶች አንድዋ የትያጥሮን ከተማ ተወላጅ የሆነች የቀይ ልብስ ነጋዴ፥ ልድያ የምትባል ሴት ነበረች፤ እርስዋ እግዚአብሔርን የምታመልክ ሴት ነበረች፤ ጌታም ልቡናዋን ስለ ከፈተላት ጳውሎስ የሚናገረውን ቃል ታዳምጥ ነበር፤ 15እርስዋና በቤትዋ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ፥ “በጌታ የማምን መሆኔን ካረጋገጣችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ተቀመጡ” ስትል አጥብቃ ለመነችን።
በፊልጵስዩስ ከተማ ጳውሎስና ሲላስ መታሰራቸው
16አንድ ቀን ወደ ጸሎት ቦታ ስንሄድ ወደፊት የሚሆነውን ነገር በጥንቈላ የሚያናግር ርኩስ መንፈስ ያደረባት አንዲት አገልጋይ ልጃገረድ በመንገድ አገኘችን፤ ይህች ልጃገረድ በጥንቈላዋ ለአሳዳሪዎችዋ ብዙ ትርፍ ታስገኝላቸው ነበር። 17እርስዋ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፥ “እነዚህ ሰዎች የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው! እነርሱ የመዳንን መንገድ ያበሥሩአችኋል!” በማለት ትጮኽ ነበር። 18ይህንንም ብዙ ቀን እየደጋገመች ታደርግ ነበር፤ ጳውሎስ ግን ተበሳጨና ዞር ብሎ ርኩሱን መንፈስ “በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከእርስዋ እንድትወጣ አዝሃለሁ!” አለው። ርኩሱም መንፈስ ወዲያውኑ ወጣ።
19አሳዳሪዎችዋ ጥቅም የሚያገኙበት ተስፋ እንደ ተቋረጠባቸው ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ያዙአቸው፤ እየጐተቱም ወደ አደባባይ ወሰዱአቸውና በሹሞች ፊት አቀረቡአቸው። 20ወደ ሮማውያን ባለሥልጣኖችም አመጡአቸውና እንዲህ አሉ፤ “እነዚህ ሰዎች የአይሁድ ወገኖች ናቸው፤ በከተማችንም ሁከት ያስነሣሉ፤ 21እኛ የሮም ዜጋዎች ልንቀበለው ወይም ልናደርገው ያልተፈቀደልንን ሥርዓት ያስተምራሉ።” 22ሕዝቡም ሁሉ ተባብሮ በእነርሱ ላይ ተነሣ።
ባለሥልጣኖችም የጳውሎስንና የሲላስን ልብስ ገፈፉና በዱላ እንዲደበደቡ አዘዙ። 23ብዙ ከተደበደቡም በኋላ ወደ ወህኒ ቤት አገቡአቸው፤ የወህኒ ቤቱም ጠባቂ በጥብቅ እንዲጠብቃቸው ታዘዘ። 24ጠባቂው ይህን ትእዛዝ ከተቀበለ በኋላ፥ በወህኒ ቤቱ ውስጠኛ ክፍል አስገባቸው፤ እግሮቻቸውንም በግንድና ግንድ መካከል አጣብቆ አሰራቸው።
25ወደ እኩለ ሌሊት ገደማ ጳውሎስና ሲላስ በጸሎትና በመዝሙር እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ ሌሎችም እስረኞች ያዳምጡአቸው ነበር። 26በድንገት የወህኒ ቤቱ መሠረት እስኪናጋ ድረስ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ በሮቹም ሁሉ በአንድ ጊዜ ተከፈቱ፤ የእያንዳንዱም እስረኛ ሰንሰለት ተፈታ። 27ጠባቂው ከእንቅልፉ ነቅቶ የወህኒ ቤቱ በሮች ተከፍተው ባየ ጊዜ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ሊገድል ሰይፉን መዘዘ። 28ነገር ግን ጳውሎስ፥ “ሁላችንም እዚህ ነን! ስለዚህ በራስህ ላይ ጒዳት አታድርስ!” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
29በዚህ ጊዜ ጠባቂው መብራት አስመጥቶ እየሮጠ ወደ ውስጥ ገባ፤ እየተንቀጠቀጠም በጳውሎስና በሲላስ እግር ሥር በግንባሩ ተደፋ። 30ወደ ውጪም አወጣቸውና “ጌቶቼ ሆይ! ለመዳን ምን ማድረግ ይገባኛል?” አላቸው።
31እነርሱም “በጌታ በኢየሱስ እመን፤ ትድናለህ፤ ቤተሰቦችህም ይድናሉ” አሉት። 32የጌታንም ቃል ለእርሱና በእርሱ ቤት ላሉትም ሁሉ ተናገሩ። 33በዚያኑ ሰዓት በሌሊት የወህኒ ቤቱ ጠባቂ ወሰዳቸውና ቊስላቸውን አጠበላቸው፤ ወዲያውኑ እርሱና ቤተሰቡ በሙሉ ተጠመቁ። 34ከዚህ በኋላ ጳውሎስንና ሲላስን ወደ ቤቱ ወስዶ ምግብ አቀረበላቸው፤ በእግዚአብሔር ስላመነም ከቤተ ሰቡ ሁሉ ጋር ደስ አለው።
35በነጋም ጊዜ ባለሥልጣኖቹ “እነዚያ ሰዎች ይለቀቁ” ብለው ፖሊሶችን ላኩ።
36የወህኒ ቤት ጠባቂውም “እናንተ እንድትለቀቁ ባለሥልጣኖቹ ሰው ልከዋልና እንግዲህ ወጥታችሁ በሰላም ሂዱ” ሲል ለጳውሎስ ነገረው።
37ጳውሎስ ግን “እኛ የሮም ዜጋዎች ስንሆን ያለ ፍርድ በአደባባይ ገርፈው ወደ ወህኒ አስገብተውናል። አሁን ደግሞ ከወህኒ ቤት በስውር እንድንወጣ ያደርጋሉን? አይሆንም! እነርሱ ራሳቸው መጥተው ያስወጡን!” ሲል መለሰ።
38ፖሊሶቹ ይህን ነገር ለባለሥልጣኖቹ ነገሩ፤ ባለሥልጣኖቹም ጳውሎስና ሲላስ የሮም ዜጋዎች መሆናቸውን ባወቁ ጊዜ ፈሩ። 39ስለዚህ መጥተው ይቅርታ ጠየቁአቸውና ከወህኒ ቤት አስወጡአቸው፤ ከከተማውም እንዲሄዱ ለመኑአቸው።
40ጳውሎስና ሲላስም ከወህኒ ቤት ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ፤ እዚያም ወንድሞችን አግኝተው፥ አጽናኑአቸውና ከተማውን ለቀው ሄዱ።
Currently Selected:
የሐዋርያት ሥራ 16: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997