የሐዋርያት ሥራ 8
8
ሳውል ክርስቲያኖችን እንደ አሳደደ
1ሳውልም በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ነበር፤ እስጢፋኖስ በሞተበት ቀን በኢየሩሳሌም በምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ተነሣ፤ ከሐዋርያት በቀር አማኞች ሁሉ ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ ምድር ተበተኑ። 2አንዳንድ መንፈሳውያን ሰዎች እስጢፋኖስን ቀበሩት፤ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ አለቀሱለት።
3ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ይጥር ነበር፤ ከቤት ወደ ቤትም እየገባ ወንዶችና ሴቶች አማኞችን እየጐተተ ያወጣ ነበር፤ ወደ እስር ቤትም ያስገባቸው ነበር። #ሐ.ሥ. 22፥4-5፤ 26፥9-11።
ወንጌል በሰማርያ መሰበኩ
4የተበተኑትም አማኞች በሄዱበት ስፍራ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ያስተምሩ ነበር። 5ፊልጶስም ወደ ሰማርያ ከተማ ሄዶ ሰዎቹን ስለ መሲሕ አስተማራቸው። 6ሰዎቹም የፊልጶስን ቃል በሰሙና የሚያደርጋቸውን ተአምራት ባዩ ጊዜ በአንድ ሐሳብ በጥንቃቄ ያዳምጡት ነበር። 7ርኩሳን መናፍስትም በታላቅ ድምፅ እየጮኹ ከብዙ ሰዎች ይወጡ ነበር፤ ብዙ ሽባዎችና አንካሶችም ይድኑ ነበር። 8ስለዚህ በዚያች ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ።
9በዚያች ከተማ ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ይህ ሰው በከተማይቱ ውስጥ አስማት እያደረገ የሰማርያን ሕዝብ ሲያስደንቅ ቈይቶአል፤ “እኔ ትልቅ ሰው ነኝ!” እያለም ይናገር ነበር። 10ሰዎች ሁሉ ትንሹም ትልቁም “ይህ ሰው ታላቅ ተብሎ የሚጠራው የእግዚአብሔር ኀይል ነው!” እያሉ በጥንቃቄ ያዳምጡት ነበር። 11በጥንቃቄ ያዳምጡት የነበረውም ከብዙ ጊዜ ጀምሮ በጥንቈላ ያስደንቃቸው ስለ ነበረ ነው። 12ነገር ግን ፊልጶስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተናገረውን መልካም ዜና በሰሙ ጊዜ ወንዶችም ሴቶችም አምነው ተጠመቁ። 13ስምዖን እንኳን ሳይቀር አምኖ ተጠመቀና ከፊልጶስ ጋር ተባባሪ ሆነ፤ የሚደረጉትንም ድንቅ ነገሮችና ታላላቅ ተአምራት በማየቱ ይገረም ነበር።
14በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያት የሰማርያ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል መቀበላቸውን በሰሙ ጊዜ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ወደ ሰማርያ ላኩአቸው። 15ስለዚህ የሰማርያ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ጴጥሮስና ዮሐንስ ሄደው ጸለዩላቸው። 16የሰማርያ ሰዎች በጌታ ኢየሱስ ስም ተጠምቀው ነበር እንጂ መንፈስ ቅዱስ ገና በአንዳቸውም ላይ አልወረደም ነበር። 17ስለዚህ ጴጥሮስና ዮሐንስ፥ እጆቻቸውን በጫኑባቸው ጊዜ ሰዎቹ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።
18ሐዋርያት እጆቻቸውን ሲጭኑባቸው መንፈስ ቅዱስ ለሰዎቹ መሰጠቱን ስምዖን ባየ ጊዜ ገንዘብ አመጣላቸውና፥ 19“እኔም እጄን የምጭንበት ሰው መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበል ይህን ሥልጣን ስጡኝ” አለ።
20ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፦ “የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ ለማግኘት በማሰብህ ገንዘብህ ካንተ ጋር ይጥፋ! 21ልብህ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ስላልሆነ አንተ ከዚህ ነገር ክፍል ወይም ዕጣ የለህም። 22እንግዲህ ከዚህ ከክፋትህ ተጸጽተህ ንስሓ ግባ፤ ምናልባት የልብህን ክፉ አሳብ ይቅር ይልልህ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን ለምን። 23አንተ በመራራ ቅናት እንደ ተሞላህና የኃጢአት እስረኛ እንደ ሆንክ አያለሁ።”
24ስምዖንም “አሁን ከተናገራችሁት አንዳች እንኳን እንዳይደርስብኝ እናንተው ራሳችሁ ወደ ጌታ ጸልዩልኝ” አላቸው።
25ጴጥሮስና ዮሐንስ ከመሰከሩና የጌታንም ቃል ከተናገሩ በኋላ በብዙ የሰማርያ መንደሮች ወንጌልን እያበሠሩ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
ፊልጶስ ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ እንደ አጠመቀ
26የጌታ መልአክ ፊልጶስን፥ “ተነሥና ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ወደ ደቡብ ሂድ” አለው፤ ያ መንገድ የበረሓ መንገድ ነበር። 27እርሱም ተነሥቶ ሄደ፤ እነሆ፥ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ለእግዚአብሔር ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ነበር፤ ይህ ሰው ሕንደኬ ለተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ባለሟልና የገንዘብዋ ሁሉ ኀላፊ ነበረ። 28እርሱ ወደ አገሩ ሲመለስ በሠረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር። 29በዚህ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ፊልጶስን “ሂድ ወደዚያ ሠረገላ ቅረብና ተገናኘው” አለው። 30ስለዚህ ፊልጶስ ወደዚያ ሮጦ ሄደና ኢትዮጵያዊው የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰምቶ “የምታነበው ትርጒሙ ይገባሃልን?” አለው። 31ኢትዮጵያዊውም “የሚያስረዳኝ ሰው ሳይኖር እንዴት ሊገባኝ ይችላል?” አለና ፊልጶስን “ወደ ሠረገላው ውጣና ከእኔ ጋር ተቀመጥ” አለው። 32እርሱም ያነበው የነበረው የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል የሚከተለው ነበረ፦
“እርሱ ለመታረድ እንደሚነዳ በግ ነበረ፤
ሲሸልቱትም ዝም እንደሚል ጠቦት፤
እርሱም ለመናገር አፉን አልከፈተም።
33እርሱ ተዋረደ፤ ቅን ፍርድም አልተሰጠውም፤
ሕይወቱም ከምድር ተወግዶአልና
ስለ ትውልዱ ማን ሊናገር ይችላል?” #ኢሳ. 53፥7-8።
34ጃንደረባውም ፊልጶስን፥ “ነቢዩ ይህን የተናገረው ስለ ማን ነው? ስለ ራሱ ነውን ወይስ ስለሌላ? እባክህን ንገረኝ” አለው። 35ፊልጶስም ከዚህ የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል ጀምሮ ስለ ኢየሱስ መልካሙን ዜና አበሠረው። 36ሲሄዱም ውሃ ወዳለበት ቦታ ደረሱ፤ ጃንደረባውም “እነሆ፥ እዚህ ውሃ አለ፤ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ነገር ምንድን ነው?” አለ።
[ 37ፊልጶስም “በሙሉ ልብህ ካመንክ መጠመቅ ትችላለህ” አለው። ጃንደረባውም “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አምናለሁ” አለ።] #8፥37 አንዳንድ የብራና ጽሑፎች ቊ 37 ይጨምራሉ፤ የጥንት የብራና ጽሑፎች ግን አይጨምሩም።
38ጃንደረባው ሠረገላው እንዲቆም አዘዘ፤ ሁለቱም ወደ ውሃው ወረዱና ፊልጶስ ጃንደረባውን አጠመቀው። 39ከውሃው ከወጡ በኋላ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ወሰደው፤ ጃንደረባውም ዳግመኛ አላየውም፤ ይሁን እንጂ ደስ እያለው ጒዞውን ቀጠለ። 40ፊልጶስ ግን በአዞጦስ ተገኘ፤ ወደ ቂሳርያም እስከ መጣ ድረስ በየከተሞቹ ሁሉ እየሄደ ወንጌልን ይሰብክ ነበር።
Currently Selected:
የሐዋርያት ሥራ 8: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997