ኦሪት ዘዳግም 2
2
የእስራኤል ሕዝብ በበረሓ የተንከራተቱባቸው ዓመቶች
1“እግዚአብሔር በነገረኝ መሠረት ወደ ምድረ በዳ ተመልሰን ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው አቅጣጫ በመጓዝ የኤዶምን ኮረብታማ ቦታ ለብዙ ቀን ዞርን። #ዘኍ. 21፥4። 2ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ነገረኝ፦ 3‘በእነዚህ ኮረብታማ አገሮች የተንከራተታችሁበት ጊዜው ረጅም ነው፤ አሁን ግን ወደ ሰሜን አቅጣጫ ሂዱ፤ 4ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዝ፤ ዘመዶቻችሁ የዔሳው ዘሮች በሚኖሩበት በኮረብታማው በኤዶም አገር በኩል ታልፋላችሁ፤ እነርሱ እናንተን ይፈሩአችኋል፤ ነገር ግን ተጠንቀቁ፤ #ዘፍ. 36፥8። 5የኤዶምን ኮረብታማ አገር ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታኽል እንኳ አልሰጣችሁምና በእነርሱ ላይ ጦርነት አታንሡ። 6የሚያስፈልጋችሁን ምግብና ውሃ በገንዘብ ግዙ።’
7“በእርግጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሠራችሁት ሥራ ሁሉ ብዙ በረከት ሰጥቶአችኋል፤ በዚህ በሰፊው በረሓ በሄዳችሁበት ሁሉ ተንከባክቦአችኋል፤ በእነዚህ በአርባ ዓመቶች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ስለ ነበረ ምንም የጐደለባችሁ ነገር አልነበረም።
8“ስለዚህም ወንድሞቻችን የዔሳው ዘሮች የሚኖሩበትን የኤዶምን አገር አልፈን ከኤላትና ከኤጽዮንጋብር በሚመጣው መንገድ በአራባ በኩል አድርገን ወደ ሞአብ ምድረ በዳ አቅጣጫ ተመለስን። 9እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ ‘የሎጥ ዘሮች የሆኑትን ሞአባውያንን አታስቸግሩ፤ ከእነርሱም ጋር ጦርነት ለመግጠም አታነሣሡአቸው፤ የዔርን ከተማ ለእነርሱ መኖሪያ ሰጥቼአለሁ፤ ስለዚህም ከእነርሱ ምድር ምንም አልሰጣችሁም።’ ” #ዘፍ. 19፥37።
10[ኤሚም ተብለው የሚጠሩ ብርቱ የሆኑ ብዙ ሕዝብ በዔር ይኖሩ ነበር፤ እነርሱም ግዙፋን እንደ ሆኑት እንደ ዐናቅ ነገዶች ቁመተ ረጃጅሞች ነበሩ። 11እንደ ዐናቃውያንም ረፋያውያን ተብለው ይጠሩ ነበር። ሞአባውያን ግን ኤሚማውያን ብለው ይጠሩአቸው ነበር። 12ሖራውያንም በኤዶም ይኖሩ ነበር፤ ነገር ግን የዔሳው ዘሮች ሖራውያንን ነቃቅለው በማባረር በእነርሱ ቦታ ሰፍረውበት ነበር፤ ይኸውም እስራኤላውያን ዘግየት ብለው እግዚአብሔር በሰጣቸው ምድር ላይ እንዳደረጉት ዐይነት መሆኑ ነው።]
13“ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር በነገረን መሠረት የዘሬድን ወንዝ ተሻገርን፤ 14ይህም የሆነው ቃዴስ በርኔን ትተን ከሄድን ከሠላሳ ስምንት ዓመት በኋላ መሆኑ ነው፤ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ አስቀድሞ በመሐላ በተናገረው መሠረት ለጦርነት የደረሱ የዚያ ትውልድ ወንዶች ሁሉ አልቀው ነበር። 15እግዚአብሔርም በሙሉ እስኪደመስሳቸው ድረስ እነርሱን ከመቃወም አልተመለሰም።
16“እነርሱ ሁሉ ካለቁ በኋላ፥ 17እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ 18‘የሞአብ ክልል በሆነው በዔር በኩል ዛሬውኑ ማለፍ አለባችሁ። 19ከዚህም በኋላ የሎጥ ዘሮች ወደሚኖሩበት ወደ ዐሞናውያን ምድር ትቃረባላችሁ፤ እነርሱንም አታስቸግሩአቸው፤ ወይም ከእነርሱ ጋር ጦርነት ለመግጠም አታነሣሡአቸው፤ ለእነርሱ ከሰጠኋት ምድር ለእናንተ ምንም አልሰጣችሁም።’ ” #ዘፍ. 19፥38።
20[ይህም ግዛት በዚያ ይኖሩ በነበሩ ሕዝብ ይጠሩ በነበሩበት ስም የረፋያውያን ምድር ተብሎ ይጠራ ነበር፤ ዐሞናውያን በበኩላቸው ዛምዙሚም ብለው ይጠሩአቸው ነበር። 21እነርሱም እንደ ዐናቃውያን ቁመተ ረጃጅሞች፥ ብርቱና ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኀይል ዐሞናውያን ስለ ደመሰሱአቸው ምድራቸውን ወርሰው ራሳቸው ሰፍረውበት ነበር። 22እግዚአብሔር ኮረብታማ በሆነችው በኤዶም ለሚኖሩት ለዔሳው ዘሮችም እንደዚሁ አድርጎላቸው ነበር፤ ይኸውም ቀድሞ የኖሩባትን ሖራውያንን ደምስሶ እስከ አሁን የሚኖሩባትን ምድራቸውን ኤዶማውያን ወርሰው እንዲሰፍሩባት አድርጎአል። 23ቀርጤስ ተብላ ከምትጠራ ደሴት የመጡ ሕዝቦች በጋዛ አካባቢ የሚኖሩ ኤዋውያን ተብለው የሚጠሩ ነዋሪዎችን ደምስሰው በእነርሱ ቦታ ሰፈሩ።]
24“በሞአብ በኩልም ካለፍን በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለን፦ ‘አሁን ተነሥታችሁ የአርኖንን ወንዝ ተሻገሩ፤ በሐሴቦን ተቀምጦ የሚገዛውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን ከነምድሩ ለእናንተ አሳልፌ ሰጥቻችኋለሁ፤ እርሱን ወግታችሁ ምድሩን ውረሱ፤ 25ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም ስፍራ የሚኖሩ ሕዝቦች እናንተን እንዲፈሩ አደርጋለሁ፤ ስለ እናንተ በሰሙ ቊጥር ሁሉም በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ።’
የንጉሥ ሲሖን በእስራኤላውያን ድል መመታት
(ዘኍ. 21፥21-30)
26“ከዚህም በኋላ የሰላም መልእክት የያዙ መልእክተኞችን ከቅዴሞት በረሓ ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሲሖን እንዲህ ስል ላክሁ፤ 27‘በእናንተ አገር በኩል አልፈን እንድንሄድ ፍቀድልን፤ ከመንገዱ ሳንወጣና ወደ ቀኝም ወደ ግራም ሳንል በቀጥታ እንሄዳለን፤ 28ለምንበላው ምግብና ለምንጠጣው ውሃ ዋጋ እንከፍላለን፤ እኛ የምንፈልገው በአንተ አገር በኩል ማለፍ እንዲፈቀድልን ብቻ ነው። 29በኤዶም የሚኖሩ የዔሳው ዘሮችና በዔር የሚኖሩ የሞአብ ዘሮች በግዛታቸው በኩል እንድናልፍ እንደ ፈቀዱልን ሁሉ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረን እግዚአብሔር ወደሚያወርሰን ምድር እስክንገባ ድረስ በዚያ ለማለፍ ፍቀድልን።’
30“ነገር ግን ሲሖን ንጉሥ ሴዎን በእርሱ ግዛት ውስጥ አልፈን እንድንሄድ ባለመፍቀዱ፥ አሁን እንዳደረገው አምላካችሁ እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ሊሰጠው ስለ ፈቀደ ትዕቢተኛና እልኸኛ አደረገው።
31“ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ ‘ተመልከት እኔ ንጉሥ ሲሖንንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ፤ አሁን ድል በማድረግ ምድሩን ወርሰህ ስፈርበት።’ 32ንጉሥ ሲሖንም ያለውን ሰው ሁሉ አሰልፎ በያሐጽ ከተማ አጠገብ ከእኛ ጋር ለመዋጋት ወጣ፤ 33ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችን በእኛ እጅ ስለ ጣለው እርሱንና ልጆቹን፥ ያለውንም ሰው ሁሉ ገደልን። 34ወዲያውም እያንዳንዱን ከተማ ወረን አቃጠልነው፤ በነዚያ ከተሞች የነበሩትንም ሰዎች ወንዶችንና ሴቶችን፥ ሕፃናትንም ጭምር አንድ እንኳ በሕይወት ሳናስቀር ሁሉንም ደመሰስን። 35ከብቱን ወሰድን፤ ከተሞችንም በዘበዝን። 36በአርኖን ሸለቆ ጠረፍ ከምትገኘው ከአሮዔርና በሸለቆው ከሚገኘው ከተማ ጀምሮ እስከ ገለዓድ ድረስ እኛን ሊቋቋመን የሚችል ከተማ አልነበረም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉንም አሳልፎ ሰጠን። 37ነገር ግን ወደ ዐሞናውያን ግዛት አጠገብ ወይም ወደ ያቦቅ ወንዝ ዳርቻ ወይም ወደ ኮረብታማይቱ አገር ከተሞች ወይም እግዚአብሔር እንዳንደርስባቸው ወዳዘዘን እነዚህን ከመሳሰሉት አገሮች ወደ አንዲቱ እንኳ አልቀረብንም።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 2: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997