ኦሪት ዘዳግም 21
21
ገዳዩ ያልታወቀ የግድያ ወንጀል
1“እግዚአብሔር እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር በሜዳ ላይ ማን እንደ ገደለው ሳይታወቅ አንድ ሰው ተገድሎ ቢገኝ፤ 2በዚያን ጊዜ መሪዎችህና ዳኞችህ ሄደው አስከሬኑ ወድቆ ከተገኘበት ስፍራ አንሥተው ባቅራቢያ እስከምትገኘው እስከያንዳንዱ ከተማ ድረስ ርቀቱን ይለኩት፤ 3ከዚያም በኋላ አስከሬኑ ወድቆ ለተገኘበት ስፍራ ቅርብ ሆና የምትገኘው ከተማ መሪዎች ለሥራ ያልደረሰች፥ በጫንቃዋም ላይ ቀንበር ያልተጫነባት አንዲት ጊደር ይምረጡ፤ 4እርስዋንም ጨርሶ ወዳልታረሰና ምንም ተክል ወዳልተተከለበት፥ ወንዙም ወደማይደርቅበት ሸለቆ ይዘዋት ወርደው በዚያ አንገትዋን በመቈልመም ይስበሩት፤ 5እርሱን እንዲያገለግሉት፥ በእርሱ ስም እንዲባርኩ፥ የክርክርና የወንጀል ጉዳይ በእነርሱ እንዲወሰን አምላክህ እግዚአብሔር ካህናቱን የሌዊን ልጆች ስለ መረጣቸው ወደ አስከሬኑ ይቅረቡ። 6ከዚህም በኋላ የተገደለው ሰው አስከሬን ወድቆ ለተገኘበት ስፍራ አቅራቢያ የሆነችው የዚያች ከተማ መሪዎች በጊደርዋ ላይ እጃቸውን ይታጠቡ፤ 7እንዲህም ብለው መግለጫ ይስጡ፦ ‘እኛ ይህን ሰው አልገደልንም፤ ማን እንደ ገደለውም አላየንም፤ 8እግዚአብሔር ሆይ፥ ከግብጽ ምድር ዋጅተህ ያወጣሃቸውን ሕዝብህን እስራኤልን ይቅር በል፤ እኛንም ይቅር በለን፤ ስለዚህም ስለ ፈሰሰው የንጹሕ ሰው ደም በኀላፊነት ተጠያቂዎች አታድርገን።’ 9በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር ስለምታደርግ ስለ ንጹሑ ሰው ግድያ ወንጀል ተጠያቂ አትሆንም።
የጦር ምርኮኞች ስለ ሆኑ ሴቶች የተሰጠ መመሪያ
10“ጠላቶችህን ለመዋጋት ወጥተህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ እነርሱን አሳልፎ ሲሰጥህና ስትማርካቸው 11በእነርሱ መካከል ለጋብቻ የምትፈልጋት ውበት ያላት ሴት ታይ ይሆናል፤ 12ይህም ከሆነ፥ እርስዋን ወደ ቤትህ ወስደህ፥ ራስዋን ተላጭታ፥ ጥፍርዋን ተቈርጣ፥ 13ልብስዋን ትለውጥ፤ እርስዋም ከአንተ ጋር በቤትህ ተቀምጣ እስከ አንድ ወር ድረስ በጦርነት ስለሞቱት ወላጆችዋ ታልቅስ፤ ከዚያም በኋላ ሚስት አድርገህ ታገባታለህ። 14በኋላ ግን የማትፈልጋት ከሆንህ ነጻ ልትለቃት ትችላለህ፤ ከአንተ ጋር የጋብቻ ግንኙነት እንድትፈጽም ያስገደድሃት ስለ ሆንክ ባሪያ አድርገህ ልትሸጣት አይገባም።
የበኲር ልጅ ሕጋዊ የመውረስ መብት
15“አንድ ሰው ሁለት ሚስቶችን አግብቶ አንደኛይቱን አፍቅሮ ሌላይቱን ባያፈቅርና ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ቢወልዱለት፥ ምናልባት የመጀመሪያው ልጅ የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ ቢሆን፥ 16ታዲያ፥ ያ ሰው ሀብቱንና ንብረቱን ለልጆቹ በሚያካፍልበት ጊዜ ለበኲር ልጁ ሊሰጥ የሚገባውን ድርሻ በተለይ ከሚያፈቅራት ሚስቱ ለተወለደው ልጁ በመስጠት አድልዎ ማድረግ አይገባውም፤ 17ከማያፈቅራት ሚስቱ የተወለደ ቢሆንም እንኳ ለበኲር ልጁ የሚሰጠው ድርሻ ከሌሎቹ የነፍስ ወከፍ ድርሻ በእጥፍ ከፍ ያለ መሆን አለበት፤ ስለዚህም ያ ሰው ልጁ በመጀመሪያ በመወለዱ በኲር መሆኑን ተረድቶ የብኲርና ድርሻውን ሊሰጠው ይገባል።
ለወላጆቹ ስለማይታዘዝ ልጅ የተሰጠ መመሪያ
18“አንድ ሰው ምንም ቢቀጡት የማይመለስ እልኸኛና ዐመፀኛ ሆኖ፥ ለወላጆቹ የማይታዘዝ ልጅ ይኖረው ይሆናል፤ 19ይህም ከሆነ ወላጆቹ በሚኖሩባት ከተማ አደባባይ ወዳሉት መሪዎች ዘንድ አምጥተው ለፍርድ ያቁሙት፤ 20በሚያስፈርዱበትም ጊዜ እንዲህ ይበሉ፥ ‘እነሆ፥ ይህ ልጃችን እልኸኛና ዐመፀኛ ነው፤ ለእኛ መታዘዝን እምቢ ብሎአል፤ ሰካራምና ገንዘብ አባካኝ ሆኖብናል፤’ 21የከተማይቱም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ወግረው ይግደሉት፤ በዚህም ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ታስወግዳላችሁ፤ በእስራኤልም የሚኖር ሁሉ ይህን ሁኔታ ሰምቶ ይፈራል።
ልዩ ልዩ ሕጎች
22“አንድ ሰው በሠራው ከባድ ወንጀል ምክንያት በእንጨት በስቅላት ቢቀጣ፥ 23በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር የተረገመ ስለ ሆነ አስከሬኑ በእንጨት ላይ ተሰቅሎ አይደር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በርስትነት የሚሰጥህን ምድር እንዳታረክስ አስከሬኑን በዚያኑ ዕለት ቅበረው። #ገላ. 3፥13።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 21: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997