ኦሪት ዘዳግም 26
26
በመከር ወራት የሚቀርብ በኲራትና ዐሥራት
1“እግዚአብሔር አምላክህ እንድትወርሳት ወደሚሰጥህ ምድር ገብተህ በምትወርሳትና ተደላድለህ በምትቀመጥባት ጊዜ፥ 2ከሚሰጥህ ምድር ከምታመርተው ምርት በኲራቱን በቅርጫት በማድረግ እግዚአብሔር አምላክህ ለስሙ መጠሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ቦታ ውሰድ፤ #ዘፀ. 23፥19። 3በዚያን ወራት በሥልጣን ላይ ወዳለው ካህን ሄደህ እንዲህ በለው፦ ‘እኔ ዛሬ አስቀድሞ አምላክህ እግዚአብሔር ለእኛ ለልጆቻቸው እንዲሰጠን ለአባቶቻችን በመሐላ ቃል ወደገባላቸው ምድር መግባቴን አረጋግጣለሁ።’
4“ካህኑም ቅርጫቱን ተቀብሎ በአምላክህ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ለፊት ያስቀምጠዋል፤ 5ከዚያ በኋላ በእግዚአብሔር አምላክህ ፊት ይህን መግለጫ ስጥ፦ ‘አባቴ ከቦታ ወደ ቦታ በመዞር የሚኖር ሶርያዊ ነበር፤ ጥቂት ቤተሰብ ይዞ ወደ ግብጽ በመውረድ መጻተኛ ሆኖ ኖረ፤ ጥቂት የነበረው ታላቅ፥ ኀያል፥ ብዙ ሕዝብ ሆነ። 6ግብጻውያን ግን አስጨነቁን፤ አዋረዱን፥ ባርያዎችም ሆነን እንድናገለግል አስገደዱን። 7እኛም ወደ አባቶቻችን አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ጩኸታችንን ሰምቶ ሥቃያችንን፥ ድካማችንንና መጨቈናችንን ተመለከተ። 8እግዚአብሔርም በታላቅ ኀይሉና ሥልጣኑ ታላቅ ፍርሀትን በማሳደር፥ ሥራዎችን ተአምራትንና ድንቅ ሥራዎችን በማሳየት ከግብጽ አወጣን። 9ወደዚህም አምጥቶ በማርና በወተት የበለጸገችውን ይህችን ለም ምድር አወረሰን። 10ስለዚህም እነሆ፥ እኔ እርሱ ከሰጠኝ መጀመሪያ የሆነውን በኲራት አምጥቼአለሁ።’
“ከዚህም ቀጥሎ ቅርጫቱን በእግዚአብሔር ፊት በማኖር ስገድ፤ 11ለአንተና ለቤተሰብህም እግዚአብሔር ባደረገላችሁ መልካም ነገር ሁሉ ደስ ብሎአችሁ አመስግኑ፤ ሌዋውያንና ከእናንተ ጋር የሚኖሩ መጻተኞች በዚህ የምስጋና ሥርዓት አፈጻጸም ላይ አብረው ይገኙ።
12“በሦስተኛው ዓመት ማለት ዐሥራት በምታወጣት ዓመት ዐሥራትህን ሁሉ አጠናቅቀህ ከሰበሰብክ በኋላ በከተማህ ለሚገኙ ለሌዋውያን፥ ለመጻተኞች፥ ለሙት ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ሰጥተህ ጠግበው እንዲበሉ አድርግ። #ዘዳ. 14፥28-29። 13ከዚያም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ በል፦ ‘ከቤቴ የተቀደሰውን ድርሻ ወስጄ ባዘዝከን ትእዛዞች ሁሉ መሠረት ለሌዋውያን፥ ለመጻተኞች፥ ለሙት ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ሰጥቼአለሁ፤ ከትእዛዞችህም አልተላለፍኩም፤ የዘነጋሁትም ነገር የለም። 14በሞት ሐዘን ጊዜ ከእርሱ አልበላሁም፤ ንጹሕ ባልሆንኩበት ጊዜ ከእርሱ ምንም አላነሣሁም፤ ስለ ሞተ ሰው ለሚቀርብ መባ ከእርሱ ምንም አላቀረብኩም፤ ባዘዝከኝ መሠረት የአንተን የአምላኬን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ፈጽሜአለሁ። 15በሰማይ ካለው ቅዱስ መኖሪያህ ሆነህ ወደ ታች ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንም ባርክ፤ ለቀድሞ አባቶቻችን በገባኸው ቃል መሠረት የሰጠኸንን በማርና በወተት የበለጸገችውን ለም ምድር ባርክ።’
ለእግዚአብሔር የተለየ ሕዝብ
16“እግዚአብሔር አምላክህ ሕጎችንና ሥርዓቶችን እንድትጠብቅ እነሆ፥ ዛሬ ያዝሃል፤ ስለዚህ በፍጹም ልብህና ነፍስህ ጠብቃቸው። 17እግዚአብሔር አምላክህ መሆኑንና በሕጉም የምትመራ መሆንህን ዛሬ አንተ አረጋግጠሃል፤ ሥርዓቱን፥ ትእዛዞቹንና ሕጎቹን ለመጠበቅና ታዛዥ ለመሆን ቃል ገብተሃል፤ 18ስለዚህም እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት እነሆ፥ ዛሬ ለእርሱ የተለየህ ውድ ሕዝብ አድርጎ ተቀብሎሃል፤ ትእዛዞቹንም ሁሉ እንድትፈጽም ያዝሃል፤ #ዘፀ. 19፥5፤ ዘዳ. 4፥20፤ 7፥6፤ 14፥2፤ ቲቶ 2፥14፤ 2ጴጥ. 2፥9። 19ይህን ብታደርግ ከፈጠራቸው ሕዝቦች ሁሉ በላይ በምስጋና፥ በስም፥ በክብርም ከፍ ሊያደርግህና በሰጠውም ተስፋ መሠረት ለእርሱ የተለየህ ሕዝብ እንደሚያደርግህ ነግሮሃል።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 26: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997