ኦሪት ዘዳግም 29
29
እግዚአብሔር በሞአብ ምድር ለእስራኤል የሰጠው ቃል ኪዳን
1እግዚአብሔር በሲና ካደረገው ቃል ኪዳን በተጨማሪ በሞአብ ምድር ከእስራኤል ሕዝብ ጋር እንዲያደርግ ሙሴን ያዘዘው ተጨማሪ ቃል ኪዳን የሚከተለው ነው፦
2ሙሴም የእስራኤልን ሕዝብ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እግዚአብሔር በግብጽ ንጉሥ፥ በመኳንንቱና በመላ ሀገሪቱ ላይ ያደረገውን ሁሉ፥ 3በእነርሱ ላይ ያደረሰባቸውን አሠቃቂ መቅሠፍት፥ የፈጸመውንም ተአምራትና ድንቅ ሥራ ሁሉ ራሳችሁ በዐይናችሁ አይታችኋል። 4እግዚአብሔር ግን እስከ ዛሬይቱ ዕለት ድረስ ያለፋችሁበትን ሁኔታ የምታዩበት ዐይን፥ የምትሰሙበት ጆሮ፥ የምታስተውሉበት አእምሮ አልሰጣችሁም። 5አርባ ዓመት ሙሉ በበረሓ ስመራችሁ ልብሳችሁ አላረጀም፤ ጫማችሁም አላለቀም። 6አምላካችሁ እግዚአብሔር መሆኑን ታውቁ ዘንድ እንጀራ አልበላችሁም ወይን ወይም ጠንካራ መጠጥ አልጠጣችሁም። 7ወደዚህም ስፍራ በደረስን ጊዜ፥ የሐሴቦን ንጉሥ ሲሖንና የባሳን ንጉሥ ዖግ ሊወጉን መጥተውብን ነበር፤ ነገር ግን እኛ ድል አደረግናቸው፤ #ዘኍ. 21፥21-35። 8ምድራቸውንም ወርሰን ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች እንዲሁም ለእኩሌታ የምናሴ ነገድ ርስት እንዲሆን አከፋፍለን ሰጥተናል፤ #ዘኍ. 32፥33። 9ስለዚህም የምትሠሩት ነገር ሁሉ ይሳካላችሁ ዘንድ የዚህን ቃል ኪዳን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ፈጽሙ።
10-11“እነሆ፥ ዛሬ እናንተ የየነገድ መሪዎቻችሁ፥ ሽማግሌዎቻችሁ፥ ሹሞቻችሁ፥ ሌሎችም የእስራኤል ወንዶች ሁሉና ልጆቻችሁ፥ ሴቶቻችሁ፥ በእናንተ ሰፈር ሆነው እንጨት የሚለቅሙላችሁና ውሃ የሚቀዱላችሁ መጻተኞች፥ ሁላችሁም በእግዚአብሔር አምላካችሁ ፊት ቆማችኋል። 12የቆማችሁትም ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት ነው፤ ይህም ቃል ኪዳን እግዚአብሔር አምላካችሁ ዛሬ ለእናንተ በመሐላ ያረጋገጠው ነው። 13እግዚአብሔር ይህን ያደረገው በሰጣችሁ ተስፋና ለአባቶቻችሁም ለአብርሃም፥ ለይስሐቅ፥ ለያዕቆብ በመሐላ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት እናንተን የራሱ ሕዝብ አድርጎ ሊመሠርታችሁ ነው። 14እግዚአብሔር ይህን ሁሉ በመሐላ የጸና ቃል ኪዳን የሚያደርገውም ከእናንተ ጋር ብቻ አይደለም። 15እርሱ ይህን ቃል ኪዳን የሚገባው ዛሬ በዚህ ስፍራ በፊቱ ከቆምነው ከእኛ ሁሉና ዛሬም ከእኛ ጋር እዚህ ከሌሉት ጋር ነው።
16“በግብጽ ምድር እንዴት እንደ ኖርንና ባለፋችሁባቸውም ሕዝቦች መካከል እንዴት እንደ መጣን ታውቃላችሁ። 17በመካከላቸው አጸያፊ የሆነውን፥ የእንጨት፥ የድንጋይ፥ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን አይታችኋል። 18በዚህ ከቆማችሁት መካከል ማንም ወንድ ወይም ሴት፥ ቤተሰብ ወይም ነገድ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ፈቀቅ በማለት የሌሎችን ሕዝቦች አማልክት የሚከተል እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ በመካከላችሁ እንደዚህ ያለ መርዘኛና መራራ የሆነ ሥራ የሚሠራ አይኑር፤ #ዕብ. 12፥15። 19እንደዚህ ያለው ሰው የዚህን ርግማን ቃላት ሰምቶ ምንም እንኳ በራሴ መንገድ ብቀጥል እኔ እድናለሁ ብሎ በልቡ ቢያስብ በደጎችና በክፉዎች ሰዎች ላይ ጥፋትን ያመጣል። 20እግዚአብሔር ለእንደዚህ ያለው ሰው ይቅርታ አያደርግም፤ ይልቁንም የእግዚአብሔር ቊጣና ቅናት በእርሱ ላይ እንደ እሳት ይነዳል፤ እግዚአብሔርም እንደዚህ ያለውን ሰው ፈጽሞ እስኪደመስሰው ድረስ በዚህ መጽሐፍ የተጻፉት መቅሠፍቶች ሁሉ ይወርዱበታል። 21እግዚአብሔር እንደዚህ ያለውን ሰው በዚህ የሕግ መጽሐፍ በተጻፈው የእርግማን ቃል ኪዳን መሠረት ከእስራኤል ነገዶች መካከል አውጥቶ ያጠፋዋል።
22“በሚመጡት ትውልዶች፥ ዘሮቻችሁና ከሩቅ አገር የመጡ የውጪ አገር ሰዎች እግዚአብሔር በምድራችሁ ላይ ያመጣውን ጥፋትና በሽታ ያያሉ። 23ምድሪቱም ሁሉ በዲንና በጨው ትሸፈናለች፤ ምንም ነገር አይተከልባትም፤ ምንም ነገር አታበቅልም፤ እግዚአብሔር በኀይለኛ ቊጣው እንደ ደመሰሳቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ጺባዮ ትሆናለች። #ዘፍ. 19፥24-25። 24በዚያን ጊዜ የመላው ዓለም ሕዝብ እንዲህ ሲል ይጠይቃል፤ ‘እግዚአብሔር በዚህች ምድር ላይ ይህን ሁሉ ስለምን አደረገ? ለብርቱ ቊጣውስ ምክንያት የሆነው ነገር ምንድን ነው?’ 25መልሱም፦ ‘እነርሱ የቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን በማፍረሳቸው ነው። 26እነርሱ ከዚያ በፊት ሰግደውላቸው የማያውቁትንና እግዚአብሔርም እንዳይሰግዱላቸው የከለከላቸውን ባዕዳን አማልክትን ተከተሉ። 27ስለዚህም እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ተቈጥቶ በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ይህን መቅሠፍት ሁሉ በምድራቸው ላይ አወረደ። 28እግዚአብሔርም በብርቱ ተቈጣ፤ ከብርቱ ቊጣውም የተነሣ ከምድራቸው ነቃቅሎ ወደ ባዕድ አገር እንዲሰደዱ አደረጋቸው። ስለዚህም እነሆ፥ ዛሬም በዚያው ይገኛሉ።’
29“እግዚአብሔር አምላካችን ምሥጢር ያደረጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ፤ የተገለጡ ነገሮች ግን እኛና ልጆቻችን ልንጠብቃቸው የሚገባን የሕጉ ቃሎች ሁሉ ናቸው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 29: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997