ኦሪት ዘዳግም 32
32
1ሰማይ ሆይ፥ የምናገረውን አድምጥ፤
ምድርም ከአፌ የሚወጣውን ቃል ትስማ፤
2ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይዝነብ፤
ንግግሬም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤
በሣር ላይ እንደ ለስላሳ ዝናብ፥
በቡቃያም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥
3የእግዚአብሔርን ስም ዐውጃለሁ፤
የአምላካችንን ታላቅነት ተናገሩ።
4“እርሱ ምሽጋችን ነው፤ ሥራዎቹም ፍጹሞች ናቸው፤
መንገዶቹም ሁሉ የቀኑ ናቸው፤
የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፥
እርሱም ቀጥተኛና እውነተኛ ነው።
5በእርሱ ፊት የረከሰ ጠባያቸውን አሳዩ፤
በዚህም የእርሱ ልጆች አለመሆናቸው ይታወቃል፤
እነርሱ የተበላሹና ጠማማ ትውልድ ናቸው።
6እናንተ ሞኞችና ኅሊና ቢሶች፥
የእግዚአብሔርን ዋጋ የምትከፍሉ በዚህ ዐይነት ነውን?
እርሱ የፈጠራችሁ አባታችሁ አይደለምን?
የመሠረታችሁስ እርሱ አይደለምን?
7“የቀድሞውን ዘመን አስታውስ፤
ከዘመናት በፊት የነበረውን አስተውል፤
አባትህን ጠይቅ እርሱም ይነግርሃል፤
ሽማግሌዎችህን ጠይቅ እነርሱም ይተርኩልሃል።
8ልዑል እግዚአብሔር ለሕዝቡ ርስታቸውን ባከፋፈለ ጊዜ፥
የሰውን ዘር በለያየ ጊዜ፥
እንደ እስራኤል ልጆች ቊጥር ብዛት፥
ለሕዝቡ ድንበርን ሠራላቸው። #ሐ.ሥ. 17፥26።
9እስራኤል የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፤
ያዕቆብም አንጡራ ሀብቱ ነው።
10“በነፋሻማ ባዶ በረሓ
በምድረ በዳ አገኘው፤
መከታ ሆነለት፤ ጠበቀውም፤
እንደ ዐይን ብሌኑም ተንከባከበው።
11በጫጩቶችዋ ላይ እንደምታንዣብብ፥
ጎጆዋን እንደምትጠብቅ ንስር፥
እርሱን ለመያዝ ክንፎቹን ይዘረጋል፤
በክንፎቹም ጫፍ ይደግፈዋል።
12እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤
ባዕድ አምላክ ከእርሱ ጋር አልነበረም።
13“በከፍተኛ ቦታ ላይ አኖረው፤
የምድሩንም ምርት መገበው፤
ከቋጥኝ የተገኘውን ማርና
ከድንጋያማ መሬት ከበቀለው ወይራ የተገኘውን ዘይት መገበው።
14ከከብቶች፥ ከበጎችና ከፍየሎች መንጋ በሚገኝ ወተትና ዕርጎ፥ ከባሳን በሚገኙ ምርጥ ጠቦቶች፥ አውራ በጎች፥ ኰርማዎችና ፍየሎች ጮማ ሥጋ ከምርጥ ስንዴ ዳቦ ጋር መገባቸው። እናንተም ሕዝቦቹ ከቀይ ወይን ዘለላ ጭማቂ የወይን ጠጅ ጠጣችሁ።
15“እስራኤላውያንም ወፈሩ፤ ዐመፁም።
በጣም በልተው ወፈሩ፤ ሰቡ፤
የፈጠራቸውንም አምላክ ተዉ፤
መጠጊያ አዳኛቸውን አቃለሉ።
16እግዚአብሔርን በጣዖት አምልኮ አስቀኑት፤
በሚያደርጉትም ክፉ ነገር ሁሉ አስቈጡት።
17ከዚህ በፊት ላላወቁአቸው፥
በቅርቡ አዲስ ለመጡ፥
ለአምላክ ሳይሆን ለአጋንንት
የቀድሞ አባቶቻቸው ላላመለኩአቸው አማልክት
መሥዋዕት አቀረቡ። #1ቆሮ. 10፥20።
18ያስገኛቸውን አምላክ ተዉ፤
የፈጠራቸውንም እግዚአብሔር ረሱ።
19“ሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው ስላስቈጡት
እግዚአብሔር አስወገዳቸው።
20‘ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤
መጨረሻቸው ምን እንደሚሆን አያለሁ፤
እነርሱ የተበላሸ ትውልድ
እምነት የሚጣልባቸው ልጆች አይደሉም’ አለ።
21እውነተኛ ባልሆኑ አማልክት አስቀንተውኛል፤
ዋጋቢስ በሆኑ ጣዖቶቻቸው አስቈጥተውኛል፤
በተናቀ ሕዝብ አስቀናቸዋለሁ፤
በማያስተውል ሕዝብ አስቈጣቸዋለሁ። #1ቆሮ. 10፥22፤ ሮም 10፥19።
22በቊጣዬ እሳት ይቀጣጠላል፤
እስከ ሲኦል ጥልቀት ድረስ ይነዳል፤
ምድርንና ምርቱን ይበላል።
ቃጠሎውም እስከ ተራራዎች መሠረት ድረስ ያቃጥላል።
23“ተከታታይ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤
ፍላጻዎቼን ሁሉ በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ።
24የሚጨርስ ራብ በእነርሱ ላይ እልካለሁ፤
በወረርሽኝና በመቅሠፍት ያልቃሉ፤
ተናካሽ አውሬዎችንና
መርዘኛ ተናዳፊ እባቦችን እሰድባቸዋለሁ።
25በየመንገዱ ላይ ጦርነት ልጅ አልባ ያደርጋቸዋል፤
በቤት ውስጥ ፍርሀት ይሰፍናል፤
ወጣት ወንዶችና ሴቶች፥
ሕፃናትና ሽማግሌዎችም ያልቃሉ።
26እኔ ፈጽሜ እደመስሳቸዋለሁ፤
ከዚያም በኋላ የሚያስታውሳቸው አይኖርም፤
27ነገር ግን ጠላቶቻቸው
‘አሸናፊዎች እኛ ነን እንጂ
እግዚአብሔር አይደለም’ ብለው በመታበይ
ያስቈጡኛል ብዬ አስባለሁ።
28“የእስራኤል ሕዝብ አእምሮ ቢሶች ናቸው፤
አያስተውሉምም።
29ምነው ብልኆች ሆነው ይህን ባስተዋሉና፤
መጨረሻውንም በተገነዘቡ ነበር!
30ፈጣሪአቸው አሳልፎ ካልሰጣቸውና
አምላካቸውም ካልተዋቸው በቀር
እንዴት አንዱ ሺሁን ያሳድዳል?
ወይም ሁለቱ ዐሥር ሺሁን ያባርራሉ?
31ጠላቶቻችን እንኳ እንደሚስማሙበት
የእነርሱ አምላክ እንደ እኛ አምላክ አይደለም።
32ጠላቶቻችን እንደ ሰዶምና ገሞራ የረከሱ ናቸው፤
እነርሱም መራራና መርዘኛ ፍሬ እንደሚሰጥ የወይን ተክል ናቸው።
33ወይናቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤
እንደ ክፉ እፉኝትም መርዝ ነው።
34“ጠላቶቻችን የፈጸሙት በደል
በእግዚአብሔር መዝገብ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።
35የምበቀል እኔ ነኝ
ለሁሉም እንደየሥራቸው እከፍላለሁ፤
የጥፋታቸው ቀን ስለ ደረሰ ይሰናከላሉ፤
ፈጥነውም ይጠፋሉ። #ሮም 12፥19፤ ዕብ. 10፥30።
36ኀይል ማጣታቸውን ሲያይ፥
እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ ይራራል፤
ነጻም፥ ባሪያም ሳይለይ
ጌታ ለሕዝቡ ይፈርዳል። #መዝ. 135፥14።
37እግዚአብሔርም ሕዝቡን እንዲህ ብሎ ጠየቀ፦
‘የሚተማመኑባቸው አማልክቶቻቸው የት አሉ?
ከዚያም የተማመኑበት አለት
አማልክቶቻቸውስ የት አሉ’ ይላል።
38የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፥
የወይን ቊርባናቸውን የጠጡ አማልክታቸው
ተነሥተው ይርዱአቸው፤
መጠጊያም ይሁኑአቸው።
39“አምላክ እኔ ብቻ መሆኔን ዕወቁ፤
ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤
የምገድልም፥ ሕይወትንም የምሰጥ እኔ ነኝ፤
አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም
ከእጄ ማንም ሊያድን አይችልም
40እጄን ወደ ሰማይ ዘርግቼ
እንዲህ በማለት እምላለሁ፦ ‘እኔ ለዘለዓለም ሕያው ነኝ፤
41የሚያንጸባርቅ ሰይፌን እስለዋለሁ፤
እኔም ፍርድን እፈርዳለሁ፤
ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፤
ለሚጠሉኝም ዋጋቸውን እሰጣለሁ።
42ከተገደሉትና ከተማረኩት
ከጠላት መሪዎችም ራስ ደም
ፍላጻዎቼን አሰክራለሁ፤
ሰይፌ የጠላትን ሥጋ ይቈራርጣል።’
43“ሕዝቦች ሆይ፥ እግዚአብሔር የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላል፤
ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋል፤
የሚጠሉትን ቀጥቶ የሕዝቡን ኃጢአት ያስተሰርያል፤
የምድሪቱን ርኲሰት ያነጻል
ስለዚህ ከእርሱ ሕዝብ ጋር ደስ ይበላችሁ።” #ሮም 15፥10፤ ራዕ. 19፥2።
44ሙሴና የነዌ ልጅ ኢያሱ ሕዝቡ እንደሚሰማ አድርገው ይህን መዝሙር አነበቡ።
ሙሴ የሰጠው የመጨረሻ ምክር
45ሙሴ እነዚህን ቃላት ሁሉ ለሕዝቡ አሰምቶ ከጨረሰ በኋላ፥ 46እርሱም እንዲህ አለ፦ “የዚህን ሕግ ቃላት በጥንቃቄ መጠበቅ ይችሉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዙ እኔ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን የምሰጣችሁን ቃላት ሁሉ አስተውሉ። 47ይህ ሕግ የባዶ ቃላት ቅንብር አይደለም፤ እርሱ የሕይወታችሁ መሠረት ነው፤ ስለዚህ ለዚህ ቃል ታዛዦች ሁኑ፤ ይህን ብታደርጉ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሱአት ምድር ለረዥም ዘመን ትኖራላችሁ።”
ስለ ሙሴ ሞት በቅድሚያ መነገሩ
48በዚያኑ ቀን እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ 49“በሞአብ ምድር በኢያሪኮ ከተማ ፊት ለፊት ወደሚገኙት የዐባሪም ተራራዎች ሂድ፤ ወደ ነቦ ተራራም ውጣ፤ ከዚያም ለእስራኤል ሕዝብ የማወርሳትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት፤ 50ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ ሞቶ ወደ ወገኖቹ እንደ ተቀላቀለ አንተም በዚሁ በነቦ ተራራ ላይ ሞተህ ከወገኖችህ ጋር ትቀላቀላለህ፤ 51እናንተ ሁለታችሁም በእስራኤል ሕዝብ ፊት ለእኔ ታማኞች ሆናችሁ አልተገኛችሁም፤ በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ከተማ አጠገብ በምትገኘው በመሪባ ውሃ ምንጮች አጠገብ በነበራችሁበት ጊዜ በእስራኤል ሕዝብ ፊት እንድከበር አላደረጋችሁም። 52ከሩቅ ሆነህ ምድሪቱን ባሻገር ታያለህ፤ ነገር ግን እኔ ለእስራኤል ልጆች ወደማወርሳት ወደዚያች ምድር አትገባም።” #ዘኍ. 27፥12-14፤ ዘዳ. 3፥23-27።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 32: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
ኦሪት ዘዳግም 32
32
1ሰማይ ሆይ፥ የምናገረውን አድምጥ፤
ምድርም ከአፌ የሚወጣውን ቃል ትስማ፤
2ትምህርቴ እንደ ዝናብ ይዝነብ፤
ንግግሬም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤
በሣር ላይ እንደ ለስላሳ ዝናብ፥
በቡቃያም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥
3የእግዚአብሔርን ስም ዐውጃለሁ፤
የአምላካችንን ታላቅነት ተናገሩ።
4“እርሱ ምሽጋችን ነው፤ ሥራዎቹም ፍጹሞች ናቸው፤
መንገዶቹም ሁሉ የቀኑ ናቸው፤
የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፥
እርሱም ቀጥተኛና እውነተኛ ነው።
5በእርሱ ፊት የረከሰ ጠባያቸውን አሳዩ፤
በዚህም የእርሱ ልጆች አለመሆናቸው ይታወቃል፤
እነርሱ የተበላሹና ጠማማ ትውልድ ናቸው።
6እናንተ ሞኞችና ኅሊና ቢሶች፥
የእግዚአብሔርን ዋጋ የምትከፍሉ በዚህ ዐይነት ነውን?
እርሱ የፈጠራችሁ አባታችሁ አይደለምን?
የመሠረታችሁስ እርሱ አይደለምን?
7“የቀድሞውን ዘመን አስታውስ፤
ከዘመናት በፊት የነበረውን አስተውል፤
አባትህን ጠይቅ እርሱም ይነግርሃል፤
ሽማግሌዎችህን ጠይቅ እነርሱም ይተርኩልሃል።
8ልዑል እግዚአብሔር ለሕዝቡ ርስታቸውን ባከፋፈለ ጊዜ፥
የሰውን ዘር በለያየ ጊዜ፥
እንደ እስራኤል ልጆች ቊጥር ብዛት፥
ለሕዝቡ ድንበርን ሠራላቸው። #ሐ.ሥ. 17፥26።
9እስራኤል የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፤
ያዕቆብም አንጡራ ሀብቱ ነው።
10“በነፋሻማ ባዶ በረሓ
በምድረ በዳ አገኘው፤
መከታ ሆነለት፤ ጠበቀውም፤
እንደ ዐይን ብሌኑም ተንከባከበው።
11በጫጩቶችዋ ላይ እንደምታንዣብብ፥
ጎጆዋን እንደምትጠብቅ ንስር፥
እርሱን ለመያዝ ክንፎቹን ይዘረጋል፤
በክንፎቹም ጫፍ ይደግፈዋል።
12እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤
ባዕድ አምላክ ከእርሱ ጋር አልነበረም።
13“በከፍተኛ ቦታ ላይ አኖረው፤
የምድሩንም ምርት መገበው፤
ከቋጥኝ የተገኘውን ማርና
ከድንጋያማ መሬት ከበቀለው ወይራ የተገኘውን ዘይት መገበው።
14ከከብቶች፥ ከበጎችና ከፍየሎች መንጋ በሚገኝ ወተትና ዕርጎ፥ ከባሳን በሚገኙ ምርጥ ጠቦቶች፥ አውራ በጎች፥ ኰርማዎችና ፍየሎች ጮማ ሥጋ ከምርጥ ስንዴ ዳቦ ጋር መገባቸው። እናንተም ሕዝቦቹ ከቀይ ወይን ዘለላ ጭማቂ የወይን ጠጅ ጠጣችሁ።
15“እስራኤላውያንም ወፈሩ፤ ዐመፁም።
በጣም በልተው ወፈሩ፤ ሰቡ፤
የፈጠራቸውንም አምላክ ተዉ፤
መጠጊያ አዳኛቸውን አቃለሉ።
16እግዚአብሔርን በጣዖት አምልኮ አስቀኑት፤
በሚያደርጉትም ክፉ ነገር ሁሉ አስቈጡት።
17ከዚህ በፊት ላላወቁአቸው፥
በቅርቡ አዲስ ለመጡ፥
ለአምላክ ሳይሆን ለአጋንንት
የቀድሞ አባቶቻቸው ላላመለኩአቸው አማልክት
መሥዋዕት አቀረቡ። #1ቆሮ. 10፥20።
18ያስገኛቸውን አምላክ ተዉ፤
የፈጠራቸውንም እግዚአብሔር ረሱ።
19“ሴቶችና ወንዶች ልጆቻቸው ስላስቈጡት
እግዚአብሔር አስወገዳቸው።
20‘ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤
መጨረሻቸው ምን እንደሚሆን አያለሁ፤
እነርሱ የተበላሸ ትውልድ
እምነት የሚጣልባቸው ልጆች አይደሉም’ አለ።
21እውነተኛ ባልሆኑ አማልክት አስቀንተውኛል፤
ዋጋቢስ በሆኑ ጣዖቶቻቸው አስቈጥተውኛል፤
በተናቀ ሕዝብ አስቀናቸዋለሁ፤
በማያስተውል ሕዝብ አስቈጣቸዋለሁ። #1ቆሮ. 10፥22፤ ሮም 10፥19።
22በቊጣዬ እሳት ይቀጣጠላል፤
እስከ ሲኦል ጥልቀት ድረስ ይነዳል፤
ምድርንና ምርቱን ይበላል።
ቃጠሎውም እስከ ተራራዎች መሠረት ድረስ ያቃጥላል።
23“ተከታታይ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤
ፍላጻዎቼን ሁሉ በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ።
24የሚጨርስ ራብ በእነርሱ ላይ እልካለሁ፤
በወረርሽኝና በመቅሠፍት ያልቃሉ፤
ተናካሽ አውሬዎችንና
መርዘኛ ተናዳፊ እባቦችን እሰድባቸዋለሁ።
25በየመንገዱ ላይ ጦርነት ልጅ አልባ ያደርጋቸዋል፤
በቤት ውስጥ ፍርሀት ይሰፍናል፤
ወጣት ወንዶችና ሴቶች፥
ሕፃናትና ሽማግሌዎችም ያልቃሉ።
26እኔ ፈጽሜ እደመስሳቸዋለሁ፤
ከዚያም በኋላ የሚያስታውሳቸው አይኖርም፤
27ነገር ግን ጠላቶቻቸው
‘አሸናፊዎች እኛ ነን እንጂ
እግዚአብሔር አይደለም’ ብለው በመታበይ
ያስቈጡኛል ብዬ አስባለሁ።
28“የእስራኤል ሕዝብ አእምሮ ቢሶች ናቸው፤
አያስተውሉምም።
29ምነው ብልኆች ሆነው ይህን ባስተዋሉና፤
መጨረሻውንም በተገነዘቡ ነበር!
30ፈጣሪአቸው አሳልፎ ካልሰጣቸውና
አምላካቸውም ካልተዋቸው በቀር
እንዴት አንዱ ሺሁን ያሳድዳል?
ወይም ሁለቱ ዐሥር ሺሁን ያባርራሉ?
31ጠላቶቻችን እንኳ እንደሚስማሙበት
የእነርሱ አምላክ እንደ እኛ አምላክ አይደለም።
32ጠላቶቻችን እንደ ሰዶምና ገሞራ የረከሱ ናቸው፤
እነርሱም መራራና መርዘኛ ፍሬ እንደሚሰጥ የወይን ተክል ናቸው።
33ወይናቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፤
እንደ ክፉ እፉኝትም መርዝ ነው።
34“ጠላቶቻችን የፈጸሙት በደል
በእግዚአብሔር መዝገብ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል።
35የምበቀል እኔ ነኝ
ለሁሉም እንደየሥራቸው እከፍላለሁ፤
የጥፋታቸው ቀን ስለ ደረሰ ይሰናከላሉ፤
ፈጥነውም ይጠፋሉ። #ሮም 12፥19፤ ዕብ. 10፥30።
36ኀይል ማጣታቸውን ሲያይ፥
እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ ይራራል፤
ነጻም፥ ባሪያም ሳይለይ
ጌታ ለሕዝቡ ይፈርዳል። #መዝ. 135፥14።
37እግዚአብሔርም ሕዝቡን እንዲህ ብሎ ጠየቀ፦
‘የሚተማመኑባቸው አማልክቶቻቸው የት አሉ?
ከዚያም የተማመኑበት አለት
አማልክቶቻቸውስ የት አሉ’ ይላል።
38የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፥
የወይን ቊርባናቸውን የጠጡ አማልክታቸው
ተነሥተው ይርዱአቸው፤
መጠጊያም ይሁኑአቸው።
39“አምላክ እኔ ብቻ መሆኔን ዕወቁ፤
ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤
የምገድልም፥ ሕይወትንም የምሰጥ እኔ ነኝ፤
አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም
ከእጄ ማንም ሊያድን አይችልም
40እጄን ወደ ሰማይ ዘርግቼ
እንዲህ በማለት እምላለሁ፦ ‘እኔ ለዘለዓለም ሕያው ነኝ፤
41የሚያንጸባርቅ ሰይፌን እስለዋለሁ፤
እኔም ፍርድን እፈርዳለሁ፤
ጠላቶቼንም እበቀላለሁ፤
ለሚጠሉኝም ዋጋቸውን እሰጣለሁ።
42ከተገደሉትና ከተማረኩት
ከጠላት መሪዎችም ራስ ደም
ፍላጻዎቼን አሰክራለሁ፤
ሰይፌ የጠላትን ሥጋ ይቈራርጣል።’
43“ሕዝቦች ሆይ፥ እግዚአብሔር የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላል፤
ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋል፤
የሚጠሉትን ቀጥቶ የሕዝቡን ኃጢአት ያስተሰርያል፤
የምድሪቱን ርኲሰት ያነጻል
ስለዚህ ከእርሱ ሕዝብ ጋር ደስ ይበላችሁ።” #ሮም 15፥10፤ ራዕ. 19፥2።
44ሙሴና የነዌ ልጅ ኢያሱ ሕዝቡ እንደሚሰማ አድርገው ይህን መዝሙር አነበቡ።
ሙሴ የሰጠው የመጨረሻ ምክር
45ሙሴ እነዚህን ቃላት ሁሉ ለሕዝቡ አሰምቶ ከጨረሰ በኋላ፥ 46እርሱም እንዲህ አለ፦ “የዚህን ሕግ ቃላት በጥንቃቄ መጠበቅ ይችሉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዙ እኔ ዛሬ በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን የምሰጣችሁን ቃላት ሁሉ አስተውሉ። 47ይህ ሕግ የባዶ ቃላት ቅንብር አይደለም፤ እርሱ የሕይወታችሁ መሠረት ነው፤ ስለዚህ ለዚህ ቃል ታዛዦች ሁኑ፤ ይህን ብታደርጉ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሱአት ምድር ለረዥም ዘመን ትኖራላችሁ።”
ስለ ሙሴ ሞት በቅድሚያ መነገሩ
48በዚያኑ ቀን እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ 49“በሞአብ ምድር በኢያሪኮ ከተማ ፊት ለፊት ወደሚገኙት የዐባሪም ተራራዎች ሂድ፤ ወደ ነቦ ተራራም ውጣ፤ ከዚያም ለእስራኤል ሕዝብ የማወርሳትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት፤ 50ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ ሞቶ ወደ ወገኖቹ እንደ ተቀላቀለ አንተም በዚሁ በነቦ ተራራ ላይ ሞተህ ከወገኖችህ ጋር ትቀላቀላለህ፤ 51እናንተ ሁለታችሁም በእስራኤል ሕዝብ ፊት ለእኔ ታማኞች ሆናችሁ አልተገኛችሁም፤ በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ከተማ አጠገብ በምትገኘው በመሪባ ውሃ ምንጮች አጠገብ በነበራችሁበት ጊዜ በእስራኤል ሕዝብ ፊት እንድከበር አላደረጋችሁም። 52ከሩቅ ሆነህ ምድሪቱን ባሻገር ታያለህ፤ ነገር ግን እኔ ለእስራኤል ልጆች ወደማወርሳት ወደዚያች ምድር አትገባም።” #ዘኍ. 27፥12-14፤ ዘዳ. 3፥23-27።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997