ኦሪት ዘዳግም 34
34
የሙሴ አሟሟት
1ሙሴም ከሞአብ ሜዳዎች ተነሥቶ ወደ ነቦ ተራራ ወጣ፤ ከኢያሪኮም በስተምሥራቅ ወዳለው ወደ ፒስጋ ተራራ ጫፍ ደረሰ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ምድሪቱን በሙሉ አሻግሮ እንዲመለከት አደረገው፤ ይኸውም ከገለዓድ ግዛት አንሥቶ በስተ ሰሜን በኩል እስካለው እስከ ዳን ከተማ፥ 2የንፍታሌምንም ግዛት በሙሉ፥ የኤፍሬምንና የምናሴን ግዛት፥ በስተምዕራብ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ጠረፍ ያለውን የይሁዳን ግዛት፥ 3ኔጌብንና ሜዳውን፥ የኢያሪኮን ሸለቆ የዘንባባዎች ከተማ የምትባለውን ኢያሪኮን፥ እስከ ጾዓር ድረስ አሳየው። 4እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለዘሮቻቸው አወርሳት ዘንድ ለአብርሃም ለይስሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ቃል የገባሁላቸው የተስፋ ምድር ይህች ናት፤ እነሆ፥ እርስዋን በዐይንህ እንድታያት አድርጌአለሁ፤ ወደዚያች መግባት ግን አይፈቀድልህም።” #ዘፍ. 12፥7፤ 26፥3፤ 28፥13።
5ስለዚህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሞአብ ምድር ሳለ እግዚአብሔር በተናገረው መሠረት በዚያ ሞተ። 6እግዚአብሔርም ከቤትፐዖር ከተማ ፊት ለፊት በሞአብ አገር በሚገኘው ሸለቆ ቀበረው፤ ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ እርሱ የተቀበረበትን ትክክለኛ ቦታ ለይቶ የሚያውቅ የለም። 7ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ኻያ ዓመት ነበር፤ ነገር ግን ዐይኑ ያልፈዘዘና ጒልበቱም ያልደከመ ገና ብርቱ ሰው ነበር። 8የእስራኤልም ሕዝብ የሐዘኑ ጊዜ እስከሚያበቃ ድረስ ለሙሴ በማዘን ሠላሳ ቀን በሞአብ ሜዳ አለቀሱለት።
9ሙሴ የእርሱ ተተኪ እንዲሆን እጆቹን በመጫን ሹሞት ስለ ነበር የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ የተሞላ ሆነ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ለኢያሱ ታዘዘለት፤ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጣቸውንም ትእዛዝ ጠበቁ።
10እግዚአብሔር ፊት ለፊት ያነጋገረው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ በእስራኤል ከቶ ተነሥቶ አያውቅም፤ #ዘፀ. 33፥11። 11እግዚአብሔር ሙሴን ወደ ግብጽ ንጉሥና ወደ መኳንንቱ እንዲሁም በመላ ሀገሪቱ ልኮ በእርሱ አማካይነት እንዲፈጸሙ ያደረጋቸውን ተአምራትና ድንቅ ሥራዎች ያሳየ ሌላ ነቢይ ከቶ የለም። 12ሙሴ በእስራኤላውያን ሁሉ ፊት ያደረገውን ዐይነት ታላቅና አስፈሪ ነገር ሁሉ ያደረገ ሌላ ነቢይ ከቶ የለም።
Currently Selected:
ኦሪት ዘዳግም 34: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997