ወደ ኤፌሶን ሰዎች መግቢያ
መግቢያ
ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች የጻፈው መልእክት ከሁሉ በፊት የሚያተኲረው “የእግዚአብሔር ዕቅድ እንዲሆን በሰማይና በምድር ያሉት ፍጥረቶች ሁሉ ተጠቃለው በአንዱ በክርስቶስ ሥልጣን ሥር የሚሆኑበት ጊዜ ሲደርስ ነው” (1፥10) በሚለው አሳብ ላይ ነው። በተጨማሪም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በመተባበር የሰው ዘር ሁሉ አንድ ይሆን ዘንድ ይህን ታላቅ ዕቅድ በሥራ ላይ እንዲያውሉት የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚያሳስብ ነው።
የኤፌሶን መልእክት በመጀመሪያው ክፍል ጸሐፊው ስለ አንድነት የጀመረውን ርእስ በማስፋፋት፥ እግዚአብሔር አብ ሕዝቡን እንዴት እንደ መረጠ፥ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ የኃጢአታቸውን ይቅርታ አግኝተው እንዴት ነጻ እንደሆኑና፥ የእግዚአብሔርም ታላቅ የተስፋ ቃል በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት እንዴት እንደ ተረጋገጠ ያስረዳል፤ በሁለተኛው ክፍል ደግሞ ጸሐፊው አንባቢዎቹ በጋራ ሕይወታቸው በክርስቶስ ያላቸው አንድነት እውነተኛ ይሆን ዘንድ እንዴት መኖር እንደሚገባቸው ያሳስባቸዋል።
ሰዎች በክርስቶስ ባላቸው ኅብረት እንዴት አንድነት እንዳላቸው በልዩ ልዩ ፈሊጣዊ አነጋገር ተገልጦአል፤ ቤተ ክርስቲያን እንደ አካል ስትሆን ክርስቶስ እንደ አካሉ ራስ ነው፤ ቤተ ክርስቲያን እንደ ሕንጻ ስትሆን ክርስቶስ የማእዘኑ ድንጋይ ነው፤ ቤተ ክርስቲያን እንደ ሚስት ስትሆን ክርስቶስ እንደ ባል ነው፤ ጸሐፊው በክርስቶስ በኩል የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ጸጋ እጅግ በማድነቅ በሚናገርበት ጊዜ ጥልቀት ያለው አገላለጥ ያቀርባል፤ ሁሉን ነገር የሚመለከተው በክርስቶስ ፍቅር፥ መሥዋዕትነት፥ ይቅርታ፥ ጸጋና ሰላም አኳያ ነው።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
መግቢያ 1፥1-2
ክርስቶስና ቤተ ክርስቲያን 1፥3—3፥21
በክርስቶስ አዲስ ሕይወት 4፥1—6፥20
መደምደሚያ 6፥21-24
Currently Selected:
ወደ ኤፌሶን ሰዎች መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997