ትንቢተ ሕዝቅኤል 2
2
እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን ለነቢይነት መጥራቱ
1ከዚያም በኋላ “የሰው ልጅ ሆይ! ተነሥተህ በእግርህ ቁም፤ እኔም አነጋግርሃለሁ” አለኝ። 2በተናገረኝም ጊዜ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጤ ገብቶ በእግሮቼ አቆመኝ፤ የሚናገረኝንም ሰማሁ፤ 3እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! በእኔ ላይ ወደ ዐመፁት ወደ እስራኤል ሕዝብ እልክሃለሁ፤ እነርሱና የቀድሞ አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ በእኔ ላይ እንዳመፁ ናቸው። 4ትውልዱ እልኸኛና ልበ ደንዳና ነው። ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ እንድትነግራቸው ወደ እነርሱ እልክሃለሁ። 5እነዚያ ዐመፀኞች ቢሰሙህም ባይሰሙህም ነቢይ በመካከላቸው መኖሩን ያውቃሉ።
6“ነገር ግን የሰው ልጅ ሆይ! እነርሱንም ሆነ የሚናገሩትን ቃል አትፍራ፤ እንደ እሾኽና እንደ አሜከላ ሆነውብህ በጊንጦች መካከል እንደምትኖር ሆነህ ቢሰማህም ቃላቸውንም ሆነ የእነዚያን ዐመፀኞች የቊጣ ፊት ከቶ አትፍራ። 7ዐመፀኛ ሕዝብ ስለ ሆኑ ቢሰሙህም ባይሰሙህም እኔ የምልህን ቃል ትነግራቸዋለህ።
8“የሰው ልጅ ሆይ! እኔ የምነግርህን ስማ፤ አንተም እንደ እነርሱ ዐመፀኛ አትሁን፤ አፍህን ክፈት፤ እኔም የምሰጥህን ብላ።” 9ከዚህ በኋላ የብራና ጥቅል የያዘ እጅ ወደ እኔ ተዘርግቶ አየሁ። 10ያም እጅ የብራናውን ጥቅል ፈቶ በፊቴ ዘረጋው፤ እርሱም በሁለት በኩል ጽሑፍ ያለበት መሆኑን አየሁ፤ በእርሱም ላይ የለቅሶ፥ የሐዘንና የዋይታ ቃሎች ተጽፈውበት ነበር። #ራዕ. 5፥1።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 2: አማ05
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997