ትንቢተ ሕዝቅኤል 21
21
በኢየሩሳሌም ላይ የእግዚአብሔር ቅጣት
1እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! ፊትህን ወደ ኢየሩሳሌም መልሰህ በተቀደሱ ቦታዎችዋ ላይና በእስራኤል ምድር ላይ ትንቢት ተናገር። 3እንዲህም በላት! ‘እኔ በአንቺ ላይ ተነሥቼአለሁ፤ ሰይፉን ከሰገባው አውጥቼ ኃጢአተኛውንና ጻድቁን ከመካከልሽ አጠፋለሁ። 4ከመካከልሽም ኃጢአተኛውንና ጻድቁን ለማጥፋት ከደቡብ እስከ ሰሜን ባሉት ሁሉ ላይ ሰይፌ ከሰገባው ይመዘዛል። 5እኔ እግዚአብሔር ሰይፌን እንደ መዘዝኩና መልሼም ወደ አፎቱ እንደማልከተው ሰው ሁሉ ያውቃል።’
6“ስለዚህ በእነርሱ ፊት በተሰበረ ልብና በመረረ ሐዘን ቃትት! የሰው ልጅ ሆይ! ቃትት!” 7“ለምን ትቃትታለህ” ብለው ቢጠይቁህ “ስለሚመጣው ወሬ ነው” ትላቸዋለህ፤ “በዚያም ወሬ ልብ ሁሉ ይቀልጣል፤ እጅ ሁሉ ይዝላል፤ ወኔ ሁሉ ይከዳል፤ ጒልበት ሁሉ እንደ ውሃ ይፈስሳል፤ እነሆ እየመጣ ነው፤ በእርግጥ ይፈጸማል” ይላል ልዑል እግዚአብሔር።
8እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ 9“የሰው ልጅ ሆይ! ትንቢት ተናገር፤ እኔ እግዚአብሔር የምለውን ለሕዝቡ ተናገር፤ ሰይፍ! የተሳለና የተወለወለ ሰይፍ!
10ለመግደያ ተስሎአል፤
እንደ መብረቅ ለማብለጭለጭ ተወልውሎአል፤
ሕዝቤ የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያና ቅጣት ሁሉ ችላ ስላሉ፤
ከእንግዲህ ወዲህ ደስታ አይኖርም።
11ሰይፉ ተወልውሎ በእጅ እንዲያዝ ተሰጥቶአል፤
ለገዳዩ ይሰጥ ዘንድ ተስሎና ተወልውሎ ተዘጋጅቶአል።
12የሰው ልጅ ሆይ! በሐዘን ጩኽ፤
ይህ ሰይፍ የተዘጋጀው ሕዝቤንና
የእስራኤልን መሪዎች ለማጥፋት ነው።
እነርሱም ከቀሩት ሕዝቤ ጋር ይገደላሉ፤
ስለዚህ በሐዘን ደረትህን ምታ።
13ሕዝቤን እፈትናለሁ፤
ንስሓ መግባት እምቢ ቢሉ ይህ ሁሉ በእነርሱ ላይ ይደርሳል።
እኔ ጌታ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
14“አሁንም የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፤ እጅህን በቊጣ አማታው፤ ሰይፉም በመደጋገም ተወዛውዞ እየዞረም የሚገድል፥ የሚያሸብርና የሚያርድ ሰይፍ ነው፤ 15ሕዝቤ በፍርሃት በመሞላት ተሰናክለው ይወድቃሉ፤ እንደ መብረቅ በሚያብለጨልጭ፥ ለመግደያ የተዘጋጀውን ሰይፍ፥ በየበራፋቸው አድርጌአለሁ። 16አንተ ስለታም ሰይፍ! ስለትህ በዞረበት በቀኝና በግራ ቈራርጥ! 17እኔም በቊጣ እጄን አማታለሁ፤ ኀይለኛ ቊጣዬም ይበርዳል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ
18እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ 19“የሰው ልጅ ሆይ! የባቢሎን ንጉሥ ሰይፉን ይዞ የሚመጣባቸውን ሁለቱን መንገዶች ምልክት አድርግባቸው፤ የሁለቱም መነሻቸው አንዲት አገር ናት፤ ሁለቱ መንገዶች በሚገናኙበት መስቀለኛ ስፍራ ወደ ከተማ የሚያመራውን ምልክት ትከል። 20ለጦሩ ወደ አሞናውያን ከተማ ራባ በሚወስደው መንገድ ላይና እንዲሁም ወደ ተመሸገችው የይሁዳ ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም በሚወስደው መንገድ ላይ የአቅጣጫ ምልክት አድርግ። 21የባቢሎን ንጉሥ በመስቀለኛ መንገዶቹ መታጠፊያ አጠገብ ይቆማል፤ በየትኛው መንገድ መሄድ እንዳለበት ለማወቅ ፍላጻዎችን ይወረውራል፤ ጣዖቶቹንም ምክር ይጠይቃል፤ ለመሥዋዕት ከታረደ እንስሳ የጒበት ሞራ ወስዶም ይመረምራል። 22እነሆ ቀኝ እጁ ‘ኢየሩሳሌም!’ የሚል ጽሑፍ ያለበትን ፍላጻ አንሥቶ ይይዛል፤ እርሱም ሄዶ ምሽግ ማፍረሻዎችን እንዲያዘጋጅ፥ ለጦርነት የሚያዘጋጅ ድንፋታ እንዲያሰማ፥ ምሽግ ማፍረሻዎችን ወደ ቅጽር በሮቹ እንዲያስጠጋ፥ ዐፈር ቈልሎ እንዲደለድልና የከበባ ምሽግ እንዲሠራ ይነግረዋል። 23እያንዳንዱ ሰው ለባቢሎን ታማኝ ለመሆን ቃል ስለ ገባ ማንም ይህ ነገር ይፈጸማል ብሎ አያምንም ነበር፤ የባቢሎን ንጉሥ በሚማርካቸው ጊዜ ግን ኃጢአታቸውን ያስታውሳቸዋል። 24እንግዲህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፤ ኃጢአታችሁ ተገልጦአል፤ በደለኞች መሆናችሁን ሰው ሁሉ ያውቃል፤ በምታደርጉት ነገር ሁሉ ኃጢአተኞች መሆናችሁን ታሳያላችሁ፤ ስለዚህ ተማርካችሁ ትሄዳላችሁ።
25“አንተ ክፋትና ርኲሰት የሞላብህ የእስራኤል መሪ! ለመጨረሻ ጊዜ የምትቀጣበት ቀን እነሆ ቀርቦአል። 26እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ የራስ ዘውድህን አንሣ! ጥምጥምህን አውልቅ! ነገሮች እንደ ነበሩ አይቀሩም፤ ዝቅተኞችን በሥልጣን ከፍ አድርገህ አሁን ገዢዎች የሆኑትን ዝቅ አድርጋቸው! 27ጥፋት! ጥፋት! አዎ በእርግጥ ከተማይቱ እንድትጠፋ አደርጋለሁ፤ ነገር ግን ከተማይቱን እንዲቀጣ የመረጥኩት እስከሚመጣ ድረስ ይህ አይሆንም፤ በዚያን ጊዜ ለእርሱ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።
ሰይፍና ዐሞናውያን
28“የሰው ልጅ ሆይ! ትንቢት ተናገር፤ ስለ ዐሞናውያንና ስለ ስድባቸው እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውን እንዲህ ብለህ አስታውቃቸው፤
‘አጥፊ ሰይፍ ተዘጋጅቶአል፤
ለመግደልና ለማውደም እንደ መብረቅም ለማብለጭለጭ ተወልውሎአል!’ #ኤር. 49፥1-6፤ ሕዝ. 25፥1-7፤ አሞጽ 1፥3-15፤ ሶፎ. 2፥8-11።
29የምታዩት ራእይ ሐሰት ነው፤ የምትናገሩትም የትንቢት ቃል ውሸት ነው፤ እናንተ ክፋትና ርኲሰት የሞላችሁ ናችሁ፤ ለመጨረሻ ጊዜ ቅጣት የምትቀበሉበት ቀን ቀርቦአል፤ በአንገታችሁ ላይ ሰይፍ ተቃጥቶአል።
30“ ‘ሰይፉን ወደ አፎቱ መልሱ! በተፈጠራችሁበት ስፍራ፥ በተወለዳችሁበትም አገር እፈርድባችኋለሁ፤ 31የቊጣዬ ኀይል እንደ ተቀጣጠለ እሳት በእናንተ ላይ ይወርዳል፤ የማጥፋት ልምድ ላላቸው ለጨካኞች ሰዎች አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ 32በእሳት ትጠፋላችሁ፤ ደማችሁ በገዛ አገራችሁ ላይ ይፈስሳል፤ ዳግመኛም የሚያስታውሳችሁ አይኖርም፤’ ” እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 21: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997