ትንቢተ ሕዝቅኤል 26
26
በጢሮስ ላይ የተነገረ ትንቢት
1በተሰደድን በዐሥራ አንደኛው ዓመት በወሩም መባቻ ዕለት እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥ #ኢሳ. 23፥1-18፤ ኢዩ. 3፥4-8፤ አሞጽ 1፥9-10፤ ዘካ. 9፥1-4፤ ማቴ. 11፥21-22፤ ሉቃ. 10፥13-14። 2“የሰው ልጅ ሆይ! በጢሮስ ከተማ ያሉ ሕዝቦች የሚደሰቱበት ነገር ይህ ነው፦ ‘ኢየሩሳሌም ፈራርሳለች! የንግድ ኀይልዋም ወድቋል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ከእኛ ጋር መወዳደር ከቶ ስለማትችል እኛ እንበለጽጋለን’ ይላሉ።
3“ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ጢሮስ ሆይ! እኔ በአንቺ ላይ ተነሥቼ ባሕር ሞገድን እንደሚያስነሣ በአንቺ ላይ ብዙ ሕዝቦቼን አስነሣለሁ። 4የከተማሽን የቅጽር ግንቦች ያፈራርሳሉ፤ የዘብ መጠበቂያ ግንብሽን ይሰባብራሉ፤ ዐፈሩን ሁሉ ጠራርጌ በማጥፋት አለቱ ብቻ አግጥጦ እንዲቀር አደርጋለሁ፤ 5እዚያው በባሕር መካከል አጥማጆች መረባቸውን ለማድረቅ የሚያሰጡበት ስፍራ አደርጋታለሁ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ ሕዝቦች ጢሮስን ይመዘብራሉ። 6በዋናይቱ ምድር ላይ ባሉት መንደሮች የሚኖሩትንም ሕዝብ በጦርነት በሰይፋቸው ይጨፈጭፋሉ፤ በዚያን ጊዜ ጢሮስ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ታውቃለች።’ ”
7ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በጢሮስ ላይ አደጋ እንዲጥል የነገሥታት ንጉሥ የሆነውን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከሰሜን በኩል አመጣባታለሁ፤ እርሱም ከታላቅ ሠራዊት ጋር በብዙ ፈረሶችና ሠረገሎች በፈረሰኞችም ታጅቦ ይመጣል። 8በዋናይቱ ምድር ባሉት መንደሮች ነዋሪ የሆኑ ሕዝብ ሁሉ በጦርነት ያልቃሉ፤ እናንተን የሚከላከልበት ምሽግ ይሠራል። ጠላትም እስከ ቅጽሮችሽ ጫፍ ዐፈር ይደለድላል፤ በጋሻም ብዛት እየተከላከለ ያጠቃችኋል። 9በምሽግ ማፍረሻ መሣሪያ ቅጽሮችሽን ይመታል፤ የዘብ መጠበቂያ ግንብሽን በምሳር ያፈራርሳል፤ 10በፈረሶቻቸው ኮቴ የሚነሣው አቧራ እንደ ደመና ሆኖ ይሸፍንሻል፤ እርሱ ወደ ቅጥር በሮችሽ በሚገባበት ጊዜ ከፈረሰኛው፥ ከሠረገላውና ከመንኰራኲሩ የሚሰማው ድምፅ ተጥሳ እንደሚገባባት ከተማ ቅጥሮችሽን ያናጋል። 11ሠራዊቱ በፈረሶቹ ሰኰናዎች መንገዶችሽን ይረጋግጣል፤ ሕዝብሽን በሰይፍ ይገድላል፤ ጠንካራ ዐምዶችሽም ወደ መሬት ይወድቃሉ። 12ሀብትሽ ይማረካል፤ የንግድ ዕቃሽ ይዘረፋል፤ ቅጥርሽ ይፈርሳል፤ የተዋቡ ቤቶችሽ ይፈራርሳሉ፤ ድንጋዮችሽ፥ ሳንቃዎችሽና ፍርስራሹ ወደ ባሕር ይጣላሉ። 13ዘፈንሽንና በበገና የምታሰሚውን የሙዚቃ ድምፅ ሁሉ ጸጥ አደርጋለሁ። #ራዕ. 18፥22። 14ዓሣ አጥማጆች መረባቸውን የሚያሰጡበት አለት ብቻ አግጥጦ ይቀራል፤ ከተማይቱ ዳግመኛ አትታደስም፤ ይህም የሚሆነው እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ ተናገርኩ ነው።”
15ልዑል እግዚአብሔር ለጢሮስ ከተማ እንዲህ ይላታል፦ “ቊስለኞች ሲቃትቱና በመካከልሽ ግድያ ሲካሄድ ባወዳደቅሽ ድምፅ የጠረፉ አካባቢ አይናወጥምን? 16በባሕር አጠገብ ያሉ አገሮች ነገሥታት ሁሉ ከዙፋናቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውንና በእጅ ሥራ ጥልፍ ያጌጠ ልብሳቸውን አውልቀው በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ መሬት ላይ ይቀመጣሉ፤ በአንቺ ላይ የደረሰውን አሠቃቂ ሁኔታ እያሰቡ በብርቱ ይሸበራሉ፤ በአንቺም ሁኔታ ይደነግጣሉ። #ራዕ. 18፥9-10። 17እንዲህም እያሉ ስለ አንቺ ሙሾ ያወጣሉ፤
‘በባሕር ጠረፍ ያሉ አገሮችን ያሸበራችሁ፥
በባሕር ላይ ኀያል
የነበርሽ ዝነኛይቱ ከተማ ሆይ!
እንዴት ከባሕር ጠፋሽ?
18እነሆ አሁን በወደቀችበት ቀን
ደሴቶች ተንቀጠቀጡ፤
በላያቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ
ከዚህ ታላቅ ጥፋት የተነሣ ደነገጡ።’ ”
19ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ማንም ሊኖርባቸው እንደማይችል እንደ ፈራረሱ ከተሞች ባድማ አደርግሻለሁ፤ ጥልቅ ከሆነ ውቅያኖስ በሚገኝ ውሃ እሸፍንሻለሁ፤ 20ወደ ሙታን ዓለም ወርደሽ በጥንት ዘመን ይኖሩ ከነበሩ ሕዝቦች ጋር እንድትደባለቂ አደርጋለሁ፤ ከሙታን ጋር ተወዳጅተሽ እንድትኖሪ በዚያ ከምድር በታች ባለ ዓለም ውስጥ ዘለዓለም ፈራርሰው ከቀሩ ነገሮች ጋር እተውሻለሁ፤ ከዚህም የተነሣ ዳግመኛ ሰው አይኖርብሽም፤ በሕያዋንም ምድር ለመኖር ቦታ የለሽም፤ 21መጨረሻሽ አስፈሪ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ፍጻሜሽ ይሆናል፤ ሰዎች ቢፈልጉሽ እንኳ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከቶ አያገኙሽም፤” እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ። #ራዕ. 18፥21።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 26: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997