ትንቢተ ሕዝቅኤል 31
31
ግብጽ በዝግባ ዛፍ መመሰልዋ
1በተሰደድን በዐሥራ አንደኛው ዓመት፥ ሦስተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! ለግብጽ ንጉሥና ብዛት ላለው ሕዝቡ እንዲህ ብለህ ንገር፥
‘በታላቅነት ከማን ጋር ትመሳሰላለህ?
3አንተ የተዋቡ ጥላማ ቅርንጫፎች እንዳሉትና
የቁመቱም ርዝመት ደመናዎችን እንደሚነካ
የሊባኖስ ዛፍ ነህ።
4እዚያም ዛፉን የሚያሳድገው በቂ ውሃ ነበረው፤
በመሬት ውስጥ ያለው ጥልቅ ውሃ ዛፉን ያሳድገዋል፤
ጅረቶችም በሜዳ በተተከሉ ዛፎች ዙሪያ ይፈስሳሉ።
5ይህም ዛፍ ብዙ ውሃ በማግኘቱ፥
ቁመቱ ከሌሎች ዛፎች ሁሉ የረዘመ ሆነ፤
ቅርንጫፎቹም ወፍራሞችና ረጃጅሞች ሆኑ።
6የወፍ ዐይነቶች ሁሉ በቅርንጫፎቹ ላይ ጎጆአቸውን ሠሩ፤
የምድር አራዊትም ግልገሎቻቸውን በጥላዎቹ ሥር ወለዱ፤
ታላላቅ ሕዝቦች ሁሉ በጥላው ሥር ያርፉ ነበር።
7ብዙ ውሃ ወዳለበት ሥሮቹን ስለ ሰደደ፥
ታላቅነቱና የቅርንጫፎቹ መስፋፋት ውበትን ሰጥቶት ነበር።
8በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ያለው የሊባኖስ ዛፍ ሊወዳደረው አይችልም፤
የጥድ ዛፍም ቅርንጫፉን አያኽልም፤
የግራር ዛፎች ቅርንጫፍ ከእርሱ ቅርንጫፎች ጋር
ሲወዳደር እንደ ኢምንት ነው።
በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ካሉ ዛፎች መካከል
አንዳቸው እንኳ እንደ እርሱ ያለ ውበት የላቸውም። #ዘፍ. 2፥9።
9እኔ እርሱን በተንሠራፉ ቅርንጫፎች የተዋበ አደረግሁት፤
እርሱ እኔ እግዚአብሔር በተከልኳት በዔደን ገነት ያለውን ዛፍ ሁሉ የሚያስቀና ነበር።’
10“እንግዲህ አድጎ እስከ ደመናት በደረሰ መጠን፥ ትዕቢት በሚሰማው በዚያ ዛፍ ላይ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የማደርገው ይህ ነው፤ 11እኔ እርሱን አውጥቼ እጥለዋለሁ፤ ለሕዝቦች መሪ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፤ እርሱም እንደ ክፋቱ መጠን ይደረግበታል። 12ከምድር ሕዝቦች በጣም ጨካኞች የሆኑት ዛፉን ቈርጠው ይጥላሉ። ቀንበጦቹም በተራሮችና በሸለቆዎች ላይ ይወድቃሉ፤ ቅርንጫፎቹ ተሰባብረው በወራጅ ውሃ ላይ ይጋደማሉ። በጥላው ሥር ተጠልለው የነበሩት የምድር ሕዝቦች ሁሉ ትተውት ይሄዳሉ። 13ወፎች መጥተው በወደቀው ግንድ ላይ ያርፋሉ፤ ቅርንጫፎቹም ለአራዊት መጠጊያ ይሆናሉ፤ 14የቱንም ያኽል ውሃ እየጠጣ ቢያድግ በዚህ ዐይነት ከፍተኛ ቁመት እስከ ደመና የሚደርስ ዛፍ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አይኖርም። ሟቾች በሆኑ ሰዎች ላይ የሚደርሰው የሞት ፍርድ በእነርሱም ላይ ይደርሳል፤ ወደ ሙታን ዓለምም ይወርዳሉ።”
15ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ያ ዛፍ ተቈርጦ ወደ ሙታን ዓለም በሚወርድበት ጊዜ ጥልቁን ውሃ ዘግቼ እየተለቀሰለት ይሸፈናል። ወንዞችም እንዲቋረጡ አደርጋለሁ፤ ኀይለኞቹ ወራጅ ውሃዎችም እንዲቆሙ ይደረጋሉ። በዚህም ምክንያት በሊባኖስ ተራራዎች ላይ የጨለማ ግርዶሽ አመጣለሁ፤ ስለዚህም የሜዳ ዛፎች ሁሉ ይጠወልጋሉ። 16እኔ ያን ዛፍ ወደ ሙታን ዓለም እንዲወርድ በማደርግበት ጊዜ አወዳደቁ የሚያሰማው ድምፅ ሕዝቦችን ሁሉ ያንቀጠቅጣል፤ ወደ ሙታን ዓለም የወረዱ የዔደን ዛፎችና የጥሩ መስኖ ውሃ የሚጠጡ የተመረጡ የሊባኖስ ዛፎች ሁሉ እርሱ ወደ ሙታን ዓለም በመውረዱ ደስ ይላቸዋል፤ 17በጥላው ሥር የነበሩትና ከሕዝቦች መካከል ተባባሪዎቹ የነበሩት በሰይፍ ወደ ተገደሉት ከእርሱ ጋር ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳሉ።
18“ዛፉ የግብጽ ንጉሥና የሕዝቡ ሁሉ ምሳሌ ነው፤ በዔደን ገነት ከነበሩት ዛፎች መካከል እንኳ በቁመትና በውበት እርሱን የሚያኽል አልነበረም። አሁን ግን በዔደን ገነት እንደ ነበሩት ዛፎች ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳል፤ እዚያም በእግዚአብሔር የማያምኑ በጦርነት ከተገደሉት ሁሉ ጋር ይደባለቃል፤” ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 31: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997