ትንቢተ ሕዝቅኤል 42
42
በቤተ መቅደሱ አጠገብ የተሠሩ ሁለት ሕንጻዎች
1ከዚህም በኋላ ያ ሰው በውጭ በኩል ወደሚገኘው አደባባይ ወሰደኝ፤ ከባዶ ቦታ ፊት ለፊት እና በሰሜን በኩል ካለው ሕንጻ ትይዩ ወደነበሩት ክፍሎች አመጣኝ። 2በሰሜን በኩል ያለው ሕንጻ ርዝመት መቶ ክንድ ሲሆን፥ ወርዱ ኀምሳ ክንድ ነበር። 3ኻያ ክንድ የሆነው የውስጥ አደባባይ ታልፎ በውጪው አደባባይ ንጣፍ ትይዩ የተሠሩት ክፍሎች ከፎቅ ወደ ፎቅ እያደጉ ወደ ሦስተኛ ፎቅ ደርሰዋል። 4ከክፍሎቹ ፊት ለፊት በውስጥ በኩል ዐሥር ክንድ ወርድና መቶ ክንድ ርዝመት ያለው መተላለፊያ ነበር፤ መግቢያዎቹም በስተ ሰሜን በኩል ነበሩ። 5የሦስተኛው ፎቅ ክፍሎች ከሁለተኛውና ከምድር ቤቱ ክፍሎች የጠበቡ ናቸው። ይህም የሆነበት ምክንያት ፎቆቹ ከፍ ባሉ ቊጥር በረንዳዎቻቸው ሰፋ ስለሚሉና ክፍሎቹን ስለሚያጣብቡአቸው ነው። 6እነርሱም በሦስት ፎቆች የተሠሩ ሲሆኑ እንደ ውጪው አደባባይ ሕንጻዎች ዐምዶች አልነበሩአቸውም። ስለዚህ የላይኛው ፎቅ ክፍሎች ከሁለተኛው ፎቅና ከምድር ቤቱ ክፍሎች ይልቅ ወደ ውስጥ ገባ ያሉ ነበሩ። 7ከክፍሎቹ ፊት ለፊት ኀምሳ ክንድ ርዝመት ያለው በስተውጪው አደባባይ በኩል በክፍሎቹ ትይዩ አንድ ግንብ ነበር። 8በውጪው አደባባይ በኩል ያሉት ክፍሎች ኀምሳ ክንድ ርዝመት ሲኖራቸው ከቤተ መቅደሱ ትይዩ ያሉት ክፍሎች ግን መቶ ክንድ ርዝመት ነበራቸው። 9የታችኛዎቹ ክፍሎች በምሥራቅ በኩል ከወደ ውጪው አደባባይ መግቢያ ነበራቸው። 10በስተ ደቡብ በኩል ደግሞ ከውጪው አደባባይ ግንብ ርዝመት ጐን ለጐን ከባዶ ቦታውና ከሕንጻው ፊት ለፊት ክፍሎች ነበሩ። 11በክፍሎቹም ፊት ለፊት መተላለፊያ ነበር፤ ክፍሎቹ ልክ በሰሜን በኩል እንዳሉት ክፍሎች ርዝመትና ወርዳቸው፥ መውጫዎቻቸውና የበሮቻቸው አቀማመጥ ተመሳሳይ ነበር። 12ስለዚህ በደቡብ በኩል ወዳሉት ክፍሎች መግቢያ በሮች የሚገባው በትይዩ በስተምሥራቅ ባለው ተመሳሳይ ግንብ መጨረሻ በሚገኘው መተላለፊያ በኩል ነው። 13ያም ሰው እንዲህ አለኝ፦ “ከቤተ መቅደሱ ባዶ ቦታ ፊት ለፊት በሰሜንና በደቡብ ያሉት ክፍሎች የተቀደሱ ናቸው። የተቀደሱበት ምክንያት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡት ካህናት የተቀደሱ ቊርባኖችን የሚበሉባቸው ቦታዎች ስለ ሆኑ ነው፤ ቦታዎቹም የተቀደሱ በመሆናቸው የእህል ቊርባን፥ የኃጢአት ማስተስረያ ቊርባንና ለበደል የሚቀርብ መሥዋዕትን ያኖሩባቸዋል። 14ካህናቱ ወደተቀደሰው ቦታ ገብተው የሚያገለግሉባቸውን ልብሶች ከለበሱ በኋላ ያን ያገልግሎት ልብስ ሳያወልቁ ወደ ውጪው አደባባይ አይወጡም፤ ልብሶቹም የተቀደሱ ስለ ሆኑ ከተቀደሰው ቦታ ወጥተው ለሕዝብ ወደተፈቀደው ቦታ ከመድረሳቸው በፊት ሌላ ልብስ መልበስ ይኖርባቸዋል።”
ቤተ መቅደሱ የተሠራበት ቦታ መጠን
15ያ ሰው የቤተ መቅደሱን ውስጣዊ ክፍሎች ለክቶ ከጨረሰ በኋላ፥ በምሥራቁ የቅጽር በር በኩል ወደ ውጪ አወጣኝ፤ ከዚያም በኋላ የውጪውን ክልል ለካ። 16የመለኪያውንም ዘንግ ወስዶ የምሥራቁን አቅጣጫ ሲለካ አምስት መቶ ክንድ ነው። 17ከዚያም በኋላ በሰሜን በኩል በዘንጉ ሲለካ አምስት መቶ ክንድ ነው። 18በደቡብ በኩልም ያው አምስት መቶ ክንድ ሆነ። 19በምዕራቡ በኩል ሲለካ አምስት መቶ ክንድ ሆነ። 20በተቀደሰውና በተራው ቦታ መካከል ለመለየት ቤተ መቅደሱን የሚከልለው ግንብ ርዝመቱ አምስት መቶ ክንድ፥ ወርዱ አምስት መቶ ክንድ ሆነ።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 42: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997