ትንቢተ ሕዝቅኤል 45
45
በርስት አከፋፈል ለእግዚአብሔር የተለየ ድርሻ
1ምድሪቱ ለእያንዳንዱ ነገድ በርስትነት በምትከፋፈልበት ጊዜ አንድ ዕጣ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል፤ እርሱም ርዝመቱ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ፥ ወርዱም ኻያ ሺህ ክንድ ይሆናል፤ ጠቅላላውም ክልል የተቀደሰ ይሆናል። 2ከዚህም ክልል ውስጥ የእያንዳንዱ ማእዘን ርዝመት አምስት መቶ ክንድ ሆኖ አራት ማእዘን ያለው አንድ ቦታ ለቤተ መቅደሱ ይመደባል፤ በዚህም ክልል ዙሪያ ስፋቱ ኀምሳ ክንድ የሆነ ክፍት ቦታ ይኖራል። 3ለእግዚአብሔር ከተከለለው ክልል ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመት፥ ዐሥር ሺህ ክንድ ወርድ ይለካል፤ እርሱም ከሁሉም የበለጠ ለተቀደሰው ቤተ መቅደስ መሥሪያ ይሆናል። 4ይህ ከጠቅላላው መሬት የተቀደሰ ክፍል ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ቀርበው በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለሚያገለግሉት ካህናት የተደለደለ ነው፤ ቦታውም ለካህናቱ መኖሪያና ለቤተ መቅደሱ መሥሪያ ይሆናል። 5ቀሪው አጋማሽ ማለትም ርዝመቱ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱ ዐሥር ሺህ ክንድ የሆነው ቦታ ደግሞ በቤተ መቅደስ ለሌሎች ልዩ ልዩ አገልግሎት ለተመደቡት ሌዋውያን ርስት ይሆናል፤ ለእነርሱ መኖሪያ የሚሆኑ ከተሞችም በዚያ ይሠራሉ።
6ከተቀደሰውም ክልል ቀጥሎ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመትና አምስት ሺህ ክንድ ወርድ ያለው ለእስራኤል ነገድ ሁሉ የሚሆን ከተማ መሥሪያ ይከለላል።
በርስት አከፋፈል የመስፍኑ ድርሻ
7የሀገሪቱም መሪ ድርሻ ከተቀደሰው ቦታና ከከተማው ክልል ቀጥሎ በሁለቱም በኩል ማለትም በስተምዕራብ እስከ ሀገሪቱ ድንበር ሲደርስ በስተ ምሥራቅም እስከ ሀገሪቱ ድንበር የሚደርስ ይከለላል፤ ርዝመቱም ለአንድ ነገድ የሚደርሰውን ድርሻ ያኽላል። 8ይህም ክልል በእስራኤል ምድር መሪ ለሚሆነው መስፍን የርስት ድርሻ ይሆናል፤ ከዚህም በኋላ መሪዎች ሁሉ ሕዝቡን መጨቈን የለባቸውም፤ ነገር ግን ከሀገሪቱ ቀሪውን ምድር በሙሉ ለእስራኤል ነገዶች መተው ይኖርባቸዋል።
የመስፍኑ መመሪያ ሕግ
9ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የእስራኤል መሪዎች! እነሆ ለረጅም ጊዜ ኃጢአት ስትሠሩ ኖራችኋል፤ አሁን ግን ግፍንና ጭቈናን አቁሙ! ቅንና ትክክል የሆነውን ነገር ሥሩ! ሕዝቤ እንደገና ከምድራቸው ተፈናቅለው እንዲባረሩ አታድርጉ! ይህን የምነግራችሁ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ነኝ።
10“እያንዳንዱ ሰው ትክክለኛ ሚዛንና መለኪያ እንዲሁም እኩል የሆነ መስፈሪያ ይኑረው።
11“የመስፈሪያዎች ሁሉ አማካኝ መለኪያ ጎሞር ይሁን፤ የደረቅ ነገሮች መስፈሪያ የሆነው ኢፍ፥ የፈሳሽ ነገሮች መለኪያ ከሆነው ባት ጋር እኩል መሆን አለበት፤ በዚህም ዐይነት አንድ ጎሞር ከዐሥር ኤፋና ከዐሥር ባት ጋር እኩል ይሆናል።
12“ሚዛናችሁም፥
ኻያ ጌራህ አንድ ሰቅል፥
ሥልሳ ሰቅል አንድ ምናን ይሁን፤ #45፥12 ጎሞር ሆሜር ወይም ኦሜር፦ አንድ ኪሎ ተኩል ወይም ሁለት ሊትር። #45፥12 ኢፍ (ኤፋ)፦ ዐሥር ጎሞር። #45፥12 ባት፦ ከኢፍ ጋር እኩል ነው። #45፥12 ጌራ፦ ሦስት አምስተኛ ማለት ነው። #45፥12 ሰቅል፦ 5 ግራም ነው። #45፥12 ምናን፦ 6 ግራም ነው።
13“የምታቀርቡት መሥዋዕት ከእያንዳንዱ ጎሞር ስንዴ አንድ ስድስተኛ ኢፍ፥ ከእያንዳንዱ ጎሞር ገብስም አንድ ስድስተኛ ኢፍ ነው። 14ከዘይትም የተመደበው ከያንዳንዱ ቆሮስ አንድ ዐሥረኛ ባት ነው። (አንድ ቆሮስ፥ አንድ ጎሞር ወይም ዐሥር ባት ማለት ነው) 15እንዲሁም ከእስራኤል የበግ መንጋዎች መካከል ከየሁለት መቶ በግ የተመደበው አንድ በግ ነው፤ ይህም ለእነርሱ የኃጢአት ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ከእህል ቊርባን ጋር የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብ ነው፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ። 16በምድሪቱ የሚኖሩ ሕዝብ በሙሉ ይህን ሁሉ የእስራኤል መሪ ለሆነው ይሰጣሉ፤ 17ለሚቃጠለው መሥዋዕት፥ ለእህል ቊርባንና ለመጠጥ ቊርባን በወር መባቻ፥ በሰንበቶች፥ በተወሰኑትም የእስራኤል ሕዝብ በዓላት እንዲቀርቡ የሚያስፈልጉትን ማዘጋጀት የመሪው ግዴታ ነው፤ ለእስራኤላውያን የኃጢአት ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ስለ ኃጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት፥ የእህሉን ቊርባን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነትን ቊርባን ማዘጋጀት አለበት።”
የበዓላት አከባበር
(ዘፀ. 12፥1-20፤ ዘሌ. 23፥33-43)
18ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የመጀመሪያው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ምንም ነውር የሌለበት አንድ ወይፈን በመሠዋት ቤተ መቅደሱን ታነጻለህ። 19ካህኑ ከዚህ የኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ጥቂት ደም ወስዶ የቤተ መቅደሱን መቃኖች፥ የመሠዊያውን እርከን አራት ማእዘኖችና ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገቡትን የቅጽር በሮች መቃኖች ይቀባል፤ 20ማንም ሆን ብሎ ባለማሰብ ወይም ባለማወቅ ስለ ሠራው ኃጢአት ሁሉ በሰባተኛው ቀን እንደዚሁ ታደርጋለህ፤ በዚህ ሁኔታ ቤተ መቅደሱ እንዲቀደስ ታደርጋለህ።
21“የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካን በዓል ታከብራላችሁ፤ በዚህም በዓል አከባበር እስከ ሰባት ቀን ድረስ እርሾ ያልነካው ቂጣ ትበላላችሁ። 22በበዓሉም ቀን በሥልጣን ላይ ያለው መስፍን ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ስርየት አንድ ኰርማ ያዘጋጃል። 23በዓሉ በሚከበርባቸው ሰባት ዕለቶች በእያንዳንዱ ቀን ምንም ነውር የሌለባቸውን ሰባት ኰርማዎችና ሰባት የበግ አውራዎች በሙሉ ለሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የሚቀርቡትን ያዘጋጃል፤ ከዚህም ጋር በእያንዳንዱ ዕለት ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚሆን አንድ የፍየል አውራ ያዘጋጃል። 24እያንዳንዱ ኰርማና እያንዳንዱ የበግ አውራ በሚሠዋበት ጊዜ አንድ አንድ የኤፋ መስፈሪያ እህልና ሦስት ሦስት ሊትር የወይራ ዘይት አብሮ ይቀርባል።
25“ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥራ አምስተኛው ቀን መከበር ለሚጀምረው የዳስ በዓል፥ መስፍኑ በሰባቱ ቀኖች በእያንዳንዱ ዕለት ለኃጢአት ስርየትና በሙሉ ለሚቃጠል ተመሳሳይ መሥዋዕት ያዘጋጃል፤ የእህሉና የዘይቱም መሥዋዕት በተመሳሳይ ሁኔታ ይቀርባል።”
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 45: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997