ትንቢተ ሕዝቅኤል 48
48
የምድሪቱ አከፋፈል
1ምድሪቱን ለመካፈል የተመዘገቡት ነገዶች እነዚህ ናቸው፤ የዳን ነገድ በምድሪቱ ሰሜናዊ ወሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ እርሱም ከሔትሎን ወደ ሐማት መግቢያ የሚወስደውን ጐዳና ተከትሎ ከዚያም ሐጻርዔኖንና የደማስቆ ሰሜናዊ ክፍል ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የዳን ድንበር ይሆናል። 2አሴርም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከዳን ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ 3ንፍታሌም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከአሴር ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ 4ምናሴ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከንፍታሌም ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ 5ኤፍሬም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከምናሴ ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ 6ሮቤል ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከኤፍሬም ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ 7ይሁዳ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከሮቤል ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል።
በምድሪቱ ማእከል የሚከለል ልዩ ቦታ
8ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከይሁዳ ነገድ ድንበር ጋር የተያያዘ ቦታ ለይታችሁ ትመደባላችሁ፤ ይህም ቦታ ወርዱ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመት ከሌሎች ነገዶች ድርሻ ጋር ከምሥራቅ ጐን እስከ ምዕራብ ጐን ድረስ እኩል ይሆናል፤ ቤተ መቅደሱም የሚገኘው በዚህ ቦታ መካከል ነው።
9በዚህም ክልል መካከል ርዝመቱ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ፥ ወርዱም ኻያ ሺህ ክንድ የሆነ ቦታ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል። #48፥9 ኻያ ሺህ ክንድ፦ በዕብራይስጡ ዐሥር ሺህ ክንድ ይላል ምዕራፍ 45 ቊ. 1 ይመለከቷል። 10ካህናቱም ከዚህ ከተቀደሰው ቦታ የተወሰነ ድርሻ ይኖራቸዋል፤ እርሱም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመትና ከሰሜን እስከ ደቡብ ዐሥር ሺህ ክንድ ወርድ ይኖረዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም በመካከሉ ይኖራል። 11ይህም ቦታ የሳዶቅ ተወላጆች ለሆኑት የተቀደሱ ካህናት የተለየ ይሆናል። እስራኤላውያን ሁሉና ሌሎቹ ሌዋውያን እኔን ትተው በባዘኑ ጊዜ የሳዶቅ ልጆች ከትእዛዞቼ ፈቀቅ ሳይሉ ጠብቀው የኖሩ ናቸው። 12ከተቀደሰው ቦታ ይህ የእነርሱ ድርሻ ነው፤ እርሱም በጣም የተቀደሰ ሲሆን ከሌዋውያን ድንበር ጋር የተያያዘ ነው። 13ከካህናቱ ቦታ ጐን ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመትና ዐሥር ሺህ ክንድ ወርድ የሆነ የሌዋውያን ድርሻ አለ፤ ጠቅላላውም ከካህናቱ ድርሻ ጋር ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመትና ኻያ ሺህ ክንድ ወርድ ነው። 14ለእግዚአብሔር የሚከለለው ስፍራ በምድሪቱ ከሚገኘው ሁሉ የተሻለ ምርጥ ቦታ ነው፤ ከእርሱም ተከፍሎ የሚሸጥና የሚለወጥ ወይም ለማንም በውርስ የሚተላለፍ አይሆንም፤ እርሱ ለእግዚአብሔር ተለይቶ የተቀደሰ ስፍራ ነው።
15ልዩ ከሆነው ክልል ተከፍሎ የሚቀረው ስፍራ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመት አምስት ሺህ ክንድ ወርድ ነው፤ እርሱም በአጠቃላይ ለሕዝቡ የጋራ መጠቀሚያ ይሆናል፤ ለቤት ሥራና ለከብት ማሰማሪያም ይሆናል፤ ከተማይቱም በመካከሉ ትሆናለች። 16እርስዋም አራት ማእዘን እኩል ርዝመት ያላት ሆና የእያንዳንዱ ማእዘን ርዝመት አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ይሆናል። 17ከተማዋ በአራቱም ማእዘን የመሰማሪያ ቦታ ይኖራታል፤ በየማእዘኑ ያለው የመሰማሪያ ቦታ ስፋት ሁለት መቶ ኀምሳ ክንድ ነው። 18ከተቀደሰው ክልል በምሥራቅ ዐሥር ሺህ ክንድ በምዕራብ ዐሥር ሺህ ክንድ ተነሥቶለት ከተማይቱ ከተሠራች በኋላ የሚቀረው ትርፍ ቦታ በከተማይቱ ለሚኖሩት ሕዝብ የእርሻ መሬት ይሆናል። 19በከተማይቱ የሚኖር ከየትኛውም ነገድ የተወለደ ሰው ሁሉ ያን መሬት ማረስ ይችላል።
20ስለዚህም በምድሪቱ መኻል የተለየው ቅዱስ ድርሻ በጠቅላላው የእያንዳንዱ ማእዘን ርዝመት ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ሲሆን እርሱም ከተማይቱ የተሠራችበትን ቦታ ያጠቃልላል።
21በተቀደሰው ቦታና በከተማውም ይዞታ በሁለቱም በኩል የተረፈው ክፍል የመስፍኑ ድርሻ ነው። ይኸውም በምሥራቅ በኩል የተቀደሰውን ቦታ ከሚያዋስነው ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ተነሥቶ እስከ ምድሪቱ ወሰን ድረስ ነው። በምዕራብም በኩል የተቀደሰውን ቦታ ከሚያዋስነው ከኻያ አምስት ሺህ ክንድ ተነሥቶ እስከ ምድሪቱ ወሰን ድረስ ነው። የመሪውም ድርሻ ርዝመቱ ከሌሎቹ ነገዶች ድርሻ እኩል ነው። በዚህ ዐይነት የተቀደሰው ቦታና ቤተ መቅደሱ በመካከል ይሆናሉ ማለት ነው። 22እንደዚሁም የሌዋውያኑና የከተማው ይዞታ በምሥራቅና በምዕራብ የመሪው ይዞታ ከሆኑት ቦታዎች መካከል ናቸው ማለት ነው፤ እንዲሁም በሰሜን ከይሁዳ ዕጣ፥ በደቡብም ከብንያም ዕጣ ጋር ይዋሰናል።
ለሌሎች ነገዶች የተከፈለ ምድር
23ስለቀሩትም ነገዶች የምድሪቱ አከፋፈል እንደሚከተለው ነው፤ ብንያም ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የሚደርስ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ 24ስምዖን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከብንያም ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ 25ይሳኮር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከስምዖን ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ 26ዛብሎን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከይሳኮር ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ 27ጋድ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከዛብሎን ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል።
28የጋድ ደቡባዊ ድንበር ከታማር ከተማ ደቡብ ተነሥቶ በመሪባ ቃዴስ እስከምትገኘው የውሃ ምንጭ ይዘልቃል፤ ከዚያም የግብጽ ወሰን የሆነውን ወንዝ ተከትሎ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ይደርሳል።
29ልዑል እግዚአብሔር “በዚህ ዐይነት ለእስራኤል ነገዶች ሁሉ በርስትነት የምታከፋፍሉአቸው ምድር ይህች ናት” ሲል ተናገረ።
የኢየሩሳሌም ቅጽር በሮች
30-31የከተማይቱ መውጫ በሮች አራት ማእዘኖች የሚከተሉት ናቸው፦ በየማእዘኑ ሦስት በሮች ሲኖሩ ለያንዳንዱ በር የአንድ ነገድ ስም ተሰጥቶታል። በሰሜን በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ርዝመት አለው። በዚህ ማእዘን ያሉት ሦስት በሮች በሮቤል፥ በይሁዳና በሌዊ ስም ተሰይመዋል። 32በምሥራቅ በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ርዝመት አለው። በዚህ ማእዘን ያሉት ሦስት በሮች በዮሴፍ፥ በብንያምና በዳን ስም ተሰይመዋል። 33በደቡብ በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ርዝመት አለው። በዚህም ማእዘን ያሉት ሦስት በሮች በስምዖን፥ በይሳኮርና በዛብሎን ስም ተሰይመዋል። 34በምዕራብ በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ርዝመት አለው። በዚህም ማእዘን ያሉት ሦስት በሮች በጋድ፥ በአሴርና በንፍታሌም ስም ተሰይመዋል። #ራዕ. 21፥12-13። 35በአራቱም አቅጣጫ ያሉት የከተማይቱ የቅጽር ግንቦች ጠቅላላ ርዝመት ዐሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ ከአሁን በኋላ የከተማይቱ መጠሪያ ስም “እግዚአብሔር በዚያ አለ!” የሚል ይሆናል።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 48: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997