ትንቢተ ሕዝቅኤል 5
5
ሕዝቅኤል ጠጒሩን መላጨቱ
1እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የተሳለ ሰይፍ ወስደህ ጢምህንና የራስ ጠጒርህን በሙሉ ተላጭ፤ ጠጒርህንም በሚዛን መዝነህ በሦስት ቦታ ክፈለው። 2ከበባው ከተፈጸመ በኋላ ከሦስቱ አንዱን እጅ የከተማውን ንድፍ በሠራህበት ጡብ መካከል አቃጥለው፤ ሁለተኛውን አንድ ሦስተኛ እጅ ቈራርጠህ የከተማው ንድፍ በተሠራበት ጡብ ዙሪያ አኑረው። ሦስተኛውን አንድ ሦስተኛ እጅ ደግሞ ለነፋስ በትነው፤ እኔም በሰይፍ አሳድደዋለሁ። 3በከተማው ዙሪያ በሰይፍ ቈራርጠው፤ ደግሞም ከዚሁ ጥቂት ጠጒር ወስደህ በመጐናጸፊያህ ጫፍ ላይ ቋጥረው። 4ከእርሱም ላይ እንደገና ጥቂት ቈንጥረህ በእሳት ውስጥ ጣለውና እንዲቃጠል አድርገው፤ ከእርሱም የሚነሣው እሳት ወደ እስራኤል ሕዝብ ሁሉ ይደርሳል።”
5ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ ኢየሩሳሌምን ተመልከት! ሌሎች አገሮች በዙሪያዋ ሆነው በሕዝቦች መካከል እንድትሆን አድርጌአታለሁ፤ 6ኢየሩሳሌም ግን ሕጎቼንና ደንቤን በመጣስ ከሌሎች ሕዝቦች ይልቅ የከፋችና በዙሪያዋም ካሉት አገሮች ይበልጥ እምቢተኛ መሆንዋን አሳይታለች፤ ኢየሩሳሌም ሕጎቼንና ደንቦቼን ንቃለች፤ ትእዛዞቼንም አልተከተለችም።” 7ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር የሚለው እንዲህ ነው፦ “እናንተ የኢየሩሳሌም ኗሪዎች! በዙሪያችሁ ካሉት ሕዝቦች ይበልጥ ሥርዓተ አልበኞች ሆናችኋል፤ ሕጎቼንና ሥርዓቴን አላከበራችሁም፤ በአካባቢአችሁ ባሉት ሕዝቦች ሥርዓት እንኳ አልተመራችሁም። 8በዚህም ምክንያት እኔ ልዑል እግዚአብሔር በአንቺ በኢየሩሳሌም ላይ በቊጣ የተነሣሁብሽ መሆኔን እገልጥልሻለሁ፤ ሕዝቦች ሁሉ እያዩ በፍርድ እቀጣሻለሁ። 9በርኲሰቶችሽ ሁሉ ምክንያት ከዚህ በፊት ያላደረግኹትንና ወደፊትም የማላደርገውን ቅጣት በአንቺ ላይ አመጣለሁ። 10በዚህም ምክንያት በኢየሩሳሌም ያሉ ወላጆች በእርግጥ ልጆቻቸውን ይበላሉ፤ ልጆችም ወላጆቻቸውን ይበላሉ፤ በዚህ ዐይነት ሁላችሁንም እቀጣለሁ፤ የተረፉትንም በአራቱ ማእዘን እበትናቸዋለሁ። #ሰቆ.ኤ. 4፥10።
11“ስለዚህ ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ እኔ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፤ ክፋትና ርኲሰት የተሞላበት ነገር ሁሉ በመፈጸም ቤተ መቅደሴን በማርከሳችሁ ምክንያት እኔም ያለ ምሕረት እንድትዋረዱ አደርጋለሁ። 12ከሕዝባችሁ አንድ ሦስተኛው እጅ በራብና በበሽታ ያልቃል፤ አንድ ሦስተኛው ከከተማው ውጪ በሰይፍ ይገደላል፤ ሌላው ሦስተኛ እጅ በአራቱ ማእዘን በነፋስ እንዲበተን አድርጌ በኋላ በሰይፍ አሳድደዋለሁ።
13“ቊጣዬ በእርሱ ላይ ይፈጸማል ኀይለኛ ቊጣዬንም በእነርሱ ላይ አውርጄ እረካለሁ ይህንንም ቊጣዬን በእነርሱ ላይ ባወረድኩ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር በቅናቴ የተናገርኩ መሆኔን ያውቃሉ። 14እንዲሁም አገራችሁን ባድማና በአካባቢአችሁ ለሚኖሩ ሕዝቦች መሳለቂያ አደርጋለሁ፤ ይህንንም የማደርገው አላፊ አግዳሚ ሁሉ እያየ ነው።
15“በኀይለኛ ቊጣዬ በእናንተ ላይ ፍርዴን ተግባራዊ አድርጌ በምቀጣችሁ ጊዜ በአካባቢአችሁ ለሚኖሩ ሕዝቦች የመሳለቂያ፥ የሽሙጥ፥ የማስጠንቀቂያ የድንጋጤ ምክንያት ትሆናላችሁ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። 16እንደ ገዳይ ቀስት የሆነውን ራብ የማመጣባችሁ እንዲያጠፋችሁ ነው፤ ደጋግሜ ራብን አመጣባችኋለሁ፤ የምግብ አቅርቦታችሁም እንዲቋረጥ አደርጋለሁ። 17ራብንና የዱር አራዊትን እለቅባችኋለሁ፤ ልጆቻችሁንም ይገድላሉ፤ ጦርነትንም አመጣባችኋለሁ፤ መቅሠፍትና ግድያም በመካከላችሁ ይስፋፋል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” #ራዕ. 6፥8።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 5: አማ05
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997