ትንቢተ ሕዝቅኤል መግቢያ
መግቢያ
ነቢዩ ሕዝቅኤል ኢየሩሳሌም ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስት መቶ ሰማኒያ ስድስት ዓመት ከመፍረስዋ በፊትና ከመፍረስዋም በኋላ በስደት በባቢሎን ይኖር ነበር፤ የእርሱ የትንቢት ቃል የተላለፈው በባቢሎን በስደት ለሚገኙትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ሕዝብ ነበር። ትንቢተ ሕዝቅኤል አራት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት።
1. የእግዚአብሔር ፍርድ በሕዝቡ ላይ ሊመጣ መቃረቡንና የኢየሩሳሌምም መያዝና መፍረስ የደረሰ መሆኑን የሚያስጠነቅቅ መልእክት፥
2. እግዚአብሔር ሕዝቡን የጨቈኑትንና ያሳሳቱትን ልዩ ልዩ መንግሥታት የሚቀጣ ስለ መሆኑ የተነገረ ቃል፥
3. ከኢየሩሳሌም መውደቅ በኋላ እስራኤልን ለማጽናናት የተሰጠ መልእክትና ወደፊትም መልካም ዕድል እንደሚገጥማት የተነገረ የተስፋ ቃል፥
4. ቤተ መቅደሱና የእስራኤል መንግሥት ወደ ቀድሞው ሁኔታ እንደሚመለስ ሕዝቅኤል ያቀረበው ሥዕላዊ መግለጫ ናቸው።
ሕዝቅኤል ታላቅ እምነትና አርቆ አስተዋይነት የነበረው ሰው ነበር፤ የወደፊቱን ሁኔታ አብዛኛውን ጊዜ የተመለከተው በራእይ መልክ ነበር፤ ከመልእክቱ አብዛኞቹ የተላለፉት ግልጥ በሆነ ምሳሌያዊ ድርጊት ነው። ሕዝቅኤል አጒልቶ ያሳየው ውስጣዊ የሆነ የልብና የመንፈስ መታደስ አስፈላጊ መሆኑንና እያንዳንዱ ሰው ስለ ራሱ ኃጢአት ተጠያቂ መሆኑን ነው፤ ከዚሁም ጋር የሕዝቡ ሕይወት ስለ መታደሱ ያለውን ተስፋ ገልጦአል፤ ሕዝቅኤል ካህንም ነቢይም እንደ መሆኑ መጠን ስለ ቤተ መቅደሱና ስለ ቅድስና አስፈላጊነት የተለየ ስሜት አሳይቶአል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
1. ሕዝቅኤል የእግዚአብሔርን ክብር ማየቱና የእርሱም ነቢይ እንዲሆን መመረጡ (1፥1—3፥27)
2. ይሁዳና ኢየሩሳሌም የሚደመሰሱ መሆናቸውን ሕዝቅኤል በምሳሌ ማስረዳቱ (4፥1—5፥17)
3. ጥፋት መቃረቡ (6፥1—7፥27)
4. የእግዚአብሔር ክብር ኃጢአተኛይቱን ኢየሩሳሌምን መተዉ (8፥1—11፥25)
5. የይሁዳና የኢየሩሳሌም ውድቀት (12፥1—24፥27)
6. በሌሎች አገሮች ላይ የተላለፈ ፍርድ (25፥1—32፥32)
7. ሕዝቡ ከኃጢአታቸው እንዲመለሱ ሕዝቅኤል ማስጠንቀቅ የሚገባው መሆኑ (33፥1-20)
8. የኢየሩሳሌም ውድቀት ዜና (33፥21-22)
9. ሕዝቡን እንደሚመልስና ይሁዳን እንደሚያድን እግዚአብሔር ተስፋ መስጠቱ (34፥1—37፥28)
10. ጎግ ተሸንፎ እስራኤል እንደምትመለስ (38፥1—39፥29)
11. ሕዝቅኤል ወደፊት ስለሚሠራው ቤተ መቅደስ ያየው ራእይ (40፥1—46፥24)
12. ከቤተ መቅደሱ ሥር ስለሚፈልቀው ውሃ (47፥1-12)
13. ለእስራኤላውያን የሚመለሰላቸው የጥንት ርስታቸው ድንበርና ለየነገዱ የተደረገ ክፍፍል (47፥13—48፥35)
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል መግቢያ: አማ05
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997