ኦሪት ዘፍጥረት 23
23
የሣራ መሞትና የአብርሃም የመቃብር ቦታ መግዛት
1ሣራ መቶ ኻያ ሰባት ዓመት ከኖረች በኋላ፥ 2በከነዓን ምድር ባለችው “ቂርያት አርባዕ” ተብላ በምትጠራው በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃም በሣራ ሞት ምክንያት እጅግ አዘነ፤ አለቀሰም።
3የሚስቱ አስከሬን ካለበት ስፍራ ተነሥቶ ወደ ሒታውያን ሄደና፥ 4“እኔ በመካከላችሁ በእንግድነት የምኖር ስደተኛ ነኝ፤ እባካችሁ የመቃብር ቦታ ሽጡልኝ፤ የሚስቴንም አስከሬን በዚያ ልቅበር” አላቸው። #ዕብ. 11፥9፤13፤ ሐ.ሥ. 7፥16።
5ሒታውያንም እንዲህ ብለው መለሱለት፥ 6“ጌታው፥ እስቲ ስማን፤ አንተ በመካከላችን እንደ ታላቅ መስፍን ነህ፤ ከመቃብሮቻችን ጥሩውን መርጠህ የሚስትህን አስከሬን እዚያ ቅበር፤ ሁላችንም ብንሆን የሚስትህን አስከሬን የምትቀብርበት መቃብር ልንሰጥህ ፈቃደኞች ነን” አሉት።
7ከዚህ በኋላ አብርሃም በሒታውያን ፊት እጅ ነሥቶ እንዲህ አለ፤ 8“የሚስቴን አስከሬን እዚህ እንድቀብር ከፈቀዳችሁልኝ የጾሐር ልጅ ዔፍሮን፥ 9በእርሻው ድንበር ላይ ያለችውን ማክፌላ የተባለችውን ድርብ ክፍል ያላትን ዋሻ እንዲሸጥልኝ ጠይቁልኝ፤ ይህ ስፍራ የመቃብር ቦታ እንዲሆንልኝ በእናንተ ፊት ሙሉ ዋጋ ከፍዬ እንድገዛው አድርጉልኝ።”
10ዔፍሮን ራሱ በከተማው በር አጠገብ በነበረው መሰብሰቢያ ስፍራ ከሌሎች ሒታውያን ጋር ተቀምጦ ነበር፤ ስለዚህ እዚያ የነበሩት ሰዎች ሁሉ እየሰሙ እንዲህ አለ፤ 11“ጌታው ስማ፤ እርሻውን በክልሉ ውስጥ ካለው ዋሻ ጋር ሰጥቼሃለሁ፤ ሙታንህን እንድትቀብርበት በወገኖቼ በሒታውያን ፊት ሰጥቼሃለሁ።”
12አብርሃም ግን በሒታውያን ፊት እንደገና እጅ ነሣና፥ 13ሁሉም እየሰሙ ዔፍሮንን “እባክህ አድምጠኝ፤ ቦታውን በሙሉ እገዛዋለሁ፤ እነሆ ዋጋውን ተቀበለኝና የሚስቴን አስከሬን እዚያ ወስጄ ልቅበር” አለው።
14ዔፍሮንም አብርሃምን እንዲህ ሲል መለሰለት፦ 15“ጌታዬ የመሬቱ ዋጋ አራት መቶ ብር ቢሆን ነው፤ ታዲያ ይህ በእኔና በእናንተ መካከል ምንድን ነው? ይልቅስ የሚስትህን አስከሬን እዚህ ቅበር።” 16አብርሃምም በነገሩ ተስማምቶ ዔፍሮን በሕዝቡ ፊት በተናገረው መሠረት በነጋዴዎች ሚዛን ልክ አራት መቶ ብር መዝኖ ሰጠው።
17በዚህ ዐይነት ከመምሬ በስተምሥራቅ ማክፌላ የተባለው የዔፍሮን ቦታ የአብርሃም ርስት ሆነ፤ ይህም ቦታ እርሻውን፥ በውስጡ ያለውን ዋሻና በእርሻው ክልል ውስጥ ያለውን ዛፍ ሁሉ ያጠቃልላል። 18በዚያም ተገኝተው የነበሩት ሒታውያን ሁሉ የአብርሃም ርስት መሆኑን አረጋገጡ።
19ከዚህ በኋላ አብርሃም በከነዓን ምድር ባለችው በዚህችው ዋሻ የሚስቱን የሣራን አስከሬን ቀበረ፤ 20ስለዚህ የሒታውያን የነበረው እርሻ በውስጡ ካለው ዋሻ ጋር የአብርሃም የመቃብር ርስት ሆነ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 23: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997