ኦሪት ዘፍጥረት 28
28
1ይስሐቅ ያዕቆብን ጠርቶ መረቀው፤ እንዲህም ሲል አዘዘው፤ “ከነዓናዊት ሴት እንዳታገባ፤ 2ይልቅስ ተነሥተህ በመስጴጦምያ ወዳለው ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ሂድ፤ እዚያም ከአጐትህ ከላባ ሴቶች ልጆች አንዷን አግባ፤ 3ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ይባርክህ! ብዙ ልጆችም ይስጥህ! የብዙ ሕዝቦችም አባት ያድርግህ! 4አብርሃምን እንደ ባረከ አንተንና ዘርህን ይባርክ! ይህንንም ለአብርሃም ሰጥቶት የነበረውንና አንተም ስደተኛ ሆነህ የኖርክበትን ምድር ርስት አድርጎ ይስጥህ!” #ዘፍ. 17፥4-8።
5በዚህ ሁኔታ ይስሐቅ ያዕቆብን አሰናበተው፤ ያዕቆብም በመስጴጦምያ ወደሚኖረው ወደ ላባ ሄደ፤ ላባ የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም ነበረ፤ አባቱም ሶርያዊው ባቱኤል ነበር።
ዔሳው ሌላ ሚስት ማግባቱ
6ይስሐቅ ያዕቆብን እንደ መረቀውና ሚስት እንዲፈልግ ወደ መስጴጦምያ እንደ ላከው ዔሳው ተረዳ፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ሲመርቀው፦ “ከነዓናዊት ሴት እንዳታገባ” ብሎ ያዘዘው መሆኑንም ሰማ፤ 7ያዕቆብ ለአባቱና ለእናቱ በመታዘዝ ወደ መስጴጦምያ መሄዱንም ተረዳ፤ 8በዚህም አባቱ ይስሐቅ የከነዓናውያንን ሴቶች እንደማይወድ ዔሳው ተገነዘበ፤ 9ስለዚህ ከዚህ በፊት ካገባቸው ሌላ በተጨማሪ ወደ አብርሃም ልጅ ወደ እስማኤል ሄዶ ልጁን ማሕላትን አገባ፤ እርስዋም የነባዮት እኅት ናት።
ያዕቆብ በቤትኤል ያየው ሕልም
10ያዕቆብ ቤርሳቤህን ትቶ ወደ ካራን ለመሄድ ተነሣ፤ 11ፀሐይ በጠለቀች ጊዜ ወደ አንድ ስፍራ መጥቶ ዐረፈ፤ በዚያም አንድ ድንጋይ ተንተርሶ ተኛ፤ 12በሕልሙም ከመሬት እስከ ሰማይ የሚደርስ መሰላል አየ፤ በመሰላሉም የእግዚአብሔር መላእክት ወደ ላይ ይወጡና ወደ ታች ይወርዱ ነበር። #ዮሐ. 1፥51። 13እግዚአብሔርም በአጠገቡ ቆሞ እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ ለአንተና ለትውልድህ እንዲሆን ይህን የተኛህበትን ምድር እሰጥሃለሁ፤ #ዘፍ. 13፥14-15። 14ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ እነርሱ በሁሉ አቅጣጫ ይዞታቸውን ያስፋፋሉ፤ በአንተና በዘርህ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ። #ዘፍ. 12፥3፤ 22፥18። 15አይዞህ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበትም ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህም ምድር በደኅና እመልስሃለሁ፤ የገባሁልህን ቃል ኪዳን ሁሉ እፈጽምልሃለሁ፤ ከቶም አልተውህም።”
16ያዕቆብም ከእንቅልፉ ነቃና “በእርግጥ እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ አለ፤ እኔ ግን ይህን አላወቅሁም ነበር” አለ። 17በጣም ፈርቶም ስለ ነበር “ይህ እንዴት የሚያስፈራ ቦታ ነው! ይህ የእግዚአብሔር ቤት መሆን አለበት፤ ወደ ሰማይ የሚያስገባው በር ይህ ነው” አለ።
18ያዕቆብ በማግሥቱ ጠዋት በማለዳ ተነሣ፤ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ መታሰቢያ እንዲሆን እንደ ሐውልት አቆመው፤ በላዩ ላይም የወይራ ዘይት አፈሰሰበት። 19ያንንም ስፍራ “ቤትኤል” ብሎ ሰየመው፤ ይህ ስፍራ ከዚያ በፊት ሎዛ እየተባለ ይጠራ ነበር። #28፥19 ቤትኤል፦ በዕብራይስጥ “የእግዚአብሔር ቤት” ማለት ነው።
20ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ለእግዚአብሔር ተሳለ፦ “ከእኔ ጋር ሆነህ በምሄድበት መንገድ ብትጠብቀኝ፥ የሚያስፈልገኝን ምግብና ልብስ ብትሰጠኝ፥ 21ወደ አባቴም ቤት በሰላም ብትመልሰኝ፥ አንተ አምላኬ ትሆናለህ፤ 22ይህ ለመታሰቢያነት ያቆምኩት ድንጋይ ወደ ፊት የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፤ ከምትሰጠኝም ሁሉ ከዐሥር አንዱን እጅ ለአንተ እሰጣለሁ።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 28: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997