ኦሪት ዘፍጥረት 30
30
1ራሔል ለያዕቆብ አንድም ልጅ ለመውለድ አለመቻሏን ባወቀች ጊዜ በእኅቷ ቀናችባት፤ ስለዚህ ያዕቆብን “ልጅ ስጠኝ፤ አለበለዚያ እሞታለሁ” አለችው።
2ያዕቆብም ራሔልን ተቈጥቶ “ልጅ ልሰጥሽና ልከለክልሽ የምችል እግዚአብሔር መሰልኩሽን?” አላት።
3እርስዋም “እነሆ፥ አገልጋዬ ባላ እዚህ አለች፤ በእኔ ምትክ ልጅ እንድትወልድልኝ ወደ እርስዋ ግባ፤ በዚህ ዐይነት በእርስዋ አማካይነት የልጆች እናት እሆናለሁ” አለችው። 4ስለዚህ ባላን እንደ ሚስት አድርጋ ሰጠችው፤ ያዕቆብም ወደ እርስዋ ገባ። 5ባላም ፀነሰችና ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 6ራሔልም “እግዚአብሔር ፈረደልኝ፤ ጸሎቴንም ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጠኝ” አለች፤ በዚህም ምክንያት ስሙን ዳን ብላ ጠራችው። #30፥6 ዳን፦ በዕብራይስጥ “ፈረደልኝ” ማለት ነው። 7የራሔል አገልጋይ ባላ ዳግመኛ ፀነሰችና ለያዕቆብ ሌላ ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ 8ራሔልም “ከእኅቴ ጋር ብርቱ ትግል ታግዬ አሸነፍኳት” አለች፤ ስለዚህ ስሙን ንፍታሌም ብላ ጠራችው። #30፥8 ንፍታሌም፦ በዕብራይስጥ “ናፍታሊ” ሲሆን “ትግል” ማለት ነው።
9ልያም መውለድ እንዳቆመች በተገነዘበች ጊዜ አገልጋይዋን ዚልፋን እንደ ሚስት አድርጋ ለያዕቆብ ሰጠችው፤ 10የልያ አገልጋይ ዚልፋ ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 11ልያም “እንዴት የታደልኩ ነኝ!” ስትል ስሙን ጋድ ብላ ጠራችው። #30፥11 ጋድ፦ በዕብራይስጥ “መልካም ዕድል” ማለት ነው። 12የልያ አገልጋይ ዚልፋ ለያዕቆብ ሌላ ወንድ ልጅ ወለደችለት። 13ልያም “እጅግ ደስ ብሎኛል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ሴቶች ሁሉ ‘ደስተኛዋ ሴት!’ ይሉኛል” ስትል ስሙን አሴር ብላ ጠራችው። #30፥13 አሴር፦ “አሴር” ሲሆን “ደስታ” ማለት ነው።
14በስንዴ መከር ወራት ሮቤል ወደ ዱር ሄዶ እንኮይ አገኘ፤ ለእናቱ ለልያም አመጣላት፤ ራሔል ልያን “እባክሽ ልጅሽ ካመጣልሽ እንኮይ ስጪኝ” አለቻት።
15ልያም “ባሌን የነጠቅሽኝ አንሶሽ፥ አሁን ደግሞ ልጄ ያመጣልኝን እንኮይ መቀማት ትፈልጊያለሽን?” አለቻት።
ራሔልም “ከልጅሽ እንኮይ ስጪኝና ዛሬ ሌሊት ያዕቆብ ካንቺ ጋር ይደር” አለቻት።
16በዚያን ምሽት ያዕቆብ ከዱር ሲመለስ፥ ልያ ከቤት ወደ እርሱ ወጥታ “በልጄ እንኮይ ስለ ገዛሁህ ዛሬ ሌሊት የምታድረው ከእኔ ጋር ነው” አለችው፤ ስለዚህ በዚያን ሌሊት ከእርስዋ ጋር ዐደረ።
17እግዚአብሔር የልያን ጸሎት ሰማ፤ ስለዚህ ፀነሰችና ለያዕቆብ አምስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደችለት። 18ልያም “አገልጋዬን ለባሌ በመስጠቴ እግዚአብሔር ደመወዜን ከፈለኝ” ስትል ይሳኮር ብላ ጠራችው፤ #30፥18 ይሳኮር፦ በዕብራይስጥ “ደመወዝ” ማለት ነው። 19ልያ ዳግመኛ ፀነሰችና ለያዕቆብ ስድስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ 20እርስዋም “እግዚአብሔር መልካም ስጦታ ሰጠኝ፤ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድኩለት አሁን ባሌ ያከብረኛል” ስትል ስሙን ዛብሎን ብላ ጠራችው። #30፥20 ዛብሎን፦ በዕብራይስጥ “ማክበር” ማለት ነው። 21ከዚህ በኋላ ሴት ልጅ ወለደች፤ ስሟንም ዲና ብላ ጠራቻት። #30፥21 ዲና፦ በዕብራይስጥ “ፈረደ” ማለት ነው።
22እግዚአብሔርም ራሔልን አሰበ፤ ጸሎትዋንም ሰምቶ ልጅ እንድትወልድ አደረጋት፤ 23ፀንሳም ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እግዚአብሔር ወንድ ልጅ ሰጠኝ፤ ስድቤንም አስወገደልኝ፤ 24ደግሞም ሌላ ወንድ ልጅ ይጨመርልኝ” ስትል ስሙን ዮሴፍ ብላ ጠራችው። #30፥24 ዮሴፍ፦ በዕብራይስጥ “ይጨምርልኝ” ወይም “አስወገደልኝ” ማለት ነው።
ያዕቆብ ስለ ደመወዝ ከላባ ጋር መከራከሩ
25ራሔል ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ “ወደ ተወለድኩበት አገር እንድመለስ አሰናብተኝ፤ 26አንተን በማገልገል ያገኘኋቸውን ሚስቶቼንና ልጆቼን ስጠኝና ልሂድ፤ ምን ያኽል አገልግሎት እንዳበረከትኩልህ ታውቃለህ።”
27ላባም “በልዩ መገለጥ እንደ ተረዳሁት በአንተ ምክንያት እግዚአብሔር የባረከኝ መሆኑን እንድገልጽልህ ፍቀድልኝ፤ 28የምትፈልገውን ደመወዝ ልክ ንገረኝና እከፍልሃለሁ” አለው።
29ያዕቆብም እንዲህ አለው “እንዴት እንዳገለገልኩህና የከብትህም መንጋ በእኔ ጠባቂነት እንዴት እንደ ረባልህ አንተ ታውቃለህ፤ 30እኔ ከመምጣቴ በፊት ጥቂት የነበሩት መንጋዎችህ አሁን እጅግ በዝተዋል፤ እኔ በደረስኩበት ስፍራ ሁሉ እግዚአብሔር በረከትን ሰጥቶሃል፤ የምሠራውስ መቼ ለቤተሰቤ የሚጠቅም ነገር ነው?” አለው።
31ላባም “ታዲያ ምን ያኽል ልክፈልህ?” ብሎ ጠየቀው።
ያዕቆብም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ የምልህን አንድ ነገር ብቻ ብታደርግልኝ መንጋህን ማሰማራቴንና መጠበቄን እቀጥላለሁ፤ 32ዛሬ በመንጋዎችህ መካከል ልለፍና ዝንጒርጒርና ነቊጣ፥ ጥቊርም የሆኑትን በጎች ሁሉ ልለይ፤ እንዲሁም ነቊጣና ዝንጒርጒር የሆኑትን ፍየሎች እመርጣለሁ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ፤ 33በዚህ ዐይነት ታማኝነቴ ወደ ፊት ይታያል፤ ደመወዜን ለመቈጣጠር ስትመጣ ዝንጒርጒር ያልሆነ ወይም ነቊጣ የሌለበት ፍየል ብታገኝ፥ እንዲሁም ጥቊር ያልሆነ በግ ብታገኝ የተሰረቀ መሆኑን መረዳት ትችላለህ።”
34ላባም “እሺ አንተ ባልከው እስማማለሁ” አለ። 35ነገር ግን በዚያኑ ቀን ላባ ሸመልመሌ የሆኑትን ወይም ነቊጣ ያለባቸውን ወንዶች ፍየሎችና ዝንጒርጒር የሆኑትን ነጭ ነጠብጣብ ያለባቸውን ሴቶች ፍየሎች መረጠ፤ እንዲሁም ጥቊር የሆኑትን በጎች ለየና ልጆቹ እንዲጠብቁአቸው አደረገ። 36ከዚህ በኋላ ላባ መንጋውን ነድቶ የሦስት ቀን መንገድ ያኽል ከያዕቆብ ርቆ ሄደ፤ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን መንጋዎች መጠበቁን ቀጠለ።
37ያዕቆብም ልብን፥ ለውዝና አስታ ከሚባሉ እንጨቶች እርጥብ በትሮችን ወሰደ፤ በበትሮቹ ውስጥ ያለው ነጭ እንዲታይ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው፤ 38መንጋዎቹ ውሃ ለመጠጣት ሲመጡ ከፊት ለፊት እንዲያዩአቸው የተላጡትን በትሮች በውሃ ማጠጫዎቹ ውስጥ አደረጋቸው፤ መንጋዎቹ ውሃ ለመጠጣት በሚመጡበት ጊዜ፥ 39በዱላዎቹ ፊት ለፊት ፍትወት እየተሰማቸው ይጐመዡ ነበር፤ ስለዚህ ሸመልመሌ፥ ዝንጒርጒርና ነቊጣ የሆኑ ግልገሎችን ወለዱ። 40ያዕቆብ እነዚህን ግልገሎች ለብቻ ለየ፤ የቀሩትን ግን ዝንጒርጒርና ጥቊር በሆኑት በላባ መንጋዎች ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በዚህ ዐይነት የራሱን መንጋ ወደ ላባ መንጋ ሳይቀላቅል ለብቻ አቆማቸው።
41ጤናማና ብርቱ የሆኑት መንጋዎች ፍትወት እየተሰማቸው ሲጐመዡ ያዕቆብ በትሮቹን በፊታቸው ባሉት ውሃ መጠጫዎች ውስጥ ያኖራቸው ነበር፤ በዚህ ዐይነት በትሮቹን እያዩ ይፀንሱ ነበር። 42ነገር ግን በትሮቹን በደካሞቹ መንጋዎች ፊት ለፊት አያስቀምጣቸውም ነበር፤ በዚህ ዐይነት ደካሞቹ መንጋዎች ለላባ ሲሆኑ ብርቱዎቹ ግን የያዕቆብ ሆኑ። 43በዚህ አኳኋን ያዕቆብ እጅግ ባለ ጸጋ ሆነ፤ ብዙ መንጋዎች፤ ሴቶችና ወንዶች አገልጋዮች፥ ብዙ ግመሎችና አህዮችም ነበሩት።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 30: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997