ኦሪት ዘፍጥረት 32
32
ከዔሳው ጋር ለመገናኘት የያዕቆብ ዝግጅት
1ያዕቆብ በጒዞ ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መላእክት በመንገድ ተገናኙት። 2ባያቸውም ጊዜ “እግዚአብሔር ከሠራዊቱ ጋር የሚሠፍርበት ቦታ ነው” አለ፤ ስለዚህ ያንን ቦታ ማሕናይም ብሎ ጠራው። #32፥2 ማሕናይም፦ በዕብራይስጥ “ሰፈሮች” ማለት ነው።
3ከዚህ በኋላ ያዕቆብ በኤዶም አገር ሤዒር ተብላ በምትጠራው ምድር ወደሚኖረው ወደ ወንድሙ ወደ ዔሳው መልእክተኞች አስቀድሞ ላከ። 4እንዲህም በማለት አዘዛቸው፥ “ለጌታዬ ለዔሳው እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤ ‘ታማኝ አገልጋይህ እኔ ያዕቆብ እስከ አሁን የቈየሁት ከላባ ጋር እንደ ነበር ልነግርህ እወዳለሁ፤ 5እነሆ፥ አሁን ብዙ ከብቶች፥ አህዮች፥ በጎችና ፍየሎች እንዲሁም አሽከሮችና ገረዶች አሉኝ፤ ይህን መልእክት የላክሁብህ በአንተ ዘንድ ሞገስ አገኛለሁ በሚል ተስፋ ነው።’ ”
6መልእክተኞቹም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው መጡና “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ከአንተ ጋር ለመገናኘት በመምጣት ላይ ነው፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ” አሉት። 7በዚህ ጊዜ ያዕቆብ እጅግ በመፍራት ተጨነቀ፤ አብረውት የነበሩትንም ሰዎች በሁለት ክፍል መደባቸው፤ እንዲሁም በጎቹን፥ ፍየሎቹን፥ ከብቶቹንና ግመሎቹን በሁለት በሁለት መደባቸው። 8ይህንንም ያደረገው “ዔሳው መጥቶ በድንገተኛ አደጋ የመጀመሪያውን ክፍል ቢያጠቃ፥ ሌላው ክፍል ሊያመልጥ ይችላል” ብሎ በማሰብ ነው።
9ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ጸለየ፤ “የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ ሆይ! ልመናዬን አድምጥ፤ አምላክ ሆይ፥ ‘ወደ ትውልድ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፤ እዚያም መልካም ነገር እንዲሆንልህ አደርጋለሁ’ ብለኸኝ ነበር። 10እኔ ባሪያህ ይህን ያኽል ቸርነትና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ስመጣ ከምመረኰዘው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን እነዚህን በሁለት ቡድን የተከፈሉ ወገኖች ይዤ ተመልሻለሁ። 11በእኔ ላይ አደጋ በመጣል ሴቶችና ሕፃናት እንኳ ሳይቀሩ ያጠፋናል ብዬ ስለ ፈራሁ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ 12‘መልካም ነገር አደርጋለሁ፤ ዘርህንም ሊቈጠር እንደማይቻል እንደ ባሕር ዳር አሸዋ አበዛልሃለሁ’ ያልከውን አስታውስ።” #ዘፍ. 22፥17።
13እዚያም ዐደረ፤ በማግስቱም ካለው ነገር ሁሉ ለወንድሙ ለዔሳው ስጦታ የሚሆን ነገር መርጦ አዘጋጀ፤ 14በዚህ ዐይነት ሁለት መቶ እንስት ፍየሎች፥ ኻያ ተባዕት ፍየሎች፥ ሁለት መቶ እንስት በጎች፥ ኻያ ተባዕት በጎች፤ 15ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎች ከነግልገሎቻቸው፥ አርባ ላሞች፥ ዐሥር ኰርማዎች፥ ኻያ እንስት አህዮችና ዐሥር ተባዕት አህዮች መረጠ፤ 16እነዚህንም በየመንጋው ከፈለና ለእያንዳንዳቸው እረኞች መደበላቸው፤ እረኞቹንም “ከእኔ ቀድማችሁ ሂዱ፤ በየመንጋው መካከል ርቀት እንዲኖር አድርጋችሁ፥ በመከታተል ሂዱ” አላቸው። 17የመጀመሪያዎቹንም እረኞች እንዲህ በማለት አዘዛቸው፤ “ወንድሜ ዔሳው በመንገድ አግኝቶ ‘የማን ሰዎች ናችሁ? ወዴትስ ትሄዳላችሁ? እነዚህ የምትነዱአቸው ከብቶች የማን ናቸው?’ ብሎ የጠየቃችሁ እንደ ሆነ፥ 18‘እነዚህ ከብቶች የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው፤ እርሱ እነዚህን የላከው ለጌታዬ ለዔሳው ስጦታ የሚሆን ነው፤ እነሆ ያዕቆብ ከኋላችን ነው’ ብላችሁ ንገሩት።” 19ለሁለተኛውም ለሦስተኛውም ክፍል እረኞችና ለቀሩትም የመንጋ ጠባቂዎች “እናንተም ዔሳውን ስታገኙት እንደዚሁ ንገሩት፤ 20‘በተለይም አገልጋይህ ያዕቆብ ከበስተኋላ እየመጣ ነው’ ብላችሁ ንገሩት” አላቸው። ይህንንም ያለበት ምክንያት “እኔ ከመድረሴ በፊት በሚደርስለት ስጦታ ቊጣውን አበርድ ይሆናል፤ በኋላም በማገኘው ጊዜ በደስታ ይቀበለኛል” በሚል ሐሳብ ነው። 21በዚህ ዐይነት ስጦታውን አስቀድሞ ከላከ በኋላ፥ እዚያው በሰፈሩበት ቦታ ዐደረ።
ያዕቆብ ከእግዚአብሔር ጋር መታገሉ
22በዚያኑ ሌሊት ያዕቆብ ተነሣ ሁለቱን ሚስቶቹን፥ ሁለቱን ሴቶች አገልጋዮቹንና፥ ዐሥራ አንዱን ልጆቹን ይዞ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ። 23እነርሱን ካሻገረም በኋላ ያለውን ጓዝ ሁሉ አሻገረ። 24እርሱ ግን በስተማዶ ለብቻው ቀረ፤
ከዚህ በኋላ ሌሊቱ እስኪነጋ ድረስ አንድ ሰው ሲታገለው ዐደረ። 25ያ ሰው ያዕቆብን በትግል ማሸነፍ እንዳቃተው ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ መታው፤ ያዕቆብም በሚታገልበት ጊዜ ጭኑ ከመገጣጠሚያው ላይ ተለያየ፤ 26ከዚህ በኋላ ሰውየው “ሌሊቱ ሊነጋ ስለ ሆነ ልቀቀኝ” አለ።
ያዕቆብም “ካልባረክኸኝ አለቅህም” አለው። #ሆሴዕ 12፥3-4።
27ሰውየውም “ስምህ ማን ነው?” አለው።
“ስሜ ያዕቆብ ነው” አለው።
28ሰውየውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ከእግዚአብሔርም ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃል፤ ስለዚህ ስምህ ‘እስራኤል’ ይባላል” አለው። #32፥28 እስራኤል፦ በዕብራይስጥ “ይታገላል” ማለት ነው። #ዘፍ. 35፥10።
29ያዕቆብም “አንተስ ስምህ ማን ነው?” አለው።
ሰውየውም “ስሜን ለማወቅ የምትፈልገው ለምንድን ነው?” አለውና ያዕቆብን ባረከው። #መሳ. 13፥7-18።
30ያዕቆብም “እኔ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አይቼ እነሆ፥ በሕይወት እገኛለሁ” አለ። በዚህም ምክንያት ያንን ቦታ “ጵንኤል” ብሎ ጠራው። #32፥30 ጵንኤል፦ በዕብራይስጥ “የእግዚአብሔር ፊት” ማለት ነው። 31ያዕቆብ ከጵንኤል ተነሥቶ ሲሄድ ፀሐይ ወጥታ ነበር፤ በጭኑም ሕመም ምክንያት ያነክስ ነበር። 32ያዕቆብ ከሰውየው ጋር ሲታገል ሰውየው ሹልዳውን መቶት ስለ ነበር እስራኤላውያን እስከ ዛሬ ድረስ በጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን የሹልዳ ሥጋ አይበሉም።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 32: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997