ኦሪት ዘፍጥረት 35
35
እግዚአብሔር ያዕቆብን በቤትኤል መባረኩ
1እግዚአብሔር ያዕቆብን “አሁን ተነሥተህ ወደ ቤትኤል ሂድና እዚያ ኑር፤ በዚያም ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድክ ጊዜ ለተገለጥኩልህ አምላክ ለእኔ መሠዊያ ሥራ” አለው። #ዘፍ. 28፥11-17።
2ስለዚህ ያዕቆብ ለቤተሰቡና አብረውት ለነበሩት ሰዎች ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ንጹሕ ልብስም ልበሱ፤ 3ከዚህ ተነሥተን ወደ ቤትኤል እንውጣ፤ በዚያም ከዚህ በፊት በተቸገርኩ ጊዜ ጸሎቴን ሰምቶ ለረዳኝና በሄድኩበት ስፍራ ሁሉ ከእኔ ላልተለየኝ አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።” 4ስለዚህም በእርሱ ዘንድ የነበሩትን ባዕዳን አማልክት ሁሉ አምጥተው ለያዕቆብ ሰጡት፤ እንዲሁም በየጆሮአቸው አድርገውት የነበረውን ጒትቻ ሁሉ አውልቀው ሰጡት፤ እርሱም ሁሉንም ወሰደና በሴኬም አጠገብ በነበረው የወርካ ዛፍ ሥር ቀበራቸው።
5ያዕቆብና ልጆቹ ያንን ስፍራ ትተው ለመሄድ ተነሡ፤ እግዚአብሔር በዙሪያቸው በነበሩት ሰዎች ላይ ፍርሀትና ድንጋጤ ስላሳደረባቸው ሊያሳድዱአቸው አልደፈሩም። 6ያዕቆብ አብረውት ከነበሩት ሰዎች ጋር ሆኖ ወደ ሎዛ ደረሰ፤ ሎዛ ቤትኤል ተብላ የምትጠራው በከነዓን ምድር የምትገኝ ስፍራ ናት። 7ያዕቆብ እዚያ መሠዊያ ሠርቶ “ኤል ቤትኤል” ብሎ ሰየመው፤ ከወንድሙ ፊት ሸሽቶ በሄደበት ጊዜ እግዚአብሔር የተገለጠለት በዚህ ስፍራ ነበር። #35፥7 ኤል ቤትኤል፦ በዕብራይስጥ “የቤትኤል አምላክ” ማለት ነው። 8እዚያም የርብቃ ሞግዚት ዴቦራ ሞተች፤ ከቤትኤል በስተደቡብ ባለውም ወርካ ሥር ተቀበረች፤ ስለዚህም ያ ዛፍ አሎን ባኩት ተባለ። #35፥8 አሎን ባኩት፦ በዕብራይስጥ “የለቅሶ ወርካ” ማለት ነው።
9ያዕቆብ ከመስጴጦምያ በተመለሰ ጊዜ እግዚአብሔር ዳግመኛ ተገለጠለትና ባረከው። 10ደግሞም “ስምህ ያዕቆብ ነው፤ ከእንግዲህ ወዲህ ግን እስራኤል ትባላለህ እንጂ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም” አለው። ስለዚህም እግዚአብሔር ያዕቆብን “እስራኤል” ብሎ ጠራው። #ዘፍ. 32፥28። 11ደግሞም እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ፤ ብዙ ልጆች ይኑርህ፤ ዘርህም ይብዛ፤ የብዙ ሕዝብ አባት ሁን፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወለዱ። 12ለአብርሃምና ለይስሐቅ የሰጠሁትን ምድር ለአንተም እሰጥሃለሁ፤ ይህንኑ ምድር ከአንተም በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ።” #ዘፍ. 17፥4-8። 13እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ከዚያ ስፍራ ወደ ላይ ወጣ። 14ያዕቆብም፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ስፍራ መታሰቢያ የሚሆን የተቀደሰ ዐምድ አቆመ፤ የወይን ጠጅና ዘይት በላዩ አፈሰሰበት፤ 15ያዕቆብ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የተነጋገረበትን ይህንኑ ስፍራ “ቤትኤል” ብሎ ጠራው። #ዘፍ. 28፥18-19።
የራሔል ሞት
16ያዕቆብና ቤተሰቡ ከቤትኤል ለቀው ሄዱ፤ ወደ ኤፍራታ ሊደርሱ ጥቂት ሲቀራቸው የራሔል መውለጃ ጊዜ ደረሰና በከባድ ምጥ ተያዘች። 17ምጧ እየበረታ በሄደ ጊዜ አዋላጅዋ “ራሔል ሆይ፥ ሌላ ወንድ ልጅ መውለድሽ ስለ ሆነ አይዞሽ አትፍሪ” አለቻት። 18እርስዋ ግን ልትሞት ታጣጥር ስለ ነበር ከመሞቷ በፊት ልጅዋን “ቤንኦኒ” አለችው፤ አባቱ ግን “ብንያም” አለው። #35፥18 ቤንኦኒ፦ በዕብራይስጥ “የሐዘኔ ልጅ” ማለት ነው። #35፥18 ብንያም፦ በዕብራይስጥ “ቢንያሚን” “ቀኝ እጄ” ሲሆን “የመልካም ዕድል ልጅ” ማለት ነው።
19ከዚህ በኋላ ወዲያውኑ ራሔል ሞተች፤ አሁን ቤተ ልሔም ተብሎ በሚጠራው ወደ ኤፍራታ በሚወስደው መንገድ ዳር ተቀበረች። 20ያዕቆብም በራሔል መቃብር ላይ ለመታሰቢያዋ የሚሆን የድንጋይ ሐውልት አቆመ። ይህም ሐውልት እስከ ዛሬ ድረስ የራሔልን መቃብር ያመለክታል። 21ያዕቆብ ጒዞውን ቀጥሎ በዔዴር ግንብ ባሻገር ድንኳን ተክሎ ሰፈረ።
የያዕቆብ ልጆች
(1ዜ.መ. 2፥1-2)
22ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፥ ሮቤል ወደ አባቱ ቁባት ወደ ባላ ገባ። ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ። የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው። #ዘፍ. 49፥4።
23የልያ ልጆች፥ የያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮርና ዛብሎን ናቸው።
24የራሔል ልጆች፥ ዮሴፍና ብንያም ናቸው።
25የራሔል አገልጋይ የነበረችው የባላ ልጆች፥ ዳንና ንፍታሌም ናቸው።
26የልያ አገልጋይ የነበረችው የዚልፋ ልጆች ጋድና አሴር ናቸው።
እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በመስጴጦምያ ሳለ የተወለዱለት ናቸው።
የይስሐቅ ሞት
27ያዕቆብ በኬብሮን አጠገብ መምሬ ወደምትባል ስፍራ ወደሚኖረው አባቱ ወደ ይስሐቅ ሄደ፤ ይህም ስፍራ አብርሃምና ይስሐቅ የኖሩበት ነው። #ዘፍ. 13፥18። 28ይስሐቅ መቶ ሰማኒያ ዓመት ኖረ፤ 29ዕድሜ ጠግቦ ካረጀ በኋላ ሞተ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 35: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997