ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 2
2
ታላቁ መዳን
1ስለዚህ ከሰማነው ነገር ተንሸራትተን እንዳንወድቅ ስለ ሰማነው ነገር በጣም መጠንቀቅ አለብን። 2በመላእክት አማካይነት የተነገረው ቃል እርግጠኛ ሆኖአል፤ ይህንንም ቃል የሚተላለፍና ለዚህም ቃል የማይታዘዝ ተገቢውን ቅጣት ይቀበላል፤ 3ታዲያ፥ እኛ ይህን ታላቅ መዳን ችላ የምንል ከሆንን እንዴት እናመልጣለን? ይህን መዳን በመጀመሪያ ያበሠረው ጌታ ራሱ ነው፤ ከእርሱ የሰሙትም ሰዎች ይህንኑ አረጋግጠውልናል። 4እግዚአብሔርም ደግሞ ምልክቶችን፥ ድንቅ ነገሮችን፥ ልዩ ልዩ ተአምራትን በማድረግና እንደ ፈቃዱ በታደሉት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አማካይነት ምስክርነታቸውን አጽንቶአል።
ለሰው ዘር መዳን መሪ ኢየሱስ መሆኑ
5እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚመጣውን፥ ይህን የምንነጋገርበትን ዓለም ለመላእክት አላስገዛም 6እንዲያውም በቅዱሳት መጻሕፍት በአንድ ስፍራ እንዲህ ተብሎአል፦
“አንተ እርሱን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?
ለእርሱስ ትጠነቀቅለት ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?
7ጥቂት ከመላእክት አሳነስከው፤
የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንክለት፥
በእጆችህም ሥራ ላይ ሾምከው፤ #2፥7 አንዳንድ ትርጒሞች “በእጆችህ ሥራ ሾምከው” የሚለውን ይጨምራሉ።
8ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር አደረግህለት።” #መዝ. 8፥4-6።
ሁሉን ነገር በሥልጣኑ ሥር ሲያደርግ፤ በሥልጣኑ ሥር ሳያደርግለት ያስቀረው ምንም ነገር የለም። ነገር ግን አሁን እንዳለ ሁሉ ነገር በእርሱ ሥልጣን ሥር እንደ ሆነ ገና አላየንም። 9አሁን ግን ከመላእክት ጥቂት ጊዜ ዝቅ ብሎ የነበረውን፥ የሞትን መከራ በመቀበሉ ምክንያት የክብርና የምስጋና ዘውድ የጫነውን ኢየሱስን እናያለን፤ እርሱ በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሁላችን ሞቶአል። 10ሁሉ ነገር በእርሱና ለእርሱ የተፈጠረው እግዚአብሔር ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት የመዳናቸውን መሪ ኢየሱስን በመከራ ፍጹም እንዲሆን እንዲያደርገው ተገባው።
11ሰዎችን ቅዱሳን የሚያደርጋቸውና በእርሱ ቅዱሳን የሆኑትም ሰዎች የአንድ አባት ልጆች ናቸው፤ በዚህ ምክንያት ኢየሱስ እነርሱን “ወንድሞቼ” ብሎ ለመጥራት አያፍርም። 12ስለዚህም በቅዱሳት መጻሕፍት
“ስምህን ለወንድሞቼ አበሥራለሁ፤
በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ” ይላል፤ #መዝ. 22፥22።
13እንዲሁም “እምነቴን በእርሱ ላይ እጥላለሁ” ይላል፤ #ኢሳ. 8፥17-18።
እንደገናም “እነሆኝ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች እዚህ ነን” ይላል።
14ስለዚህ እነዚህ ልጆች ሥጋና ደም ያላቸው ሰዎች እንደ መሆናቸው ኢየሱስም እንደ እነርሱ ሰው ሆነ፤ ይህን ያደረገውም በሞቱ አማካይነት በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ዲያብሎስን ለማጥፋት ነው፤ 15እንዲሁም ሞትን በመፍራት ምክንያት ዕድሜ ልካቸውን በባርነት ይገዙ የነበሩትን ለመዋጀት ነው። 16የኢየሱስ ፍላጎት መላእክትን ሳይሆን የአብርሃምን ዘር ለመርዳት ነው፤ 17ስለዚህ በሁሉም ነገር እንደ ወንድሞቹ መሆን ነበረበት፤ በዚህ ዐይነት የሰዎችን ኃጢአት ለመደምሰስ ብሎ እግዚአብሔርን ለማገልገል ታማኝና መሐሪ የካህናት አለቃ ሆነ። 18እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን መርዳት ይችላል።
Currently Selected:
ወደ ዕብራውያን የተላከ መልእክት 2: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997