ትንቢተ ሆሴዕ 8
8
የእስራኤል ሕዝብ ጣዖት በማምለካቸው እንደ ተገሠጹ
1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ቃል ኪዳኔን ስላፈረሱና ሕጌን ስለ ተላለፉ በቤቴ ላይ ጠላት እንደ ጆፌ አሞራ ያንዣበበ ስለ ሆነ የማስጠንቀቂያ መለከት ንፉ!” 2እነርሱም፥ “አምላክ ሆይ! እኛ ሕዝብህ እናውቅሃለን” እያሉ ወደ እኔ ይጮኻሉ፤ 3ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ በጎ ነገርን ስለ ጠሉ ጠላት ያሳድዳቸዋል።
4“ያለ እኔ ፈቃድ ነገሥታትን አነገሡ፤ እኔን ሳይጠይቁ መሳፍንትን መርጠው ሾሙ፤ ከብራቸውና ከወርቃቸው ለገዛ ራሳቸው መጥፊያ የሆኑትን ጣዖቶችን ሠሩ። 5የሰማርያ ሕዝብ ሆይ! በጥጃ ምስል የተሠራ ጣዖታችሁን ተጸይፌአለሁ፤ ቊጣዬ በእናንተ ላይ እንደ እሳት ይነዳል፤ ከበደል የማትነጹት እስከ መቼ ነው? 6ይህ በጥጃ ምስል የተሠራ ጣዖት በአናጢ እጅ የተሠራ ስለ ሆነ አምላክ ሊሆን አይችልም፤ ስለዚህ በጥጃ ምስል የተሠራው የሰማርያ ጣዖት ተሰባብሮ ይወድቃል። 7እነርሱ ነፋስን ዘርቶ ዐውሎ ነፋስን እንደሚያጭድ ይሆናሉ፤ ዛላ የሌለው የእህል አገዳ ምግብ ሊሆን አይችልም፤ ፍሬ ቢኖረውም እንኳ የሚበሉት ባዕዳን በሆኑ ነበር። 8የእስራኤል ሕዝብ በአሕዛብ መካከል ተውጠው ቀርተዋል፤ ዋጋ እንደሌለው ዕቃም ሆነዋል። 9ብቻውን እንደሚንከራተት የምድረ በዳ አህያ ወደ አሦር ሄዱ፤ እንዲጠብቁአቸውም ዋጋ በመክፈል መንግሥታትን ተለማመጡ፤ 10መንግሥታትን ለመለማመጥ ዋጋ ቢከፍሉም እንኳ እኔ በአንድነት እሰበስበዋለሁ፤ ነገሥታትና መሳፍንት በሚያደርጉባቸው ጭቈና እየመነመኑ ይሄዳሉ።
11“የእስራኤል ሕዝብ ብዙ መሠዊያዎችን ለኃጢአት ማስተስረያ ብለው ሠርተዋል፤ ነገር ግን እነዚያ መሠዊያዎች የኃጢአት መሥሪያ ቦታዎች ሆኑ። 12እኔ ለእነርሱ ከሕጌ ብዙ መመሪያዎችን ጽፌ ሰጠኋቸው፤ እነርሱ ግን እንደ እንግዳ ነገር ቈጠሩት። 13እነርሱ ለእኔ ምርጥ መሥዋዕት ቢያቀርቡ፥ የመሥዋዕቱንም ሥጋ ቢበሉ እኔ እግዚአብሔር አልቀበላቸውም። አሁን በደላቸውን አስቤ በኃጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ፤ ወደ ግብጽም ይመለሳሉ።
14“የእስራኤል ሕዝብ ለራሳቸው ታላላቅ ቤተ መንግሥቶች ሠርተዋል፤ እኔን ፈጣሪአቸውን ግን ረስተዋል፤ የይሁዳም ሕዝብ ብዙ የተመሸጉ ከተሞችን ሠርተዋል፤ ስለዚህ ከተሞቻቸውንና ምሽጎቻቸውን የሚያቃጥል እሳት እልክባቸዋለሁ።”
Currently Selected:
ትንቢተ ሆሴዕ 8: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997