ትንቢተ ኢሳይያስ 26
26
የድል መዝሙር
1በዚያን ጊዜ በይሁዳ ምድር የሚከተለው መዝሙር ይዘመራል፦
ጠንካራ ከተማ አለን፤
እንደ ቅጥርና እንደ ምሽግ የጸና መዳኛም አድርጎላታል።
2እምነቱን የጠበቀ እውነተኛ ሕዝብ እንዲገባ
የከተማይቱን በሮች ክፈቱ፤
3ጌታ ሆይ! በእምነታቸው ለጸኑ ሰዎች
ፍጹም ሰላምን ትሰጣቸዋለህ።
4ለዘለዓለሙም በእግዚአብሔር ታምናችሁ ኑሩ፤
ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም መጠጊያ አምባችን ነውና።
5በከፍተኛ ቦታ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያዋርዳል፤
ከፍ ከፍ ያለችውን ከተማ ያፈራርሳታል።
አፈራርሶም ከትቢያ ጋር ይቀላቅላታል።
6ጭቊኖች ይረማመዱባታል፤
በእግራቸውም ይረጋግጡአታል።
7አምላክ ሆይ! አንተ የጻድቃንን ጎዳና ታስተካክላለህ፤
መንገዳቸውም እንዲለሰልስ ታደርጋለህ።
8አምላክ ሆይ፥ ሕግህን እየጠበቅን በአንተ ተስፋ እናደርጋለን።
የልባችንም ምኞት የአንተ ገናናነት በሕዝቦች ዘንድ እንዲታወቅ ማድረግ ነው።
9ፍርድህ በምድር ላይ በሚሰፍን ጊዜ
የዓለም ሕዝቦች እውነትን ይማራሉ።
ነፍሴ በሌሊት አንተን ትናፍቃለች፤
በውስጤም ያለው መንፈስ አንተን ትሻለች።
10ክፉ ሰዎች ቸርነት ብታደርግላቸው እንኳ
መልካም መሥራትን አይማሩም፤
በዚህ ጽድቅ በሰፈነበት ምድር እያሉ እንኳ
ክፋት ከማድረግ አይቈጠቡም፤
ታላቅነትህንም አይገነዘቡም።
11አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤
አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤
ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤
ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ። #ዕብ. 10፥27።
12አምላክ ሆይ፥ ሰላምን አሰፈንክልን፤
ሥራችንን ሁሉ የፈጸምክልን አንተ ነህ።
13እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፥
ካንተ ሌላ ብዙ ገዢዎች ገዝተውናል፤
ነገር ግን የአንተን ስም ብቻ እናከብራለን።
14እነዚያ ሁሉ ሞተዋል፤ ዳግመኛም በሕይወት አይኖሩም፤
አንተም ቀጥተሃቸው ስለ ተደመሰሱ፥
ዳግመኛ አይነሡም፤ መታሰቢያቸውም ጠፍቶአል።
15አምላክ ሆይ! የምድራችንን ወሰን በየአቅጣጫው በማስፋት
መንግሥታችንን ከፍ ከፍ አደረግህ፤
ሕዝባችንንም አበዛህ፤
ይህም አንተ የምትከብርበት ሆኖአል።
16አምላክ ሆይ! በችግራቸው ጊዜ ፈለጉህ
በገሠጽካቸውም ጊዜ በጸሎት ወደ አንተ ተመለሱ።
17አምላክ ሆይ! ምጥ የያዛት ሴት በሕመሙ ተጨንቃ እንደምትጮኽ፥
እኛም በፊትህ እንዲሁ ሆነናል።
18እንዳረገዙ ሴቶች ሆንን፤ ምጥም ይዞን ነበር፤
ነገር ግን ምንም ልጅ አልወለድንም፤
ለምድራችንም ድል አላስገኘንላትም፤
19ሙታንህ ተነሥተው ሕያዋን ይሆናሉ፤
እናንተ በመቃብር ውስጥ የምትኖሩ፥ ተነሥታችሁ የደስታ መዝሙር ዘምሩ!
አንጸባራቂው ጠል ምድርን እንደሚያድስ
እግዚአብሔርም ከሞቱ ብዙ ጊዜ የሆናቸውን ተነሥተው
በሕይወት እንዲኖሩ ያደርጋል። #ዳን. 12፥2።
ፍርድና ከምርኮ መመለስ
20ሕዝቤ ሆይ፥ ወደየቤታችሁ ገብታችሁ በራችሁን ዝጉ፤ የእግዚአብሔር ቊጣ እስከሚያልፍ ለጥቂት ጊዜ ራሳችሁን ሸሽጉ፥ 21በምድር ላይ የሚኖሩትን ሕዝቦች ስለ ኃጢአታቸው ለመቅጣት እግዚአብሔር ከሰማይ መኖሪያው ይገለጣል፤ በዚያን ጊዜ በምድር ላይ ተሸሽገው የሚኖሩ የነፍሰ ገዳዮች ሥራ ይጋለጣል፤ ምድርም በላይዋ የፈሰሰውን ደም ታጋልጣለች። የተገደሉትንም አትደብቅም።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 26: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997
ትንቢተ ኢሳይያስ 26
26
የድል መዝሙር
1በዚያን ጊዜ በይሁዳ ምድር የሚከተለው መዝሙር ይዘመራል፦
ጠንካራ ከተማ አለን፤
እንደ ቅጥርና እንደ ምሽግ የጸና መዳኛም አድርጎላታል።
2እምነቱን የጠበቀ እውነተኛ ሕዝብ እንዲገባ
የከተማይቱን በሮች ክፈቱ፤
3ጌታ ሆይ! በእምነታቸው ለጸኑ ሰዎች
ፍጹም ሰላምን ትሰጣቸዋለህ።
4ለዘለዓለሙም በእግዚአብሔር ታምናችሁ ኑሩ፤
ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም መጠጊያ አምባችን ነውና።
5በከፍተኛ ቦታ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያዋርዳል፤
ከፍ ከፍ ያለችውን ከተማ ያፈራርሳታል።
አፈራርሶም ከትቢያ ጋር ይቀላቅላታል።
6ጭቊኖች ይረማመዱባታል፤
በእግራቸውም ይረጋግጡአታል።
7አምላክ ሆይ! አንተ የጻድቃንን ጎዳና ታስተካክላለህ፤
መንገዳቸውም እንዲለሰልስ ታደርጋለህ።
8አምላክ ሆይ፥ ሕግህን እየጠበቅን በአንተ ተስፋ እናደርጋለን።
የልባችንም ምኞት የአንተ ገናናነት በሕዝቦች ዘንድ እንዲታወቅ ማድረግ ነው።
9ፍርድህ በምድር ላይ በሚሰፍን ጊዜ
የዓለም ሕዝቦች እውነትን ይማራሉ።
ነፍሴ በሌሊት አንተን ትናፍቃለች፤
በውስጤም ያለው መንፈስ አንተን ትሻለች።
10ክፉ ሰዎች ቸርነት ብታደርግላቸው እንኳ
መልካም መሥራትን አይማሩም፤
በዚህ ጽድቅ በሰፈነበት ምድር እያሉ እንኳ
ክፋት ከማድረግ አይቈጠቡም፤
ታላቅነትህንም አይገነዘቡም።
11አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤
አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤
ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤
ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ። #ዕብ. 10፥27።
12አምላክ ሆይ፥ ሰላምን አሰፈንክልን፤
ሥራችንን ሁሉ የፈጸምክልን አንተ ነህ።
13እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፥
ካንተ ሌላ ብዙ ገዢዎች ገዝተውናል፤
ነገር ግን የአንተን ስም ብቻ እናከብራለን።
14እነዚያ ሁሉ ሞተዋል፤ ዳግመኛም በሕይወት አይኖሩም፤
አንተም ቀጥተሃቸው ስለ ተደመሰሱ፥
ዳግመኛ አይነሡም፤ መታሰቢያቸውም ጠፍቶአል።
15አምላክ ሆይ! የምድራችንን ወሰን በየአቅጣጫው በማስፋት
መንግሥታችንን ከፍ ከፍ አደረግህ፤
ሕዝባችንንም አበዛህ፤
ይህም አንተ የምትከብርበት ሆኖአል።
16አምላክ ሆይ! በችግራቸው ጊዜ ፈለጉህ
በገሠጽካቸውም ጊዜ በጸሎት ወደ አንተ ተመለሱ።
17አምላክ ሆይ! ምጥ የያዛት ሴት በሕመሙ ተጨንቃ እንደምትጮኽ፥
እኛም በፊትህ እንዲሁ ሆነናል።
18እንዳረገዙ ሴቶች ሆንን፤ ምጥም ይዞን ነበር፤
ነገር ግን ምንም ልጅ አልወለድንም፤
ለምድራችንም ድል አላስገኘንላትም፤
19ሙታንህ ተነሥተው ሕያዋን ይሆናሉ፤
እናንተ በመቃብር ውስጥ የምትኖሩ፥ ተነሥታችሁ የደስታ መዝሙር ዘምሩ!
አንጸባራቂው ጠል ምድርን እንደሚያድስ
እግዚአብሔርም ከሞቱ ብዙ ጊዜ የሆናቸውን ተነሥተው
በሕይወት እንዲኖሩ ያደርጋል። #ዳን. 12፥2።
ፍርድና ከምርኮ መመለስ
20ሕዝቤ ሆይ፥ ወደየቤታችሁ ገብታችሁ በራችሁን ዝጉ፤ የእግዚአብሔር ቊጣ እስከሚያልፍ ለጥቂት ጊዜ ራሳችሁን ሸሽጉ፥ 21በምድር ላይ የሚኖሩትን ሕዝቦች ስለ ኃጢአታቸው ለመቅጣት እግዚአብሔር ከሰማይ መኖሪያው ይገለጣል፤ በዚያን ጊዜ በምድር ላይ ተሸሽገው የሚኖሩ የነፍሰ ገዳዮች ሥራ ይጋለጣል፤ ምድርም በላይዋ የፈሰሰውን ደም ታጋልጣለች። የተገደሉትንም አትደብቅም።
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997