ትንቢተ ኢሳይያስ 30
30
ከግብጽ ጋር የሚደረግ ከንቱ ቃል ኪዳን
1እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዐመፀኞች ለሆኑ ልጆች ወዮላቸው! እኔ ባላወጣሁላቸው ዕቅድ መመራት ይፈልጋሉ፤ ከእኔም ፈቃድ ውጪ የቃል ኪዳን ውል በመፈጸም በኃጢአት ላይ ኃጢአት ይጨምራሉ። 2እኔን ሳያማክሩ ርዳታ ለመጠየቅ ወደ ግብጽ ይወርዳሉ፤ ግብጽ ከለላ እንድሆናቸው በመፈለግ በግብጽ ንጉሥ ይተማመናሉ። 3ነገር ግን የግብጽ ንጉሥ ጥበቃ ወደ ኀፍረት፥ የግብጽም ከለላ ወደ ውርደት ያደርሳቸዋል። 4መልእክተኞቻቸው ዶአንና ሐኔስ ወደሚባሉት የግብጽ ከተሞች ደርሰዋል። #ማቴ. 24፥29፤ ማር. 13፥25፤ ሉቃ. 21፥26፤ ራዕ. 6፥13-14። 5ሆኖም ለእነርሱ ኀፍረትና ውርደት እንጂ ምንም ዐይነት ጥቅምና ርዳታ ሊሰጥ ወደማይችል ሕዝብ መሄድ ለሁሉም አሳፋሪ ነው።”
6በደቡባዊ በረሓ ስለሚኖሩ እንስሶች የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፦ “መልእክተኞቹ የአንበሶች መኖሪያ፥ የመርዘኛ እባቦችና የበራሪ ዘንዶዎች መስለክለኪያ በሆነ አደገኛ አገር አቋርጠው ይሄዳሉ፤ በአህዮቻቸውና በግመሎቻቸው ውድ የሆኑ ስጦታዎችን ጭነው ምንም ርዳታ ልትሰጣቸው ወደማትችል አገር ይሄዳሉ። 7ከግብጽ የሚጠበቀው ርዳታ ከንቱ ነው፤ ስለዚህ ለግብጽ ‘መርዝ የሌለው እባብ’ የሚል የፌዝ ስም አውጥቼላታለሁ።”
የማይታዘዝ ሕዝብ
8እግዚአብሔር “አሁን ሄደህ ይህ ነገር ለሚመጡት ዘመናት ቋሚ ምስክር ይሆን ዘንድ እነርሱ እያዩ በሰሌዳ ላይ ቅረጸው፤ በመጽሐፍም ጻፈው” አለኝ። 9“እነርሱ ዘወትር የእግዚአብሔርን መመሪያ መስማት የማይፈልጉ ዐመፀኛ ዘርና የማይታመኑ ልጆች ናቸው። 10ነቢያትንም አፋቸውን ለማስያዝ እንዲህ ይሉአቸዋል፦ ‘ቀጥተኛ የሆነውን ነገር አትንገሩን፤ እኛ ልንሰማ የምንፈልገውን ብቻ ንገሩን፤ ለስላሳና ማረሳሻ የሆነውን ነገር አስተምሩን። 11ከመንገዳችን ወዲያ ዘወር በሉልን፤ ለእርምጃችንም መሰናክል አትሁኑብን፤ እኛ ስለ እስራኤል ቅዱስ ዳግመኛ መስማት አንፈልግም።’ ”
12ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ ቃል ይህ ነው፦ “እናንተ ማስጠንቀቂያን ንቃችሁ ይደግፈናል ብላችሁ በተማመናችሁበት በግፍና በማታለል ላይ እምነታችሁን ጥላችኋል። 13ስለዚህ ይህ በደላችሁ ተሰነጣጥቆ በማኰፍኰፍ ሊወድቅ እንደ ተቃረበና አወዳደቁም በፍጥነትና በቅጽበት እንደሚደርስበት እንደ ረጅም የቅጽር ግንብ ያደርጋችኋል። 14ከተሰባበረ በኋላ ለእሳት መጫሪያ ወይም ለውሃ መጥለቂያ የሚሆን ከፍ ያለ ገል እንኳ ከመካከሉ እንደማይገኝበት ተንኰታኲቶ እንደሚወድቅ የሸክላ ዕቃ ትሆናላችሁ።”
15የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በመመለስና በማረፍ ደኅንነትን ታገኛላችሁ፤ ጸጥ በማለትና በመታመን ኀይል ታገኛላችሁ፤ እናንተ ግን እምቢ አላችሁ። 16በዚህ ፈንታ በፈጣን ፈረሶች ላይ ተቀምጣችሁ ከጠላቶቻችሁ እጅ ለማምለጥ ታቅዳላችሁ፤ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ‘ፈረሶቻችን እጅግ ፈጣኖች ናቸው’ ትሉ ይሆናል፤ ነገር ግን አሳዳጆቻችሁ ከእናንተ የፈጠኑ ይሆናሉ። 17ከጠላት ወታደር የአንድ ሰው ዛቻ ከእናንተ ሺህ ሰዎችን እንዲሸሹ ያደርጋል፤ እናንተን በሙሉ አምስት የጠላት ወታደሮች በተራራ ላይ እንዳለ የሰንደቅ ዓላማ ምሰሶና በኰረብታ ላይ ያለን ምልክት ጥቂቶቻችሁ ብቻ እስክትቀሩ ድረስ ያባርሩአችኋል። 18ይህም ሁሉ ሆኖ እግዚአብሔር ምሕረት ሊያደርግላችሁ ተዘጋጅቶአል፤ እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ስለ ሆነ ሊራራላችሁ ወዶአል፤ ስለዚህ በእግዚአብሔር የሚታመኑ ሁሉ የተባረኩ ናቸው።”
እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚባርክ
19እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅሱም፤ እግዚአብሔር ርኅሩኅ ስለ ሆነ የእርሱን ርዳታ በመፈለግ በምትጮኹበት ጊዜ ሰምቶ መልስ ይሰጣችኋል። 20በብዙ መከራ ውስጥ እንድታልፉ እግዚአብሔር ይፈቅድ ይሆናል፤ ነገር ግን እርሱ ራሱ ከእናንተ ጋር በመገኘት ያስተምራችኋል፤ ዳግመኛም እርሱን በመፈለግ አትደክሙም። 21ከመንገድ ወጥታችሁ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ብትባዝኑ ከበስተኋላችሁ “ትክክለኛው መንገድ ይህ ነው! በዚህ ሂድ” የሚለውን ድምፅ ትሰማላችሁ። 22በብርና በወርቅ የተለበጡትን ጣዖቶቻችሁንም “ከእኛ ወዲያ ራቁ!” ብላችሁ በመጮኽ እንደ ረከሰ ነገር አሽቀንጥራችሁ ትጥሉአቸዋላችሁ። 23ዘር በምትዘሩበት ጊዜ ቡቃያችሁን ለማሳደግና ብዙ መከር እንድታገኙ ለማድረግ እግዚአብሔር ዝናብን ይልክላችኋል፤ ከብቶቻችሁም ብዙ የመሰማሪያ ቦታ ያገኛሉ። 24የምታርሱባቸው በሬዎችና አህዮች በጨው የታሸ መኖና በመንሽና በአካፋ ተገለባብጦ የጠራውን ገፈራ ይመገባሉ። 25በሕዝቡ ላይ እልቂት በሚደርስበት ጊዜ ከታላላቅ ተራራዎችና ከከፍተኛ ኰረብቶች የምንጭ ውሃ ይፈስሳል። 26በዚያን ጊዜ ጨረቃ እንደ ፀሐይ ትደምቃለች፤ የፀሐይም ብርሃን ከቀድሞ ሰባት እጅ የበለጠ ይሆናል፤ የሰባት ቀን ብርሃን ያኽልም ድምቀት ይኖረዋል፤ ይህም ሁሉ የሚሆነው እግዚአብሔር ራሱ በሕዝቡ ላይ ያመጣባቸውን ቊስል ጠግኖ በሚፈውስበት ቀን ነው።
እግዚአብሔር አሦርን እንደሚቀጣ
27እነሆ፥ የእግዚአብሔር ኀይልና ግርማ ከሩቅ ይታያል፤ ነበልባልና ጢስ የቊጣው ምልክቶች ናቸው፤ በሚናገርበትም ጊዜ ቃሉ እንደ እሳት ይነዳል። 28እስትንፋሱ እስከ አፍ ጢሙ ድረስ እንደ ሞላ ኀይለኛ የወንዝ ጐርፍ ነው። ሕዝቦችን በወንፊት እንደሚበጠር ብጣሪ አበጥሮ ያጠፋቸዋል። በመንጋጋቸውም ውስጥ የጥፋት ልጓም ለጒሞ ያጠፋቸዋል። 29እናንተ ግን ደስ ይላችኋል፤ በተቀደሰ በዓል ምሽት እንደምትዘምሩት ትዘምራላችሁ፤ የእስራኤል አምባ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዋሽንት እየነፉ እንደሚዘምሩት ሰዎች ትደሰታላችሁ።
30እግዚአብሔር ክቡር ድምፁን እንዲሰሙ ያደርጋል። በኀይለኛ ቊጣው፥ በሚያቃጥል የእሳት ነበልባል፥ በመብረቅ፥ በወጀብና በጠጣር በረዶ የሚወርደው ኀይለኛ ቅጣቱ እንዲታይ ያደርጋል። 31እግዚአብሔር በበትሩ ሲቀጣ በሚሰሙት ድምፅ አሦራውያን ይደነግጣሉ። 32አሦራውያንን በቀጣቸው ቊጥር የእግዚአብሔር ሕዝብ የከበሮና የመሰንቆ ድምፅ ያሰማሉ፤ አሦራውያንንም የሚዋጋቸው ራሱ እግዚአብሔር ነው። 33ከብዙ ዘመናት በፊት የአሦር ንጉሠ ነገሥት የሚቃጠልበት ቦታ ተዘጋጅቶ ነበር፤ ያም ቦታ ሰፊና ጥልቅ ሆኖ ብዙ እንጨት ተከማችቶበት ነበር፤ እንደ ዲን ጅረት የሚፈሰው የእግዚአብሔር እስትንፋስ እሳቱን ያቀጣጥለዋል።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 30: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997